Saturday, December 28, 2013

ግንቦት 7 እያካሄደ ያለው ማፊያዊ የግድያ እና የአፈና ዘመቻ ተጋለጠ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)

ግንቦት 7 እያካሄደ ያለው ማፊያዊ የግድያ እና የአፈና ዘመቻ ተጋለጠ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) December 29, 2013
እነዚህ ፎቶግራፍ ላይ የሚታዩ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ከኤርትራ ምድር ሸሽተው በበጎ አድራጊ ወገኖቻቸው እርዳታና ተባባሪነት በድብቅ ላይ ይገኛሉ። በግንቦት 7 ያዙልኝ ባይነት በሻዕቢያ አፋኝ ሰዎች እየታደኑ ስለሆኑ ተደብቀው ይገኛሉ። ታሪካቸው ወደ ታች እንመለከታለን።
ካረንት አፌርስ (ECADF) (ኢትዮጵያን ካረንት አፌርስ) ድረገጽ እና ፓልቶክ በተባለ የመወያያ መድረክ ላይ ተለጥፎ በነበረው አስፈሪ የማፊያ መሳይ ማስተወቂያ ነው ጽሑፌን የምጀምረው። ቴድሮስ ይባላላል። የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋይ የነበረ ነው። ስለ ቴድሮስ መታፈን እና ግድያ ከላይ በጠቀስኩት የግንቦት 7 ደጋፊ ድረገጽ የተለጠፈው አስፈሪ ማስታወቂያ እንዲህ ይነበባል፡

ይ ህ ሰው   አደ ገኛ    ይፈለጋል!! የሚል ስታወቂያ  ከረንት አፌርስ የመ ያያ ረክ እና ድረገጽ ላይ  ተለጥፎ የነበረ ነው። እንዲህ ያለ አስፈሪ እና የሰው ልጅ በነፃነት ምርጫን የመምረጥ ተጻራሪ የአፈና ባሕሪ ሚዲያዎች ተባባሪዎች ሆነው የግድያ እና የአፈና ስራ እንዲቀጥል ሲጥሩ ማየት አስፈሪ ክስተት ከመሆን አልፎ፤ እንዲህ ያለ የግድያ እና የሰው ልጅ ማስፈራራት ባሕሪ ማስታወቂያ መለጠፍ የሚያሳየን ምልክት ቢኖር በሚቀጥለው መጪው ስርዓትም ቢሆን የግንቦት 7  መሪዎች እና ተከታዮቹ ስልጣን ላይ ቢወጡ ከወያኔ እኩል ወይንም በባሰ መልኩ አፋና እና ነብሰገዶዮችን በሕዝቡ ላይ የሚያሰማሩ መሆናቸው ጠቋሚ ምልክት ነው።ኢካዴፍ እና ኢሳት የመሳሰሉት ሁሉ የግንቦት 7 ፕሮፓጋንዳ አሰራጪዎች ስለሆኑ የምትለግሱት የገንዘብ ዕርዳታ ካለ ካሁኑኑ አቋማችሁን መመርመር ይኖርባችሗል።
 
ባለፈው ዓመት በውሽት ደልለው ከወሰዷቸው መካክል ዕድል አጋጥሞት ያመለጠው ቴዎድሮስ የሰጠውን ምስክርነት እዚህ በመጫን ያዳምጡ።http://ginbot7d.org/audio/LetterInsiderPartf1.m3u http://ginbot7d.org/audio/LetterInsiderFromPartf2.m3u ይህንን ሰው ነው ኢካዴፍ/ECADF የተባለው ድረገጽ “አደገኛ ተፈላጊ” እያለ ታድኖ እንዲታፈንና እንዲገደል በሕይወቱ ላይ ማስተወቂያ ለጥፈውበታል። አሁን በየቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ባቋቋሙት “መንግስታቸው” ሰው አንዲታፈን ሲያዙ መንግሥት ሲሆኑ ምን ያደርጉን ይሆን? ድረገጹ የሚያከሂደው ግለሰብ ደግሞ ከናዳ ውስጥ የሞቀ ኑሮ እየኖረ ነው ሰው ለምን ከአንዳርጋቸው ጽጌ አፈና እና ብልሹ ችሎታ ሸሸ በማለት የሸሸ ሁሉ መገደል አለበት እያለ በድረገጹ እና በፓልቶክ ክፈሉ የለጠፈው (ድረገጽና ፓልቶኩ  የሚያካሂዱት ሰውየው እንደልቡ ሲሆን ሴትዮዋ ደግሞ ሙያየ ምስክር እያለች ራስዋን የምትጠራ የድሮ ራዲዮን ሰራተኛ ነበረች የምትባል የትግሬ ሕዝብ ጠሊታነቷ በግልጽ በመናገር ዘረኛነቴን እኮራበታለሁ አንጂ  አላፍርበትም “ከእንግዲህ ወዲህ ዘረኛ ነኝ” እያለች የምትናገር በዘረኛነቷ የምትኮራ ሴት ነች )። ይህ ፓልቶክ እና ድረገጽ ነው ታማኝ በየነ የተባለው የኢሳት አፈቀላጤ “ሓብላቒ” በትግርኛው ቋንቋ ሓብለቒ (ማርኛው ምናልበት ዘብራቂ (?) “እናት ክፍሌ” እያለ በማሞኳሸት የሚኩራራበት እና  የሚጠራው። አንዳንድ ተቺዎች ይህንን የፓልቶክ ክፍል በዘረኛ እና በሰካራሞች ሁሌም ስለሚጣበብ  “በቅባ ቀዱስ ታጥቦ የማይጠራ ክፍል” ይሉታል፤፡

ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ‘የተባሉ ሁለት የወያኔ  አገልጋይ የነበሩ ወዳጆቹም (በተለይም አንዳርጋቸው ጽጌ ወያኔን በመወከል ፋሺስታዊው የወያኔ የጐሳ ርዕዮተ አለሙ ክፍል ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ተወካይ እና ግምባር ቀደም ተሟጋች ካድሬ እንደነበረ እራሱ ነግሮናል።)

እነኚህ ሁለቱ ‘ቅንጅት’ ሲባል የነበረው ሀገራዊ የፖለቲካ ተቃወሚ ድርጅትን እንዴት ሾልከው ገብተው አንዳመከኑት ብዙዎቻችሁ ታስታውሷቸዋላችሁ።

ከዚያም ቀጥለው በርቱካን መዲቅሳ የተባለቺው ወጣት ዳኛን አንደ አበባ መሃላቸው ላይ በማስገባት እሷን እየገፉ እነሱ ከሗላ ሆነው የተጫወቱት ማፊያዊ “ኮንሰፒራሲ” ተንኮላቸው አንዴት እንዳከናወኑት እና እሷንም ከሃይሉ ሻውል ቡድን ነጥለው ከጨዋታ ውጭ አንዴት  እንዳደረጓት ታስታወሳለችሁ። በሗላ ብርሃኑ ነጋ ኡደት ሲፈጽምበት በነበረበት አገር እዚሁ አሜሪካ ውስጥ በመቅረት “ምስጢራዊ እገዛ” እና እንክብካቤ ተደርጎለት ግንቦት 7 የተባለ  ተቃዋሚ ድርጅት በመመስረት በርከት ያሉ ‘አቃጣሪ ሊሂቃንን’ በማሰባሰብ ማሕበረሰቡን በማጃጃል መጠኑ የማይታወቅ የገንዘብ ገቢ እና ሙገሳ አግኝቷል።
የድርጅቱ መሪዎች ሥራ ተቀጥረው ኑሯቸው እየገፉ ለ6 ኣመት የህል ያለ ምንም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከኣገር አገር እየዞሩ ጅላጅሉን ሕብረተሰብ የሕልም እንጀራ እያስቦኩ አዳራሽ ውስጥ ሲያንጨበጭቡት ቆይተው በሗላ ከኤርትራው የሻዕቢያ መሪ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመገናኘት ወታደራዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ወደ አስመራ በመጓዝ የጠየቁት ተደረገላቸው። ሃረና በተባለው የማስለጠኛ ጣቢያ ቦታ ቢሰጣቸውም፤በሁለት አመት ውስጥ በድምሩ ከ37 ሰልጣኖች በላይ ማግኘት አልቻሉም። አሁን ከ7 እስከ 10 የሚሆኑ ታጋዮች እንደቀሩ ነው ከእዛው አምልጠው ነብሳቸውን ያዳኑ ታጋዮች እየገለጹልን ያሉ።
ከእስራት፤ ከድብደባ/ቶርች፤ከአምባ ገነናዊ ምስቅልቅ፤ከእርስ በርስ ንትርክ እና ድብድብ እና አናርኪ አስተዳዳር እየሸሹ ጎረቤት አገሮች ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ የግንቦት 7 ታጋዮች ሰሞኑን እያስተላለፉት ያለውን አስፈሪ አሳዛኝ ታሪክ እና የድረሱልን ተማጽኖ ግንቦት 7 ዲ በተባለው ድረገጽ ጥሪያቸውን ይፋ ሆኗል።
ሆኖም የህ የድረሱልን ጥሪ እና ግንቦት7 የተባለ በብርሃኑ ነጋ ፤ በኤፍሬም ማዴቦ እና አስመራ በሚኖረው አንዳርጋቸው ጽጌ የሚመራ ወንጀለኛ የማፊያ ድርጅት በነዚህ ግለሰቦች ሕይወት ላይ አደጋ ለመጣል ተሸሽገው ባሉባቸው አገሮች/በረሃዎች (በዊች ሃንት ዳሰሳ) በመከታታል አስጨንቀው “ሃራስ” በማድረግ አፍነው እንደገና ወደ ኤርትራ ለመውሰድ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ናቸው።
ይህ ዜና ግን የሕዝብ ዓይን እና ጀሮ ነኝ እያለ በውሸት የሚኮፈስ “ኢትዮጵያዊ ሚዲያ” ነኝ የሚለው ሌላኛው በግንቦት 7 በኩል በሻዕቢያ የሚደጐም ‘ኢሳት’ ሆን ብሎ ዜናው እንዳይሰራጭ አፍኖታል። ይህ በኢሳያስ እና በአረቦች ገንዘብ የሚተዳዳር ሳተላይት ቲቪ እና ራዲዮን የነዚህን ኢትዮጵያዊያን ፎቶግራፍ በግዳጅ ላይ እንዳሉ በማስመስል ሻዕቢያ በትከሻቸው ላይ የማያውቁትን ላውንቸር እና መትረየስ በግድ ጭኖባቸው ተሸክመውት የተነሱትን ፎቶግራፍ በየጊዜው በማሳየት ሕዝቡን በማሳሳት ዘመቻ በውሸት ተጠምዶ አንዴ ‘የድምሒት’ አንዴ የግንቦት 7 ‘ሕዝባዊ ሃይል’ ወታደራዊ ዜና እያለ ውሸት ሲያቦካ የነበረውን ዜና ጋብ በማድረግ ሕዝባዊ ሃይል ሲለን የነበረውን ወታደራዊ የግንቦት 7 ሃይል “ዛሬ” ምን በላው ለሚሉ ጠያቂዎች ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ጣቢያው በባለቤትነት ከሚያስተዳድረው ከግንቦት 7 ጋር አፉን ዘግቶ ይገኛል።
ይባስ ብሎ፤ ማስልጠኛ ጣቢያው ውስጥ አንዲት ጎጆ ከሁለት ፈርኬታ፤ጥቂት ሹካዎች ፤ሳህን አንዲት ትሎች የፈሉባት የደፈረሰ ውሃ የያዘች በርሜል፤ እና አንድ ‘ኮምፑተር ላፕ ታፕ’ እና 7 ታጋዮች ያሉት ‘ሕዝባዊ ሃይል” የሚባል ህይወት እንዳለው በማስመሰል የሚዋሸን “ኢሳት” የተባለው ጉደኛ  የዜና ጣቢያ፤ ባለፈው ወር “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል መሪ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመግደል የተላከ ነብሰገዳይ በሕባዊ ሃይል የስለላው ክፍል እና ችሎታ ተጋለጠ” በማለት አስቂኝ የሆነ የወያኔ  “አኬልዳማ’ የሚሉት የሚመስል ‘ድራማ’ በማዘጋጀት በተዳጋጋሚ በቲ ቪ ው ጋዜጠኞች ሲተች፤ሲኳል፤ሲሞገስ ሲለጠጥ እና ሲሰራጭ ሰምተናል።
ይህ ዜና ግን ውሸት የተጨመረበት መሆኑ በቅርቡ ታጋዮች አጋልጠውታል። ዜናው እውነትንት ቢኖረውም ግንቦት 7 እና የዚሁ ድርጅት ቲቪ የሆነው ኢሳት የተባለው ጣቢያ ያቀረቡት አቀራረብ ግን እጅግ የተጋነነ እና ውሸት የተጨመረበት እንደሆነ እና ‘የስለላና መረጃ ድርጅት” የሚባለው የግንቦት 7 ድርጅት “እንደሌለ እና ቢኖርም “ግድያ ከሸፈ” ከሚባለው ታሪክና ወቅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተጋልጣል። እራሱ በራሱ ፍላጐት አነሳሽነት ያጋለጠ “ሰላይ/ነብሰ ገዳይ ተያዘ” ተብሎ በግንቦት 7 እና በኢሳት የተሰራጨው የግለሰቡ ዜና  አጋጣሚውን ተጠቅመው ለድርጅቱ መጠቀሚያ ትኩስ ዜና ተደርጎ ማጋነኛ ፍጆታ /ለፕሮፓጋንዳ ስራ/ አንዴት እንደተጠቀሙበት ለሕይወታቸው ሰግተው አሁን ተሸሽገው ከሚገኙበት ቦታ በስልክ እውነተኛውን ምስጢር ነግረውናል።
ኢሳት ያስተላለፈው ዜና የሚጻረር አዲስ ክስተት ብቅ ሲል ግን ዜናው እንዳይታወቅ እና የነዚህ ግለሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ እያለ እያወቀ ጀሮ ዳባ ማለቱ ለግንቦት ሰባት የቆመው “ኢሳት” በተጋዮች ሕይውት አስኮናኝ የሚዲያ ጨዋታ እየፈጸመ ነው። በግንቦት 7 እና ኢሳት አፈ ጮሌዎች የተጠለፈው ጅላጅል ሕዝብ ግድ ባይኖሮውም እኛ የቁርጥ ቀን ጥቂት ልጆች የነዚህ ወገኖቻችን ሕይወት አየተካታተልነው መሆኑን ኢሳት የተባለው የዜና ማሰራጫ እንዲያወቅው ይሁን።
ኢሳት ከዚህ በታች የሚከተለው ታሪክ “በሚገባ ያውቀዋል። ለምሳሌ ግንቦት7 በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ውሸት ከሚችለው በላይ ሆኖበት ድርጅቱን በመልቀቅ የድርጅቱን ውሸትና የሚያደርሰውን አፈና እና ስቃይ በማስመልከት ዳንኤል የተባለው በቅርቡ ከድርጅቱ ሸሽቶ በኤርትራ አፋኝ ሃይሎች በእንዳርጋቸው ትዕዛዝ እየታደነ ያለው ዳኒኤል የተባለው የግንቦት 7 ታጋይ የተናገረውን እዚህ ያዳምጡ።
አሳት የተስፋዬ ገብረአብ ሻዕቢያነት ከሁለት አመት በፊት ሰነዱ እንደተገኘ አውቆት እያለ ከሕዝብ እንደደበቀው ሁሉ ኢሳትም ይህንን የዳኒኤል ቃለ መጠይቅ እና የድረሱልን ጥሪ ዜና ያውቃል። ሆኖም ሆን ብሎ ሌት ተቀን  የአንዳርጋቸው ጽጌ ግድያ ሙከራ ካንድ ገጽታ ብቻ አንዲታይ ያልጣረው የዜና ስርጭት እና መደበኛ ጊዜ ሰጥቶ ያላደረገው ፕሮፓጋንዳ ሙከራ አልነበረም።
ተቃዋሚ ነኝ የሚሉት አንዳንድ የዲያስፖራ ሚዲያዎች እያደሩ ማፊያዊ ሚዲያ ዓነት ለግለሰቦች አገልግሎት እና ዝና ውለዋል። በቅርቡ ይህ ኢሳት የተባለው የዜና ተቋም የግንቦት 7 መሪዎች እና የኢሳያስ አፈወርቂ ሰብአዊነት የሚሰብክ ልሳን በአንዳርጋቸው ጽጌ በኩል ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲተላለፍ ሲያደርግ፤ ኢካዴፍ ECADF (አትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ድረገጽ) የተባለ ፓልቶክ እና ድረገጽ  ደግሞ የበኩሉን ማፊያዊ የግንቦት 7 ስራውን ለመወጣት ሲል ከግንቦት 7 “ቶርቸር’ አምልጠው የሚመሸሹ ዜጎችን “ተፈላጊ ወንጀለኞች” እያለ እንዲታፈኑ እና በያሉበት አንዲገደሉ ማሰታወቂያ በመለጠፍ ፋሺስታዊ/ማፊያ የባሕሪ በሽታ እየተናወጠው ነው።
 


ይህ ፎቶ ከግንቦት 7 እና ሻዕቢያ  አፈናና ግድያ በመከራ አምልጠው ከወጡት የህዝባዊ ኃይል ተብየው  አመራሮች አባስ/ ማስረሻ (የስልጠና ከፍል ኃላፊ) አና ኮስሞስ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) ነው

ይህ ፎቶ የኢሳት ቲቪ እና ECADF;  የግንቦት 7 ድረገጾች እና ኢካዴፍ ሕዝብን ለማሞኘት ለጥፈውት የነበረ የውሸት ፎቶግራፍ ነው። ውሸትነቱ ደግሞ በዚህ ፎቶገራፍ ብረት ይዘው የሚታዩ በነሱነታቸው በሚዲያ የተነገደባቸው ሰዎች ለምሳሌ ለውንቸር ይዞ የተነሳው የግንቦት 7 የስልጠና ክፍል ሃላፊ ተብሎ ተመድቦ የነበረው “አባስ (ማስረሻ)” የሚባለው ታጋይ ሻዕቢያ ላውንቸር አምጥቶ ለፎቶ ግራፍ ፍጆታ በትከሻው ይዞ እንዲነሳ የተደረገ መሆኑን እና የያዘው ላውነቸር ምንነቱ አይቶት አንደማያውቅ በቃለ መጠይቁ ተናግሯል።አብሮት ያለው መትረየስ የያዘው ደግሞ ዘመኔ ካሴ ይባላል። እሱም አንደዚሁ በትከሻው ተጭኖበት ለፎቶ ፍጆታ ግንቦት 7 የተጠቀመበት የውሸት እይታ ነው። በዚህ ጽሑፍ ላይ የተለጠፈው አውድዮ ቃለ መጠይቅ ለማስረጃ ይሆንዎት ዘንድ  ከራሳቸው ከአንደበታቸው ያድምጡ።
ይህ ጉደኛ ዘመን በእንዲህ ያሉ ተቃዋሚዎች እና የዜና ማሰራጫዎች እየታጀበ ጉደኛነቱ እያሳየን ያለው በጣም አስገራሚው የግንቦት 7 እና የኢሳት ቅንብር ውሸት ለየት ያደረገው የወሩ ጉደኛ ዜና ደግሞ  አንዳርጋቸው ጽጌ ለመግደል የተያዘው “ኦ ሚለዮኔም” በሚል ስያሜ የተቀነባባረው የግድያ ተልዕኮ ከወያኔ የተላከው ነብሰገዳይ በግንቦት7 የስለላ ድርጅት ተደርሶበት ተይዞ ስልክ ሲነጋጋር ለበርካታ ወራት በትእግስት እንዴት የስልኩን ልውውጥ እንዴት ይጠልፉት እንደነበረ ሳያፍሩ ለሕዝብ አስተላልፈውታል።
ታሪኩ ግን የግንቦት 7 እና የኢሳት ጋዜጠኞች አንዳናፈሱት ሳይሆን ልጁ በገዛ እራሱ ለነብሱ ሲል ኑዛዜ/ንስሃ ገብቶ ከላይ በፎቶግራፍ ለሚታየው ለዘመነ ካሴ (ለጋደኛው) ምስጢሩን ነግሮት ድርጅቱም ማወቅ አለበት ብሎ በንጽህና ራሱ በራሱ ያጋለጠና የሰጠ ሰው ንፀሁና መወደስ የነበረበት ሰው፤ የግንቦት 7 መረጃ ክፍል ደርሶበት ተጋለጠ ብሎ በውሸት ያልሆነ የሃሰት ወሬ አስሰምተውናል።
ሲያስደውለው የነበረው ደግሞ ዳኒኤል ነው።http://ginbot7d.org/audio/YegedeyaMukera.mp3 ዳንኤል ደግሞ በዚህ አውድዮ የምትሰሙት ከኤርትራ አምልጦ አሁን ከግንቦት 7 የሻዕቢያ አፈና የግድያ ቡድን ጥቃት ለማምለጥ ተደብቆ ሕይወቱ አደጋ እያንዣበበት ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ ነው። አስገራሚው ድራማ ደግሞ፤ ተፈላጊው ተገዳይ አንዳርጋቸው ጽጌ ሳይሆን “ሻምበል ዳዊት” የተባለ በወያኔ የሚፈለግ ኤርትራ ውስጥ የኒገኝ የአማራ ድርጅት አባል ተፈላጊ ነው። ነግር ግን ድራማው ወደ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደተደረገ ተደርጎ ተቀነባበረ። በሗላ ልጁ ግድያው ላንዳርጋቸው ጽጌ አንደተጠና ተደርጎ ‘ድራማ’ አንዲሰራ ከተገደደ በሗላ፤ በምስጢር ባንዳርጋቸው ፈቃድና ተባባሪነት ለሻዕቢያ ተላልፎ ለድብደባ እና ልዩ ምርመራ ለስቃይ ተዳርጎ እስካሁን ድረስ ሁኔታው የት አንዳለ የሚያውቅ ሰው የለም።
ይህ አሳዛኝ ወንጀል በግንቦት 7 ተቀነባብሮ በኢሳት ጋዜጠኞች በኩል ሰፊ ሽፋን እና ሰዓት ተሰጥቶት ሕዝብን በማደናገር ወንጀል ኢሳት ተባባሪ ሆኗል። ኢሳት የግንቦት7 እና በሻዕቢያ ገንዘብ የሚደጐም የዜና ተቋም ቢሆንም፤ ወደፊቱ ከዚህ መሳይ አደናጋሪ እና የሃሰተኛ ድርጅት ፕሮፓጋንዳ አሰራጭነት የወንጀል ተባባሪነቱ እንዲታቀብ እንማጸነዋለን።
ይህ የግንቦት ውሸት ዜና ኢሳት ሳይውቅ ነው ያሰራጨው አንኳ ቢባልም፤ ሰላዩን/ነብሰገዳይ ተብሎ የተወነጀለው ሰው እየተከታተለ ስልክ ሲያስደውለው ከነበረው በድራማው  ክንዋኔው የነበረው ታጋይ ዳኔኤል የሰጠው ቃለ መጠይቅ ይፋ ከሆነ በሗላ እንኳ ኢሳት (ገለልተኛ ሚዲያ ነኝ እንደሚለን እውነትነት ካለው) የዳኒኤልም ሆነ የቴድሮስ እና የመሳሰሉ በርከታ የግንቦት 7 (የሕዝባዊ ሃይል ተብዬ) ታጋዮች የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ዜና እና ያስተላለፉት ተማጽኖ አንደ ተቀረው ዜናዎቹ  ከየትም ድረገጽም ሆነ ከውጭና ከውስጥ አገር የዜና ማሰራጫዎች “ኮፒ ኤንድ ፔስት” አድርጎ ለሕዝብ እንደሚያሰደምጠው ሁሉ ፤የነዚህ ታገዮች የድረሱልን ጥሪም ሆነ በአንዳርጋቸው ጽጌ ትዕዛዝ በእስር ተዳርገው የቶርች ሰለባ የሆኑበትን የብሶት እሮሮ ለማስደመጥ ፈቃደኛነቱን አላሳየም። በዚህ ጥያቄ ኢሳት እምራለሁ ብሎ የተቀመጠ አንድ ደንቆሮ ኩናኩንት ብጤ በኢመይል ጠይቀው በዚህ ተፋጥጠን አንድ ሁለት ተባብለናል።
የኢሰት ጋዜጠኞች የነ ኮስሞስ (ከሳውዝ አፍሪካ ወደ ኤርትራ ወደ ግንቦት 7 ሰልጣና የሄደው) በቶርች በእስራት የተሰቃየ ልጅ፤ የነ ቴድሮስ፤ የነ ዳኒኤል ወዘተ… ሕይውት እና በፋሺሰት ባሕሪ የሚንቀሳቀሰው በዘረኛው በአንዳርጋቸው ጽጌ ብልሹ አምባገነን አሰራር ተበሳጭተው ትግሉን ጥለው ለመሰናበት ጠይቀው ማመልከቻ አስገብተው ለእስራት፤ድብደባ እና ሞት፤ አንዲሁም ለሻዕቢያ የዘንጋዳ ቆራጭ የዳረጓቸው አንዳርጋቸው ጽጌ እና ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ኤፍሬም ማዴቦ ለእነዚህ ሕይወት ተጠያቂዎች ናቸው። ይህ ተደብቆ የቆየው የግንቦት 7 ወንጀልና ምስጢር ያጋለጠው ዳኒኤልም ሆነ ሌሎቹ እየተከታተላችሁ ለማደን እና ለማፈን የምታደርጉት የፋሺሰት ተግባር አንድታቆሙ ይህ ብዕርተኛ በጥብቅ ያስገነዝባል።
ግንቦት 7 ብሎ ራሱን የሚጠራ አጭበርባሪ የሻዕቢያ ተላላኪ በዜጎቻችን እና በታጋዮቹ ላይ እያደረሰው ያለው ግድያ እና ከድርጅቱ እየሸሹ የተደበቁ ሰዎችን እያባረረ ለማፈን እያደረገው ከአለው የወረበላ ባሕሪው ይታቀብ። አብዛኛዎቹ የግንቦት 7 መሪዎች ዋሺንግተን እና መኔሶታ ስቴት እየኖሩ በሰው ሕይወት ላይ ግድያ፤እስራት፤ቶርች አደና እና አፈና እንዲፈጸም ማድረግ እና ተባባሪ መሆን በሕግ አንደሚያስጠይቃቸው እና ለሚኖሩበት አገር እና የስደተኞች መስርያቤት እና አስሬ ወደ እሚሮጡበት ወደ ኮንግሬስ ጽ/ቤት እና ወደ ፕረዚዳንቱ ጽ/ቤት አቤቱታ ማቅረብ እንደምንችል እንዲያውቀት።  ይህ ብዕርተኛ በእነዚህ እየታደኑ ሽሽት ላይ ባሉት ሰዎች ህይወት የሚደርሰው አደጋ የግንቦት 7 መሪዎች እና ሚዲያዎቻቸው አንደሚሆኑ በብርቱ ማስጠንቀቂያ ያስገነዝባል!!!!!!! I am not joking here!
አሜሪካ ኮንግሬስ ድረስ እየሮጡ ስለ ሰብአዊነት መቆርቆርና ስለ ዲሞክራሲ ማጣት መለፍለፍ ፤ አውሮጳ አገረሮች እየሁዱ ገንዘብ ድጐማ መስበስብ ባንፃሩ ሰዎች እያሳፈኑ እና እየገደሉ እያሳደዱ ሰው መስሎ መለፍለፍ ማብቃት አለበት። የግንቦት 7 የሻዕቢያ አፋኝ ቡድን አፈና ለማምለጥ ተሸሽገው ካሉት ወገኖቻችን የተሰጠ የድረሱልን ጥሪ ለማንበብ ከዚህ በታች ቀርቧል። የሰብአዊ ድርጅት ተሟጋች ነኝ የሚል የኢሳት ሰውየም በመደበኛ የሰብአዊ ጉዳይ ክፈለጊዜው ሃቅ ካለው ይህንን አቤቱታ ለሕዝብ ይፋ አንዲያደርገው ይህ ጸሓፊ በብርቱ ያሳስባል።http://www.ginbot7d.org/documents/ኤርትራየሚፈፀምወንጀል.pdf  የሙለው እና ከዚህ ጋር በማያያዝ “ከግንቦት 7 የቀን ጅቦች እና ከሻዕቢያ መንጋጋ ያመለጡ ታጋዮች” የሚለውን http://www.ginbot7d.org/ ሙሉውን ያንብቡ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com Google-it!!!!!-(Ethiopian-Semay) www.ethiopiansemay.blogspot.com
 
 





Wednesday, December 11, 2013

የጌታቸው ረዳ መልዕክት በስዊድን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ህዝባዊ ስብሰባ

የጌታቸው ረዳ መልዕክት በስዊድን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ህዝባዊ ስብሰባ
 
የተከበራችሁ ክቡራን እህቶች እና ወንድሞች፤

እንዲሁም የጉባኤው አዘጋጆች።

በአካል በስብስባው ባለመገኘቴ ይቅርታ እየጠየቅኩኝ ፤ በዚህ ደብዳቤ ላስተላልፈው የፈለግኩት መልእክት ጉባኤው ስለተጠራበት ጉዳይ ትንተና ለመስጠት ሳይሆን ማስገንዘብያ ብቻ ነው። በአካል ስለማልገኝ ትንታናውን ለሌሎች ወንድሞቼ እንዲወጡት ትቸዋለሁ።አድማጩ አንዲያውቀው አስፈላጊ ነው ስለምለው ጉዳይ አነጋጋሪ ስለሆነ አጭር መልእክቴ እነሆ።

እኔ በተወለድኩበት ትግራይ ክፍለሃገር ውስጥ ወያኔ የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት መነሻ አድርጐ ያሰራጫቸው መግለጫዎቹ መሰረት በማድረግ “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ብሎ እራሱን ሰይሞ ወደ ጫካ በመግባት ከደርግ ወታደራዊ መንግሥት ጋር ባካሄደው የትጥቅ ትግል በተለያዩ ምክንያቶች “በለስ ቀንቶት” ደርግን አሸንፎ የመንግሥት መንበር ከተቆጣጠረ ወዲህ ኢትዮጵያን እንደ ደቡብ አፍሪካ ዘረኛው የነጮች መንግሥት በጐሳ/በቋንቋ አስተዳደር አዋቅሮ “ጸረ አማራ” ሕብረተሰብ እና “ጸረ አገር” ዕቅድ ነድፎ ሕዝቧን እና አንድነቷን ለማበጣበጥ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት በጽሑፍም በቃለ መጠይቅም በመጽሐፍቶቼም ገልጫለሁ።

 

አሁን በሥልጣን ላይ እየባለገ ያለው “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ” በታሪካችን ውስጥ ለጆሮ እና  ለዓይን የሚከብዱ፤ በሕዝባችን እና በአገራችን ሉአላዊ ክብር ላይ ብዙ አስነዋሪ ወንጀሎች የፈጸመ ቢሆንም፤ ለዓይን እና ለጀሮ ጐልቶ የሚታየው ጥቃት በአማራ ሕብረተሰብ ሕይወት ላይ ፈጽሟል። ይህ የአማራ ጥቃት ከመላ የተለያዩ የአገሪቱ ጐሳዎች ሁሉ በይበልጥ የጥቃት ማሕደሩ የተከመረው በአማራው ላይ ነው።

በዚህ ጎሳ (ዘር/ሀረግ) ላይ ያነጣጠረው የወያኔ ጥቃት በምንም መለኪያው በማንኛውም ጎሳ ላይ የደረሰው ጉዳት ሲነጻጸር የት የሌለ ነው። አማራው ለዘመናት ሲኖርባቸው አካባቢዎች ውጣ እየተባለ ከነቤተሰቦቹ ሲባረር፤ኦሮሞው፤ትግሬው፤አደሬው፤ሶማሌው፤አፋሩ፤ጋምቤለው፤ወላይታው፤ወዘተ…ወዘተ… አልተባረረም። ከነ ነብሱ ወደገደል ተገፍትሮ አልተጨፈጨፈም።በዚህ-ከተማመንን፤አማራው ለምን ለብቻው ጥቃቱ አንዲነገርለት ተፈለገ ብለው ለሚጠይቁን ዜጎች ለምን አንድንጮኽለት እንደተፈለገ ግልጽ ይሆንላቸዋል።

ከላይ አንደገለጽኩት የዚህ ሕብረተሰብ ጥቃት እና መፍትሔው ምን መሆን እንዳለበት ለመግለጽ በአካል ስላልተገኘሁ በጽሑፍ መዘርዘሩ ቦታ ስለማይበቃ፤ይህንኑ ገለጻ ለወንድሞቼ በመተው አድማጩን ለማስገንዘብ የምፈልገው ነገር  አለኝ የምለው ነገር የሚከተለው አጭር ማስገንዘብያ ነው።

ይኸውም፤ ይህ ጉባኤ ለምን በአማራ ጥቃት ላይ ማተኮር አንዳለበት ቅሬታቸውን በማሰማት በግል ‘በቴክስት’፤ ‘በኢመይል’ መልእክት እና ‘በስልክ’ በጉባኤው  እንዳልሳተፍ ከተሳተፍኩ ደግሞ በሚዲያ ስሜን እንደሚያጠፉት በማስጠንቀቅያ መልክ ያስጠነቀቁኝ ወገኖች እና የአማራው ልዩ ጥቃት ሁኔታው መረዳት የተሳናቸው ግብዝ ወገኖች አንዳሉ ለማስገንዘብ እፈልጋለሁ።

እነኚህ ግለሰቦች ያልተረዳቸው ሁኔታ ‘አማራው’ ከማንኛውም ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ተለይቶ “በሻዕቢያ”፤ “በወያኔ” ፤ “በኦነግ”፤ ዓረባዊ ነኝ በሚለው “ኦብነግ” እና በተቃዋሚው ክፍል የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የዜና ማሰራጫዎች፤በተለይ በውጭ አገር የተቃዋሚውን መልሕቅ የተቆጣጠረው ከኤርትራ ሻዕቢያው ቡድን ጋር የተቆራኘው ግንቦት 7 ብሎ እራሱን የሚጠራው “ጸረ አማራ” ኤሊቱ ክፍል በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የአካል እና የስነ ልቦና ስብራት አድረሰውበታል።

ተምረናል ብለው ራሳቸውን የሚያመጻድቁ ግብዝ ኤሊቶች አማራውን ሕብረተሰብ በመጽሐፋቸው “ቀጥቅጠውታል” (የዘረኛውን የአንዳርጋቸው ጽጌ ‘የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ- በጥሞና ማንበብ አለባችሁ)። በጥይት ረሽነውታል። እርጉዝ እናቶች እና እህቶች ከነህይወታቸው ወደ ገደል ተወርውረዋል። ከሚኖሩበት አካባቢ በጉልበት ተገፍተው ንብረታቸው ሳይዙ እና ከቤተሰቦቻቸው እየተነጠሉ ፡ አንዳንዶቹ ከመቅጽበት አንዳንዶቹ ደግሞ በ24 ወይንም በ48 ሰዓት የጊዜ ገደቦች ተሰጥቷቸው አንዲባረሩ ተደርጓል።  

በጥቂት አመታት ልዩነት የሌሎቹ ጎሳዎች የሕዝብ ቁጥር ሲጨምር አማራው ግን  2 ሚሊዮን አማራ ሕብረተስብ ከምድረገጽ መጥፋቱ በእኛ ጥናት ብቻ ሳይሆን በወያኔ ስታትስቲክ ጭምር ወያኔ በፓርላማው አምኖ ገልፆታል። በወጣት እናቶች እና በአዛውንቶች ክብር ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ‘ዓይነ ስውራን’ ወንዶች አዛውንቶች ‘ብልታቸው’፤እናቶች ደግሞ ‘ጡታቸው’ በቢላዋ ተሰልበዋል።  ህፃናት በትምህርት ገበታ ላይ አንዳሉ አንዳይወጡ የየክፍሎቻቸውን መዝግያዎች ተቆልፎባቸው ከነ ነብሳቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተለኩሶባቸው አልቀዋል። እናቶች አንዳይወልዱ ማሕጸናቸው አንዲደርቅ መርዝ አንዲወጉ ተደርጓል።  አሁንም ጥቃቱ አላባራም።  

ግብዦቹ ‘ይህንን ጥቃት’ ነው “አታጋልጡ” የሚሉን።በዚህ ጉባኤ ስለ አማራ ጥቃት እና ውረደት ስቃይና መከራ ለሕብረተሰብ መንገር “ጸረ ኢትዮጵያዊነት” ነው እያሉ የአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ተሸፍኖ እንዲቀጥል በማወቅም ባለማወቅም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ወገኖች አንዳሉ ለመግለጽ እወዳለሁ።

በተለይ ለምን አንደዚህ አንደሚሉ ጥቂት ልበል። ስለ አማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ማጋለጥ፤መፈትሄ ማፈላለግ ማለት የወያኔ የጐሳ አወቃቀር ፖለቲካ መከተል ነው በማለት “ጐሰኝነት” ነው ይሉታል። ይህ “ጥርቅም” ያለ “ድንቁርና” ለወያኔዎች እና ለመሳሰሉ ለጸረ አማራ ቡድኖች የሚያመቻች ተጨማሪ ጥቃት ነው።

 

እኛ አማራው “ይገንጠል” የራሱ ክልል ይከልል፤በአካባቢው የሚኖሩ ትግሬዎች፤ኦሮሞዎች፤የደቡብ ሕዝብ ጎሳዎች ከአማራ አከባቢ መሬቶች ይባረሩ፤ይገደሉ፤ የሚል ቅስቀሳ እና አጀንዳ የለንም። እኛ እና ወያኔ በጎሰኛነት በመወንጀል የሚያያይዙን “ደንቆሮዎች” የዘር ማጥፋት ወንጀሉና ሰበቡ  አላጠኑም ወይንም ሆን ብለው የአማራው ጥቃት አንዲቀጥል የመሰሪ ቡድኖች ተላላኪዎች ናቸው ማለት ነው።ለመሆኑ ከኛ በላይ የጐሳ ፖለቲካ አምርሮ የተቃወመ እና በየሚዲያው የተከራከረ እና መጽሐፍትም የጻፈ ማን ነው? ማን በማን ላይ ነው ስለ ኢትዮያዊነት ለመመጻደቅ የሚሞክረው? ስለ አማራ ጥቃት መናገር እኛ ጐሰኞች፤እነሱ ልዩ “ኢትዮጵያዊያን” የሚሆኑበት በየትኛው መመዘኛቸው ነው?

በጣም የሚገርማችሁ ደግሞ፤ በቴክስት እና በስልክ ያስጠነቀቀኝ ግለሰብ “ዶክተር አስፋ፤ ዳኛ ከተማ ደኔ እና አንተ አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ስለ አማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ስትናገሩ ‘አማራ’ ወክሎናል የምትሉት የምስክር ወረቀት አሳዩን ማለቱ “በጣም አስገራሚ ድንቁርና ከመሆን አልፎ፤ ነገሩ በጣም አስቆኛል። ስለ ትግሬ ወይንም ስለ ኦሮሞ ጥቃት ስንናገር ወይንም “ታሪክ፤ባሕል፤ጦርነት፤ፖለቲካ” አንስተን ስንተነትን ይህ አነጋጋር ‘ወያኔዎች’ አንዲሁም ‘ኦነጐች’ ስለ ጎሳችን ‘እኛ’ እንጂ አንናተ አያገባችሁም፤ስለ እኛ ወክለህ ተናገርልን ብሎ የሰጣችሁ ፈቃድ አሳዩን፤ እያሉ በጠባብ ሕሊና የሚንቀዠቀዡት የጠባብ ቡድኖች ቅጂ ቅስቀሳ ሰለባዎች አንደሆኑ ነው የተረዳሁት።

ለነገሩ ወያኔም እኮ “ዲያስፖራ ተቃዋሚ ስለ አገር ውስጥ ላለው ሕዝብ መናገር አይችልም። መበት የለውም፤ ውክልና ወረቀት አምጡ፤ እያለ ድንቁርናውን እያስተጋባብን ነው። ታዲያ የኛ የምንላቸው ተቃዋሚዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ሲጠይቁን ከወያኔ ድንቁርና በምን ይሻላሉ?

ማን ወከላችሁ? ብሎ ለጠየቀኝ ሰው መልሱ ጥቃት የደረሰበት “አማራ ሕብረተሰብ” ስለ ጥቃቱ እንድንናገርለት በአንደበቱ ጥሪ አድርጎልናል! ይህንን የቴፕ ድምፅ ለማስረጃ አንዲደመጥ ልኬአለሁ። 45 ደቂቃ የፈጀ ዝርዘር  በኢትዮጵያን ሰማይ አውድዮ ቪድዮ ክፍል ተለጥፎ ይገኛል። ድረሱልን ያሉንን ጥሪ ግን ባጭሩ ይኼው። እነሆ ከ4 አመት በፊት ጥሪው በጀርመን ራዲዩ ። Active ethnic cleasning in Ethiopia በሚል ርዕስ በዩቱብ እና በኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ የተለጠፈው ድምፅ እነሆ ያድምጡ።

http://youtu.be/aJDyueu2Kek

የተጠቂዎቹን የድረሱልን ድምፅ መልእክቱ እንዳዳመጣችሁት፤ መልእክቱ የሚለው “ለሚመለከተው ክፍል እባካችሁ ስለ እኛ ስም ሆናችሁ አነጋግሩልን አደራ! አደራ! አደራ!”  የሚለውን የአደራ መልእክት ተንተርሰን ነው እኛም የተጠቂዎቹ አደራ ላለመብላት እዚሁ እየተነጋገርን ያለንበት እና ያስገደደን ምክንያት። ስለዚህ  ስለ አማራው ሕብረተሰብ እንደትናገሩ ማን ወከላችሁ? የውክልና የፈቃድ ወረቀት አሳዩን፤ በማለት የሚዘላብዱ እና ስለ አማራ ሕብረተሰብ እናቶች እና አባቶች ጥቃት ‘ትንፍሽ’ አትበሉ የሚሉን ወገኖች የአጥቂዎቹ ተባባሪዎች ከመሆናቸው በፊት ልቦና አንዲገዙ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ልመክራቸው እፈልጋለሁ ።

በዚህ አጋጣሚ በተጓዝኩበት አካባቢ አመች ሆኖ ካገኘሁት ከናንተው ጋር ለመቀላቀል እሞክራለሁ፡ ካልሆነልኝ ግን  ባለመገኘቴ እያዘንኩ፤ የዚህ ሕብረተሰብ ጥቃት ተጠንቶ  አጥቂዎቹ ወደ ሕግ የሚቀርቡበት ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበን፤ የተጠቂዎቹ ልሳን ዕርዱን በማለት ያስተላለፉትን  “አደራ!” ተግባራዊ ለማድረግ እንበርታ፤ በርቱ።

አማራው በዘር ማጽዳት ዘመቻ ሲጠቃ፤ በደፈናው “ስለ ኢትዮጵያ” ጥቃት እንጂ ስለ አማራ ጥቃት አትወያዩ የሚል ስሜት ያሰከራቸው አገራዊ ትርጉም በቅጡ ያልተማሩ ጋላቢዎች፤ የአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ሰሚ ጀሮ አንዳያገኝ የሚጥሩ ወገኖች እየጋለቡበት ካለው ልጓም የበጠሰ ስሜት መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

በዚህ መሰሪ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ የአማራ እናቶች ማህፀን ቢመክንም ከአጥቂዎቹ እጅ ያማለጣችሁ የአማራ ተወላጆች ሁሉ የእናቶቻችሁ እና የእህቶቻችሁ ትኩስ እምባ እንዲቆም ለማገዝ ሐላፊነቱ በናንተው በአማራዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ዘንድ የዜግነት ግዴታቸው አንዲወጡ ጥሬየን አቀርባለሁ።

በዚህ አጋጣሚ ከአማራ ሕብረተሰብ የተወለዱ ውጭ አገር እና ውስጥ አገር የሚኖሩ የሕግ ጠበቆች በየድረገጹ የሚያቀርቧቸው ሳምንታዊ/ወርሃዊ “የፖለቲካ ጅላጅል ትንተናቸውን” አቁመው የወላጆቻቸው እና የእህቶቻቸውን የድረሱልን ጥሪ፤ በቅርቡ በዓለም አቀፍ ፍርድ አጣሪ ተቋም በማመልከት “ኢትዮጵያዊያን ኦጋዴን ሶማሌ ተቃዋሚዎች” በወያኔ ላይ እንዳስመዘገቡት ክስ፤ እናንተም የወላጆቻችሁ እና የእህቶቻችሁን እምባ ማድረቅ እና ወንጀለኞቹን ወደ ሕግ የማቅረብ ሐላፊነት ከናንተው ይጠበቃል።

ይህ የክህደት ዘመን በመንደላቀቅ እና በምቾት ኑሮ በውጭም በውስጥም አገር ጆሮውን ደፍኖ ሰምቶ አንዳልሰማ ያጠረመመው ‘አማራው ልሂቅም ’ ሆነ በግንቦት 7 ስም ከኤርትራው ቡድን ጋር ትከሻ ለትከሻ እየተሻሸ ያለው አማራው ሊሂቅ እና ተከታየቹ ብቻ ሳይሆኑ ይህንን ጐሳ ያጠቁትና በመጽሀፍቶቻቸው እና በሕዝባዊ ንግግራቸው የዘለፉትና የከዱት፦ የንጉሥ ተፈሪ የልጅ ልጆች ነን የሚሉን ውጭ አገር እና በውስጥ  አገር የሚኖሩ መሳፍንቶች ‘አማራን እያጠቃ ካለው የወያኔ ቡድን እና መሪዎች ጋር በመተባባር’ አሳፋሪ የሆኑ የክህድት ተግባሮች ፈጽመዋል።

ለመግለጽ የፈለግኩት ጥንቃቄ የጎደለበት በውጭ አገር የስለላ መረቦች እየታገዘ የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ያለው የምሁሩ ክፍል ብቻ ሳይሆን፤ የንጉሱ የልጅ ልጆች ጭምር ስለ አማራ ጥቃት ከመጤፍ ያለመቁጠራቸው አንዱ አሳዛኝ እና መራራ ያደረገው ገጽታው ስታዘብ ሃዘኔ እጅግ የበረታ ያደረገዋል።

ይህ የክህደት ዘመን ስትመለከቱ “ለአማራው” ማን ያልቅስ? ስለ አማራው ጥቃት አንድትነጋገሩ “በስሜ አንድትናገሩልኝ ወክያችሗለሁ ብሎ የሰጣችሁ የምስክር ወረቀት ውክልና አሳዩን” የሚሉ ተቃዋሚ ነን የሚሉን የአማራ ተወላጆችም ሆኑ እንዲሁም  “አማራ ብቻ ስለ አማራ ቢናገር ያምርበታል፡ትግሬ የሆናችሁ ተቃዋሚዎች በዚህ ላይ አያምርባችሁም”፡ የሚሉን የወያኔ ሰዎች እና ተቃዋሚዎች የሚሰነዝሩትን አስገራሚ ተቃውሞ ጉባኤው እንዲነጋገርበት አሳስባለሁ።

የገረመኝ ነገር፡ ስለ አማራው ጥቃት መነጋጋር ማለት ስለ ኢትዮጵያ ጥቃት መነጋጋር አይደለም ወይ? ስለ አማራው ጥቃት እና እንዴት ይቁም የሚለው መነጋጋር እንዴት “ጐሰኝነት” ነው ያስብላል?

ስለ አማራ ጥቃት መቆርቆር በአገር በታኝነት ወይንም በጎሰኛነት አውቀውም ሆነ ባለማስተዋል የሚከሱን ወገኖች፤ ለጸረ አማራ ቡድኖች አመቺ መንገድ አመቻቺዎች እንዳይሆኑ የዕውቀት አድማሳቸው እንዲያሰፉ ከወዲሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

ከዚህ በተጨማሪ፤ በቅርቡ በሳውዲ አረብ በዘረኞቹ አረቦች የተቀነባበረው በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው የዘር ጥቃት ባንድነት አንደጮኽን ሁሉ፤ ከዚያ በከፋ መልኩ በወያኔ  እና በወያኔ ተላላኪዎች አማካኝነት በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የተፈጸመውና አሁንም በመፈጸም ላይ ያለው ጥቃት ተባብረን በመጮኽ ለዓለም ሕብረተሰብ ያላሰወቅንበት እና የሕግ ባለሞያዎች ነን ብለው በሳውዲ ዓረብ የደረሰው ጥቃት ለማጣራት ፈቃደኝነት ያሳዩን ወገኖች፤ ለምን በአማራው  ጥቃት ላይ ታከቱ? ወይስ ጥቃቱ በውጭ ሰው ስለተከናወነ ልዩ ጥቃት ሆኖ፤ በውስጥ ጠላት በአማራው የተፈጸመ ጥቃት ግን እንደ ጥቃት ውርደቱ አልተሰማንም? ለምን? አገር ውስጥ  ያለው ተቃዋሚም “ሰላማዊ ሰልፍ ሲታገድ” ፊቱን አዙሮ ወደ እየቤቱ ከመመለስ እና በጋዜጦች እሮሮ ከማሰማት ሌላ ምን አድርጓል? እስክንድር እና ጓደኞቹን አንኳ ለማስፈታት “የረሃብ አድማ ሲያደርጉ እና የተጥለቀለቀ እምቢታ፤ የስራ ማቆም አድማ፤ ልገማ ወዘተ.. ለማድረግ የማይችል “ድውይ” ተቃዋሚ ነው። አማራው በዚህ ዳይለማ/ ትንግርት ስቃዩ የሚጮኽለት አጥቷል። የታወቀው የህግ ባለሞያ ደ/ር ያዕቆብም “የተለመደው አፉን ከፍቶ የሕግ አንቀጽ ከመጥቀስ ሌላ” እሱ በደምብ አድርጐ ከሚያውቀው እና ከሰራበት የዓለም አቀፍ መድረክ ፍርድ ቤት እና የመሳሰሉት ተቋማት ወደ ውጭ አገር  ተጉዞ መሰል የሕግ ባለሞያዎችን አስተባብሮ ስለ አማራው እልቂት “የመሰረተው” አቤት ያለበት የሕፈግ ክስ የለም። ለምን?  

አሁንም አንድ ነገር ልጨምር። በሚገርም ሁኔታ ከማንኛውም ተቃዋሚ ጸሐፊዎች ቀድሜ በሳውዲ የደረሰው ጥቃት ስሰማ የጻፍኩት እኔ ነበርኩ። በዛው መልእክቴ ላይ “ኢትዮጵያዊያን የሕግ ባለሞያዎች ከውጭ አገር ባለሙያዎች ጋር በመነጋጋር ” ሳውዲ ድረስ ሄደው ጥቃቱ አንዲያጣሩ የጠየቅኩኝም የመጀመሪያው ሰው እኔ ነበርኩ (የለጠፍኩትን ፋይል እና ቀን ተመለክቱ)።  

በዛው አንጻር በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የደረሰው ጥቃት ከብዙ አመታት በፊት በተደጋጋሚ “የሕግ ባለሞያዎች” ጉዳዩን አጣርተው ወደ አለም ተቋማት አቤት አንዲሉም ተደጋጋሚ ተማጽኖየን አቅርቤላቸው ነበርኩ። በቅርቡ አምናም አንዲሁ ከብዙ አመታት በፊት አማራን በማጥቃት በጥቃቱ የተሳተፉ ግለሰቦች “ፎቶግራፋቸው” እና “አድራሻቸው” “የፈረስ ስሞቻቸው ጭምር” የት አንደሚገኙ ተልኮላቸው፤ “የክስ እና የማጣራቱ ሁኔታ ለመጀመር ዝግጁ አይደለንም ” ብለው መልስ የሰጡኝ አሁን በሳውዲ ሁኔታ ግምባር ቀደም ተዋናይ ሆነው የቀረቡ የሕግ ባለሞያዎች ስታዘብ፤ ይህ አማራ የተባለው ወገን “ተከላካይ ጠበቃ” ለምን አንዳጣ ሳስበው በጣም ይገርመኛል።    

የሕግ ባለሞያዎች ናቸው የሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በአማራው ሕብረተሰብ ፍትሕ ለማስገኘት እንዳይረባረቡ ያገዳቸው “ድልድይ” ምን ይሆን? የጀመሩት አቤቱታ ካለስ ለምን ይፋ አላደረጉትም?

ይህ ብቻ አይደለም።ስለ ሳውዲ ጥቃት ማንሳቴ ላልቀረ ለሳወዲ ተጠቂዎች ትብብር አንፈልጋለን በሎ የተመሰረተው ቡድን አንድ ነገር ልበል። ቡዱኑ ትብብራችሁ አንፈልጋለን ብሎ ለመላ ወገኖች ጥሪውን ካስተላለፈ በሗላ፤ “በኮሚቴው ውስጥ ካሉት አንዳንድ ወገኖች የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረንም፤ ችግሩ የጋራ በመሆኑ ለተጠቂዎቹ ሲባል ፖለቲካ ልዩነታችንን ለጊዜው ወደ ጐን ገፍቼ  እናንተ በምታዋቅሩት እርዳታ የገንዘብም ሆነ የሕሊና ድጋፍ ለማድረግ አቅሜን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡ በርቱ። መልሳችሁ እጠባበቃለሁ” ብዬ የላኩላቸውን “ኢመይል” ደብዳቤ እስካሁን ድረስ አንድ መስመር የምታክል ‘መልእክትህ ደርሶናል’ እንኳ መልስ አልሰጡኝም። ለምን? በጣም ግልጽ ነው። ይህ በፖሊተካ የነቀዘ ‘የኤሊት ስብስብ’ (ወንዱም ሴቱም) ነገሮችን የሚያዋቅረው ‘በቡድናዊ ትውውቅና የፖለቲካ ጥልፍያ’ የተተበተበ ኤሊት ክፍል ነው (ሚዲያውም ጭምር ያካተተ ‘አዲሱ አዲስ አበባዊ ኤሊት’)።  ይህ ስሞታ የኔ ብቻ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ቅሬታ አላቸው። ይህን በተመለከተ ለወደፊቱ የምትመለከቱት ስዕል ይሆናል።

የነዚህ ኤሊቶች ‘ደወል’ የሆነው “ኢሳት  ቲቪ  ስለ አማራው ጥቃት የጮኸ የመጀመሪያ የዜና ማሰራጫ ነው እያለ በውሸት ከንቱ የምጐሳ ንጥቂያ ሲያደረግ በጋዜጠኖቻቸው እና በተወካዮቻቸው አንደበት ሰምቻለሁ። ኢሳት የኦነግ፤ የሻዕቢያ፤ የኦብነግ ባንዴራ አሸብራቂ፤ የወያኔ ኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት ካርታ ‘ለጣፊ’ ቀስቃሽ ሚዲያ መሆኑ “የመጀመሪያው ቲቪ” ነኝ ቢል ያምርበታል። ኢሳት አሁን ነው የተመሰረተው። የጀርመን ራዲዩ፤ የቪኦኤ፤ የኢሕአፓው “ፍኖተ ራዲዮ”፤ የካናዳው የሃዋርያ ጋዜጣ፤ ኢትዮጵያን ረጅሰተር፤ መኢዐድ፤ ጦቢያ ጋዜጣ፤ በግል ደግሞ እነ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ እና እኔው እራሴ እና የመሳሰሉ ዜጎች እና ሚዲያዎች ኢሳት የሚባለው የግንቦት 7 አቀንቃኝ ሚዲያ ከመመስረቱ በፊት ስለ አማራው ሕብረተሰብ ጥቃት በሚገባ ለመላው ዓለም እያጋለጡ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የዘለቁት ተቋማት እንዳልነበሩ በማድረግ “ኢሳት” የመጀመሪያው የአማራውን ጥቃት ያጋለጠ ሚዲያ ነው ሲል ታማኝ በየነ በለመደው ዘባራቂነት ባሕሪው ሲዋሽ ሰምቻለሁ። ይህ ውሸቱ “ያረመው” ሰውም ሆነ ሚዲያ የለም። የነቀዘው ሕብረሰተሰብም ከነጠቃው ባሕሪ ጋር አብሮ ኖግዷል። ይህ ነጠቃ ባንዳንድ የነቀዙ ኤሊት ጸሓፊዎች እየተደገመ ነው።    

ይህ ማሳሰቢያ ባጭሩ ጉባኤው እንዲነጋገርበት ይህ መልእክት እያሳለፍኩ ፡ ጉባኤው አንዲሳካ ምኞቴ ነው።ትግሉ ረዢም እና መራራ ቢሆንም፤ በመጨረሻ ግን  የተጠቃው ሕዝብ ባሸናፊነት በድል ተራራ ላይ ቆሞ የተነጠቀው ክብሩን እና ሰንደቃላማው እንደገና ያውለበልባል።

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)-ካሊፎርኒያ  -ሳንሆዘ  (2006) getachre@aol.com