Saturday, February 26, 2011

US Peace Council Statement on Egypt:

ድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (this is diffrent book/story that is defferent than the Amharic indicated) (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com
ማሳሳቢያ ጉጉል ውስጥ “ጌታቸው ረዳ”ብላችሁ የኔ እና በኔ ድረ ገጽ ውስጥ የተለጠፉ ፎቶግራፎች በሙሉ ለማየት -ጉጉል ኢሜጅ”የሚለው ስትመርጡ የኔ ያልሆኑ የሌሎች ሰዎች ፎቶግራፎች ታያላችሁ ለማየት ብላችሁ ብትከፍቱት የድረ ገጽ አባለ ዘር (ቫይረስ) ሊያጠቃችሁ ሲሞክር ታያላችሁ። በኔ ላይ የተለጠፉ ከሆኑ የኔን የብሎግ አድራሻ በደምብ ተጽፎ ታዩታላችሁ። የኔ ኢሜጅ ካልሆነ መጠቆሚያችሁ ወደ ፎቶግራፉ መሃል ጠጋ ስታደርጉት ቫይረሱ በሚከተለው አድራሻ ከስሩ በአረንጓዴ ቀለም …ተጽፎ ታያላችሁ verf-Kampioen.comይህ ቫይረስ ነው። ቫይረሱን ለማየት ስትፈልጉ (በተለያዩ ሰዎች ፎቶግራፍ በስተጀርባ ተደብቆ ጎብኚዎችን የሚያጠቃው አባለዘር/ቫይረስ)ለማወቅ መጠቆሚያችሁ (mouse) ፎቶግራፎቹ ላይ/መሓል ላይ “ላላ” በማድረግ ሳትከፍቱት ጠጋ ካደረጋችሁት verf-Kampioen.com የሚል አድራሻ ታያላችሁ። ያ ተውሳክ/ቫይረስ ነው። ጤነኛ ከሆነ የኔን አድራሻ www.ethiopiansemay.blogspot.comታያላችሁ። በሌሎች ሰዎች ፎቶግራፍ በስተጀርባ ተሸሽጎ የሚያጠቃው ወረበላ ለሚመለከተው አመልክተን ለዙ ጊዜ እየተከታተሉት እንደሆነ ተነግሮኛል። የሕሊና በሽታ የተጠናወታቸው ሥልጣኔን ለማደናቀፍም ሆነ በፖለቲካ የተሸነፉ የወረበሎች ዐሽከሮች የማያደርጉት መፍጨርጨር የለም፤ ይህም ትግል ነው፡ ማጅራት መቺውን እየተጋፈጡ ጉዞ መቀጠል ሕግጋት ነው። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርጉ። የሚሻለው ፎቶግራፎቹ የሰጠሗችሁን አድራሻ ያለው ወይንም የሌለው መሆኑን በmouseማረጋገጥ ነው። ካልሆነም ኢመጅ በሚል ውስጥ ተሸሽጎ ስለሚያጠቃ “ጉጉል ኢመጅ”ውስጥ ስትገቡ የምትፈልጉት ስዕል ሰትፈልጉ የሌላ ሰው ስዕል በእግርጌው ግን የምትፈልጉት ሰው ስም ይታያል ያኔ በmouseመጠቆሚያችሁን ጠጋ ስታደርጉት የተውሳኩ /ቫይረሱ አድራሻ ያሳያችል፤ ያንን አለመክፈት ነው። አንዳንዴም ሌላ የቫይረስ አድራሻ ታያላችሁ።ለማንኛውም አስተማማኝ “ፀረ ቫይረስ” መከላከያ ገዝቶ መከላከል ያስፈልጋል። አሁን ወደ እለቱ ሐተታ እንግባ።እነሆ፦
US Peace Council Statement on Egypt: Victory Achieved, but the Struggle Against Imperialism Continues February 12, 2011 On February 11, 2011, the heroic and united people of Egypt spearheaded by the deeply disenchanted youth of that country — dealt a serious blow to the interests and policies of the imperialist powers, especially that of the United States, in Africa and the Middle East. With this victory, Hosni Mubarak joined the rest of the deposed imperialist puppets, in the dustbin of history. The US Peace Council congratulates the people of Egypt for this tremendous victory and expresses its deepest solidarity and support for their continuing struggles for independence, peace, freedom and social justice. Yet, despite this great victory, the people’s struggle is far from over. Although Mubarak has departed, the entrenched military and security apparatus of the Egyptian police state is still intact. Power has been transferred to the Egyptian armed forces, which has had 30 years of subservient ties to the US military and which is charged with defending the interests of the United States and Israel in the Middle East. However, with this popular victory, the US imperialism and the Egyptian military are now faced with an irreconcilable dilemma: respecting the genuine democratic rights and aspirations of the Egyptian people, or continuing to protect the repressive imperialist policies of United States, its European allies, and Israel in the region. With the transfer of power to the Egyptian armed forces, the period of pretence to neutrality has come to an end for the Egyptian Army. The Army must now decide which side it is on: US imperialism or the Egyptian people. Either way, the Middle East will not remain the same. At present, the US is following a policy of containment of the people’s movement. The plan is to create a façade of democratic state while preserving the existing imperialistic military, security and economic arrangements. Clearly, such containment is contrary to the interests and demands of the Egyptian people and can only lead to additional confrontations and bloodshed. It can only spread the movement to the rest of the region. Alternatively, the establishment of a genuinely democratic state in Egypt, based on the true national interests and aspirations of the Egyptian people, will undoubtedly lead to a loss of total US and Israeli control over the region. It will mark the beginning of the end for the imperialist domination of the Middle East. It is for this reason that the US Peace Council, along with all freedom- and peace-loving people of the world, follows the events in Egypt with great concern. The first phase of struggle has ended in the victory of the Egyptian people, but their struggle for genuine democracy continues. A concerted effort in support of the anti-imperialist struggles of the peoples of Egypt and the Middle East is needed. The US Peace Council calls upon its allies in the peace movement to redouble their organized efforts in support of the rightful struggles of the people of Egypt and the Middle East and demand that: • The US stop interfering in the internal affairs of Egypt, including use of direct military threats, manipulating the political process through funding or otherwise lending support to pro-US “opposition” figures, groups, NGOs and parties whose objective is to undermine people’s revolution. • President Obama immediately issue an executive order to stop all financial aid to the Egyptian military. • Mubarak’s bank accounts be immediately frozen and all the monies taken from the country be returned. • Trials be held for those who have committed crimes against the Egyptian people, including those who are still in power. • An end to the US-endorsed blockage of peaceful exchange between Egypt and the Palestinian people. • The United Nations guarantee the integrity, impartiality and freedom of the upcoming elections in Egypt. For a genuine democracy to be established in Egypt, the people must be able to exercise their will through a truly free and impartial election. Undoubtedly, such an election cannot be carried out by a government that is controlled by the military and the officials of the Mubarak regime. This makes the immediate transfer of power to a new pro-people interim civilian government necessary. The US Peace Council declares its full support for the struggles of the Egyptian people to achieve true democracy in their country. US Peace Council P.O. Box 3105 New Haven, Connecticut 06515 USA Telephone 203 387-0370 Fax 203 297-2539 E-mail Amistad.nai@rcn.com

Monday, February 14, 2011

ቀን ሲደርስ አምባ ሲፈርስ

>ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (this is diffrent book/story that is defferent than the Amharic indicated) (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com

ቀን ሲደርስ አምባ ሲፈርስ

ከዲዳክ

ተክለ ጻድቅ መኩርያ በጻፉት ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ዐፄ ቴዎድሮስ አንቱ የተባሉ ጉምቱ ጉምቱ መሳፍንትን እየረቱ ከቋራ ጎንደር የደረሱበትን ምክንያት ሲገልጡት «መኳንንቱ እና መሳፍንቱ የተጠናወታቸው መጠን ያለፈ ንቀት ነው» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁት ይህ ነው የተባለ የሚጠቀስ የነጋሢ ዘር የሌለው፣ «የኮሶ ሻጭ ልጅ»፣ ካሣ የተባለ ሽፍታ፣ አንድ አሥር ጀሌ አስከትሎ የት ይደርሳል? የሚል ንቀት ነበራቸው፡፡ ካሣ እቴጌ መነንን ድል ነሥተው እንኳን መሳፍንቱን ሊያስደነግጣቸው አልቻለም፡፡ ለውጡን ከጎንደር፣ ከመቀሌ እና ከጎጃም አብያተ መንግሥታት ነበር የሚጠብቁት፡፡ እነ ደጃች ውቤ፣ እነ ራስ ዐሊ፣ እነ ደጃች ጎሹ፣ እነ ደጃች ክንፉ፣ እነ ደጃች ወንድ ይራድ፣ አንዳቸው ሌላቸውን እንጂ ካሣን ለአልጋው አይጠረጥሩም ነበር፡፡

ሁሉም ምክንያታቸውን በአንድ ቃል ነበር የሚገልጡት «ይህ የኮሶ ሻጭ ልጅ የት ይደርሳል?» እያሉ፡፡ ከጎንደሯ ንግሥት ከእቴጌ መነን መኳንንት አንዱ የነበረው ደጃች ወንድይራድ «ይህን የኮሶ ሻጭ ልጅ አንገቱን እንደ ሙጭልጭላ አንቄ አመጣልሻለሁ» ብሎ ፎክሮ ነበር ጭልጋ ጫቆ ወረደ፡፡ ነገር ግን ያሰበው ከሽፎ በጦር ተወግቶ በካሣ እጅ ተማረከ፡፡ ካሣም «እናቴ ከገበያ ኮሶ ሳይሸጥላት የቀረ አለ፤ እህል ጠፍቷልና ይህንን ተመገብ» ብለው ደጃች ወንድይራድን የኮሶ ሻጭ ልጅ ብለው በተሳደበበት አፉ ኮሶ አጠጡት ይባላል፡፡

እቴጌ መነንም በሰኔ 1840 ዓም ካሣን ለመውጋት ሰባት ነጋሪት አገር አስከትተው ወደ ቋራ ሲጓዙ ከንቀታቸው ብዛት «ይህ ቆለኛ ወዴት አባቱ ሊገባ ነው ይሆን?» እያሉ የትዕቢት ቃል ተናገሩ ይባላል፡፡

ይህንን ክፉ ቃል የተናገሩትን እቴጌ መነንን ለመበቀል ካሣ ከማረኳቸው በኋላ በዋሻ ውስጥ አስገብተው ባቄላ አስፈጯቸው ይባላል፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ስለ ራሳቸው ኑሮ እና ሥልጣን ይጨነቁ ነበር እንጂ እየመጣ ያለው ነገር ሊታያቸው አልቻለም፡፡ አንድ ካሣ የሚባል ሰው ከቋራ ተነሥቶ ታሪክ እየሠራ መሆኑን ለማየት የሚችል ዓይነ ልቡና አልነበራቸውም፡፡

እንዲያውም ደጃች ጎሹ ዲ አባዲ ለሚባል ፈረንሳዊ በጻፉት ደብዳቤ «ተካሣ ጋር የተዋጋን እንደሆነ ጎንደር እገባለሁ፤ እንገናኛለን፡፡ ወደ ቆላ የሸሸ እንደሆነ ሰው ባገኝ እሰድልሃለሁ ፈረሱን» ብለው ጽፈው ነበር፡፡ ደጃች ጎሹ ካሣ እንደሚሸነፉ እንዲያውም ወደ ጫካ እንደሚሸሹ ነበር የሚያስቡት፡፡

ራስ ዐሊም ከደጃች ካሣ ጋር ታርቀው እናታቸውን እቴጌ መነንን ካስመለሱ በኋላ ካሣን ንቀው ተዋቸው፡፡ ካሣ ጎንደር ቤተ መንግሥት ደጅ ጥናት መርሯቸው ሀገራቸው ቋራ ሲሸፍቱ ቀድሞ የተሾሙበትን ርስት ደንቢያን ለደጃች ጎሹ ሰጧቸው፡፡

ሁሉም መሳፍንት እና መኳንንት የካሣን ጀግንነት እና ታሪክ ሠሪነት ለማየት የቻሉት ሊመለስ በማይችል አጋጣሚ ውስጥ ሆነው ነበር፡፡ ደጃች ጎሹ ጉር አምባ ላይ በኅዳር 19 ቀን 1845 ዓም በካሣ ሠራዊት ድል ከመሆናቸው ከቀናት በፊት

አያችሁት ብያ ይህንን ዕብድ

አምስት ጋሞች ይዞ ጉር አምባ ሲወርድ

ያንጓብባል እንጂ መች ይዋጋል ካሣ

ወርደህ ጥመድበት በሽንብራው ማሳ

እያሉ ያዘፍኑ እንደ ነበር የቴዎድሮስን ታሪክ የጻፉት አለቃ ወልደ ማርያም ይነግሩናል፡፡ ጎሹ እንደ ፎከሩት የሽንብራ ማሳ አልነበረም የገጠማቸው፤ እንደ አንበሳ የሚደቁስ የካሣ ክንድ እንጂ፡፡ በጦርነቱ ቆስለው ወዲያው ነበር ጎሹ የሞቱት፡፡

ይህንን የሰሙት ራስ ዐሊ አሁንም ንቀት አልለቀቃቸውም፡፡ ካሣ የሚባል ጀግና ሊዋጥላቸው አልቻለም፡፡ ከእውኑ ዓለም ይልቅ የሕልሙን ዓለም መርጠው «እኔ ለካሣ ጦር አልጭንም» ብለው በሦስት መኳንንት የተመራ ጦር ጎርጎራ ሰደዱ፡፡ ሚያዝያ 5 ቀን 1853 እኤአ ይህ ጦር በካሣ ሠራዊት ድባቅ ተመታ፡፡ ራስ ዐሊም ጭንቅ ውስጥ ገቡ፡፡ «ጦር አልጭንም» ማለት ትተው ካሣን አይቀጡ ቅጣት ሊቀጡ ሰኔ 23 ቀን 1845 ዓም አንድ መቶ ሺ ጦር ይዘው ጎርጎራ ወረዱ፡፡ የካሣን ጦር በመነጥራቸው አዩና «ሠርገኛ እንዳንለው በዛ፣ ጦረኛ እንዳንለው አነሰ» ብለው ዘበቱ፡፡

አይሻል ላይ የተደረገው ውጊያ እሳት እና ጭድ ሆኖ መቶ ሺው የዐሊ ሠራዊት በካሣ እጅ ተደቆሰ፡፡ ዐሊ ያልጠረጠሩት ሆነ፣ ያልገመቱት ደረሰ፤ ሊቀበሉት ያልፈለጉትን መራራ እውነት መዋጥ ጀመሩ፡፡ በመጨረሻዋ ሰዓት «ይህ በትር የእግዚአብሔር ነው እንጂ የሰው አይደለም» ብለው ራስ ዐሊ በየጁ አልፈው ራያ ወሰን ገብተው በዚያው ሞቱ፡፡

በመጨረሻ የቀሩት ደጃዝማች ውቤ «ቀን ደርሷል አምባ ፈርሷል» ይግቡ የሚል መልእክት ከካሣ መጣላቸው፡፡ ለአንድ የኮሶ ሻጭ ልጅ መግባት መደፈር ነው፡፡ ደጃች ውቤ «ምንኛ የጠገበ ነው አያ» ብለው ጦር አስከተቱ፡፡ ካሣን ገድለው ወይንም ማርከው ደረስጌ ላይ ሲነግሡ እየታያቸው ውቤ ገሠገሡ፡፡

የካቲት 3 ቀን 1847 ዓም ደረስጌ አጠገብ በተደረገው ውጊያ ውቤ ቆስለው ተማረኩ፡፡ በቴዎድሮስ እጅም ገቡ፡፡ መሳፍንቱ ሳይጠረጥሩ ዘመነ መሳፍንት አለቀ፡፡ መሳፍንቱ ሁሉ ዘመነ መሳፍንት ማለቁን የተረዱት ሁሉም ሲቆስሉ እና ሲማረኩ ነበር፡፡

«ቀን ሲደርስ አምባ ሲፈርስ መመለሻ የለውም» እንዲሉ በናቋቸው ካሣ ሁሉም ተረትተው ታሪክ ሆነው ቀሩ፡፡

ሆስኒ ሙባረክ የዛሬ ሃያ ቀን አካባቢ ግብፃውያን ወደ ጣሂር አደባባይ ሲወጡ ከጩኸት ያለፈ ነገር ይመጣል ብለው አልጠበቁም ነበር፡፡ ብርዱ ሲለበልበው፣ ሆዱ ሲሞረሙረው ወደ ቤቱ ይገባል ብለው ሕዝቡን ንቀውት ነበር፡፡ ቀን መድረሱን አምባ መፍረሱን መጠርጠር አልቻሉም፡፡

ውኃ በመርጨት፣ አንዳንዶቹን በማሠር፣ ትዊተር እና ፌስ ቡክ በመዝጋት፣ የሳተላይት ቴሌቭዥኖችን በማስተጓጎል፣ ጋዜጠኞችን በማንገላታት፣ ደጋፊዎቻቸውን በኃይል በማሠማራት ችግሩን በቀላሉ እፈታዋለሁ ብለው ገመቱ፡፡ እልፍ ሲልም የጉልቻ መለዋወጥ የመሰለ የሥልጣን ለውጥ አምጥተው ያላችሁትን ፈጽሜያለሁ ለማለት ሞከሩ፡፡ ሕዝቡ እርሳቸውን እየተቃወመ «የካቢኔ አባላቱ ስለ በደሉት እንጂ እኔንማ ሕዝቡ ይወደኛል» ይሉ ነበር፡፡

ያ ጣሂር አደባባይ የወጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ለእርሳቸው መወድስ ሊያቀርብ፣ ለዋሉለት ውለታም ሊያመሰግን፣ ለአመራራቸው ያለውንም አክብሮት ሊገልጥ የወጣ መሰላቸው፡፡ ሕዝቡ ማምረሩን፣ አንጀቱ መቃጠሉን፣ ቋቅ ብሎት አንገሽግሾት መውጣቱን መገመት አልቻሉም፡፡

ሕዝቡ «ይውረዱ» ሲላቸው እርሳቸው ስለ ልጃቸው ያወራሉ፡፡ ሕዝቡ «ይውረዱ» ሲላቸው እርሳቸው ስለ መስከረም ምርጫ ይደሰኩራሉ፤ ሕዝቡ «ይውረዱ» ሲላቸው እርሳቸው በቴሌቭዥን ቀርበው ምዕራባውያንን ይሳደባሉ፤ ጋዜጠኞችን ይኮንናሉ፡፡ ሕዝቡ «ይውረዱ» እያላቸው እርሳቸው «እኔ ከወረድኩማ ግብፅ አበቃላት» ይላሉ፡፡ ቀን መድረሱን አምባ መፍረሱን ማየት አልቻሉም፡፡

እርሳቸው በጦር ኃይል ነው የመጡት፤ ራሳቸውም ወታደር ናቸው፡፡ አገዛዛቸውም ወታደራዊ ነው፡፡ ጦር የሌለው ሕዝብ አደባባይ ቢውል ቢያድር፣ ቢራብ ቢበላ፣ ቢጮኽ ቢያቅራራ፣ ዳስ ቢጥል መፈክር ቢሰቅል፤ ቢሰለፍ ቢለፈልፍ ምን ያመጣል? ደግሞ ከመቼ ወዲህ በጩኸት መንግሥት ተቀይሮ ያውቃል? ሙባረክ ያነበቡት መጽሐፍ እንዲህ አይልም፡፡

እንዲያውም በመጨረሻ «እኔኮ እወድዳችኋለሁ» ብለው የዓመቱን ታላቅ ቀልድ ቀለዱ፡፡ ምክትላቸውም ብቅ ብለው «የሳተላይት ቴሌቭዥን አትዩ፤ እነርሱ ናቸው የሚያታልሏችሁ» ብለው በአሥር ዓመታት ውስጥ ተገኝቶ የማያውቅ ምክር ሕዝቡን መከሩ፡፡

«አልወርድም» አሉ ሙባረክ፡፡ ስዕለት ያለባቸው ይመስል ከመስከረም ወዲህ ወይ ፍንክች አሉ፡፡ ሕዝቡ ደግሞ ከጣሂር አደባባይ ወይ ፍንክች አለ፡፡ የሚያዩት ነገር እውነት ሳይመስላቸው፤ የናቁት ሕዝብ እየገነገነ መምጣቱ ሳይገለጥላቸው፤ ሰባት ወር የቀረውን መስከረም ሕዝቡ አሳጠረውና ሙባረክ ወረዱ፡፡

እኔ እንጃ፤ አሁን ራሱ ሲያስቡት «በሕልሜ ነው፣ ወይስ በውኔ፣ ወይስ በቴሌቭዥን» እያሉ ሳይቃዡ አይቀሩም፡፡ ከሳምንት በፊት እንኳን አሁን የሆነው ነገር ሊሆን ይችላል ብለው ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ አልነበራቸውም፡፡ ጦር ጭነው ያገኙትን መንበር ጦር ያልጫነ ያስለቅቀኛል ብለው እንኳን በታሪክ በተረት አስበውት አያውቁም፡፡ ግን

መናቅን የመሰለ የመሪዎች ክፉ በሽታ የለም፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ የተናቀው ተነሥቶ መሳፍንቱን ሁሉ ነድቶ ጎንደር ቤተ መንግሥት ይገባል፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ፣ የበጎች እረኛ ሙሴ እሥራኤልን እየመራ የኤርትራን ባሕር ያሻግራል፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ አገር ያንቀጠቀጠ ፈርዖን ባሕር ውስጥ ይወድቃል፡፡ ቀን ከደረሰ፣ አምባ ከፈረሰ ትንኝ ዝሆንን፣ ቁንጫም አንበሳን ትረታለች፡፡

ቀን ሲደርስ፣ አምባ ሲፈርስ በፈቃድ ያልሆነ በግዳጅ ይሆናል፤ እንደ ደጃች ወንድይራድ ኮሶ ያስጠጣል፤ እንደ እቴጌ መነን ባቄላ ያስፈጫል፤ እንደ ሙባረክ የሠላሳ ዓመት ቤት ጥሎ ያስኬዳል፡፡

ምናለ የአፍሪካ እና የዓረቡ ዓለም መሪዎች ዛሬ እንኳን ቢነቁ፡፡ ቀን እየደረሰ አምባ እየፈረሰ እኮ ነው፡፡

Monday, February 7, 2011

በስሜት ፈረስ መጋለብ አቅጣጫን ያስታል።

ድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (this is diffrent book/story that is defferent than the Amharic indicated) (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com

በስሜት ፈረስ መጋለብ አቅጣጫን ያስታልጌታቸው ረዳ ካረንት አፈይርስ የተባለው የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች የተደራጁበት “የኢንቴርኔት/የጠጅ ቤት” ቡድን (ፓል ቶክ ይሉታል መሰለኝ ፈረንጆቹ) ትናንት ማታ  እንዳያችሁት በስዕለ ድምፁ ላይ ያስተላለፈው ዘገባ እና ኢሳት የተባለው የስዕለ ድምፅ የዜና ማሰራጫም (መነፅር ያጠለቀ እዚህ በግራ በኩል ስዕሉ የሚታየው ሰውየ፤ የራዲዮኑ መልክት ማስተላለፊያ ድምፅ በእጁ ይዞ የኦጋዴን ነፃ አውጪ “ጣሊባኒሰት/ሙጃሃዲን ባንዴራ” የፎቶ ቁራጭ/ ክሊፕ ደረቱ ላይ computer screen ተለጥፎበት የሚታየው የኢሳት ዘጋቢ ከሆነ) መለስ ዜናዊን ለመቃወም ጀርመን ምዩኒክ ከተማ ድረስ በመሰባሰብ የመጡትን ሰልፈኞች ወደ ኢትዩጵያ ያስተላለፈው መልዕክት ከወንጀለኞቹ ሌላ የከፋው ወንጀል የሚፈጽም የራሱን ዘመን ብቻ ሳይሆን የመጪው ትውልድ ዕድል የሚያበላሹ፤ ከብሔራዊ ወንጀል ፈፃሚዎች ጋር የሚዳራ/የሚተሻሽ ስለሚያስመስለው በሚዲያው ላይ ግልጽ ዘመቻ ከመጀመራችን በፊት እርምጃውን በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታል እንላለን። ይህ ማሳሰቢያም ቸል ሳይለው ለሚዲያቸው ክብርና ህልውና ሲል እንዲቀበለው ከወዲሁ አሳስባለሁ። ደረቱ አጠገብ በክፕ ፎቶ ተለጥፎ የሚታየው የሙጃሃዲኖቹ ባንዴራ “ክሊፕ” ከ ኢሳት ጣቢያ ተላልፎ ከሆነ ጅግ አሳፋሪ ነው።
በተለይ “ካረንት አፈይርስ” ብሎ ራሱን የሚጠራው የትግራይ ሕዝብ ሲሳደቡ የሚውሉ እና የሚያድሩ ጠላቶች የተከማቹበት የፓልቶክ “ሽምቅ ተዋጊዎች” ስበስብ ከኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ጋር የኦጋዴን እና በኦሮሚያ ነፃ አውጪ አልቃኢዳዎች የሚውለበለበው የጠላት “ባንዴራ” ጋር በማጋራት ሰንደቃላማችንን ሲያቆሽሹብን በስዕለ ድምፅ ቀርፆ
{“የካረንት አፈይርስ ልጆች- - በተለይም ከኦሮሞ ብሐረስብ (በኔ አገላለጽ ማሕበረሰብ) ወንድሞቻችንና እንዲሁም የኦጋዴን ብሄረሰቦች (ማሕበረሰብ) የተውጣጡ ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት ባሁኑ ጊዜ የወያኔን አገዛዝ ሥርዓት ለመጣል የሚያስችለው የጋራ አንድነት እንደፈጠረ ነው የሚያሳየን”}
በማለት ያስተላለፈው የፓል ቶኩ ሽምቅ ተዋጊ ዘጋቢ፤- ኢሳትም እንዲያ አይነት ወራዳ ዘገባ አስተላልፎ ከሆነ ከጥንት 640 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያን ለመደምሰስ የተጠነጠነው ሴራ ከሚያድሱት ጂሃዲስቶች ጋራ ዓለማ ያነገቡ ጠላቶችን መደገፍ መሆኑን ከወዲሁ ሕዝቡ እንዲገነዘብ አሳስባለሁ። ኢነኚህ ጂሃዲስቶች ከጥንት ጀምረው ከዘርአያቆብ አምደፅዩን ወዘተ….ከዚየም በሗላ በተለያዩ የኢትዩጵያ አምበሳ ጦሮች ሲደከሩ የቆዩ ክረስትናን እና እስልምናን የሚያንኳስሱ፤ህግን ሚፃረሩ ተራ ወረበሎች ከጌዜና ከስልጣኔ ጋር የማይሄዱ ጣሊባኖች ጠላት መሆናቸውን አሁንም አሁንም ደጋግመን የፓልቶክ የሽምቅ ተዋጊ ቡድኖችና እንሱን የሚያሰክሩ በያገሩ እየዞሩ ድምፅ ማጉልያ ጨብጠው የሚየሳብዷቸው ዋሾችና ደላሎች አሁንም ደጋግምን እንመክራችሗለን። ተገንጣዩችና ጂሃዲሰቶች ኢትየጵያውያን አይደለንም ስለሚሉ የግድ “ወብድሞቻችን፤ ቅብጥርጥስ ..”የምትሉትን ቂልነት አሁኑኑ አቁሙ!ራሳችሁን አበላሽታችሁ ሌላውን አዲስ ትውልድ አታደንዝዙ አትሞዳሞዱ ማለት “አትሞዳሞዱ” ማለት ነው! ያለፈው ይበቃል! ሌላ ጉድ አታ ምጡብን! የወላጆቻችሁን ታሪክና ባሕል አታርክሱ!ጂሃዲሰቶቹ እና ኦኖጊያኖቹ አቅም ቢኖራቸው የ ኦርቶዶክስ እና ያማራ ገበሬዎች ሴትና እመጫት አርደው በደም እንደታጠቡት ሁሉ ድሮ ኢትዮጵያን በትነው እናንተውን አርደው በጨረሷችሁ ነበር፤ ነገር ግን ዕድሜ ላንዳንድ ኢትዩጵያዊያን ቆራጥ ዜጎች ዛሬም ገትረው ይዘዋቸው አቅማቸው ተመናምኖ ፈረንጅ አገር ለፈረንጅ እየሰገዱ ጌቶቻቸው ያሰፉላቸውን ጨርቅ እያውለበለቡ አገር ከመበተን ርቀው እራሳቸው ስደት ከትተው ከሩቅ እሳቱን ለማቀጣጠል “እፍ…እፍ..”ሲሉ መከራቸውን ሲያዩ እናንተ ደግሞ ጭዱንና ማገዶውን እያቀበላችሁ ማፈሪያ ትውልዶች ሆናችሁ እነሱ ጋር “እፍፍ እፍፍ..” አትበሉ!!!!
እነኚህ በስሜት ፈረስ የሚጋልቡ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የተከማቹበት “?ካረንት አፈይርስ”የተባለው የፓልቶክ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን፤ -ቀን በብርሃን ቁርኣን በእጃቸው የያዙ ሲጨልም ደግሞ ሰይፍን የሚያውለበልቡ ጂሃዲሰት ሽብርተኞችን “ውንድሞቻችን”እያላችሁ የማንቋለጫ ስም በመስጠት አልፎም “ከነሱ ጋር የጋራ አንድነት በመፍጠር ወያኔን በመጣል ሕዝባችንን ነፃ እናወጣለን” እያላችሁ ከፀረ አንድነት ከፀረ አገርና ከሽብርተኞች ጋር አንድነትን አበጅተናል በማለት ባደባባይ የሚትለፍፉ “የስሜት ፈረሶች” ዊኪ ሊኪ የተባለው “ምስጢር አውጪ”ድረገጽ እንዳለው እውነትም ተቃዋሚው “ከአብዛኛው ኢትዮጵያ ሕዝብ ልቦና የጎበጠ/ያፈነገጠ’/ያልተጣመረ”ሊለን የበቃውም እንደናንተው ያሉትን የስሜት ፈረሶች ግልቢያ እና ጥድፍያ ግምገማ በመነሳት እንደሆነ ይመስለኛል።
አንባቢ ሆይ!
እነኚህ የስሜት ፈረሶች የት እንደሚጋልቡ እና ከማን ጋር እየጋለቡ እንዳሉ ካላወቁት መለስ ዜናዊና ቡዱኑ ብታምኑም ባታምኑም ብዙ ጌዜ ሊገዛን ነው።የነኚህ ጂሃዲስቶችና ጣሊባን ከሃዲዎች ባንዴራ ያለ ማፈር ሰንደቃላማ ተብሎ- ለዘመናት የብዙዎቹ አፍሪካ መመኪያ ሆና በክብርና በተምሳሌነትዋ በየአፍሪካ አገሮች የምትውለበለብዋ በአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ያሸበረቀቺው ሰንደቃላማችን ጋር ዕኩል እያጎዳኙ ሲያቆሽሿት ያየነው እንዳይበቃ:-
“ኢትዮጵያዊነታችን ለነፃነታችን ለማስከበር በጋራ እንሰለፋለን ይህ የጋራ አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ የመጀመርያው ትልቁ ምልክት ነው ነው…. ምንም እንኳ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቆችን ቢደመጡም ያንኑን ከቁም ነገር ሳንቆጥር በጋራ ተሰልፈናል”
ሲል ዘጋቢው ያስደመጠን ዘገባ ምን ማለት ነው? ጥራዝ ነጠቅ ማለት ምን ማለት ነው? ኢትዮጵያ ትውደም! ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦጋዴን! ሲሉ ጂሃዲስቶቹ እንደ ቀላል ቃላት “ጥራዝ ነጠቅ” እያሉ ቸል ብሎ ህዝቡ ለማንንቱ ነቅቶ እንዳይከራከር ሕዝብን ማዘናጋት ምን የሚሉት ኢትዩጵያዊነት “ወንድማዊ አንድነት” የቱ ጋር እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም።
“ህዝባችን ባሁኑ ጊዜ ወያኔን አገዛዝ ለመጣል የሚያስችለው የጋራ አንድነትን እንደፈጠረ ነው የሚያሳየን” ማለት ምን ማለት ነው”? የጋራ አንድነት ከ “ኦኖግያ”፤ ከኦጋዴንያ ሙጃሃዲኖችና ጣሊባን ጂሃዲስቶች? በምን ስሌት ነው “የጋራ ግምባር” እና “አንድነት” ፈጥራችሁ እኛኑን ከወያኔ አገዛዝ ነፃ አውጥታችሁ የኢትዮጵያን አንድነት የምታስከብሩት?ወይስ የነሱ ፈረሶች ሆናችሁ ሊጋልቧችሁ ሲመጡ አለጥልጣችሁ ወገባችሁን በማዘጋጀት ጀብሃዎችና ሻዕቢያዎች በተማሪዎች ማህበር ጊዜ የተጫወቱትን ሚና ዛሬም በነ ብርሃኑ እና በነ ኦነግያ ቡድኖች እየተቀነባበረ ያለው እከከኝ ልከክህ አስቂኝ ‘/የፖለቲካ ኮሞዲ ሴራ ለመድገም ነው”? በጣም አስገራሚ ጊዜ!!!!!
አንድ አገር እንደ አገር ለመቀጠል ከሆነ ቤትህን እና አገርህን ለማፍረስ መጥቻለሁ እያለ በግልፅ ሳይደባብቅ የሚወጋህን ጠላት “ወንድምየ! ጋሽየ” ስላሉት ጠላት ካሰበው ማዘናጋት አይቻልም። ተሞክሮአችን ያንኑ አይቶታል/አልፈታል። ወይስ ኦኖጊያኖቹ እና ኦጋዴኒያኖቹ በረሃውን ሊያለማምዷችሁ ፤ኮሪደር ሊሰጧችሁ ነው ያ ሁሉ “ማንቋለጥ”እያደመጥናችሁ ያለው? ያ ከሆኑ ሕልማቸሁ ደካማ ነው፡ ለራሳቸው ኮሪደሩ ጠቧቸው “ሻ …ዓ…ቢ .. ያ” ጓዳ ውስጥ ከብርዱ ተጠልለው ተጣበው መርሃ ግባቸው አልሰራም ብሏቸው ተቸገርዋል! ወንድሞቼ ልንገራችሁ (የትግሬ ወንድመ የለንም ካላላችሁኝ -ሁሌም በየፓኢልቶካችሁ ትግሬ ትግሬ እያላችሁእንደምትለፋደዱት) ብዙ ተሞዳሟጆች ጠላትን ሲለሳለሱ ኢትዮጵያን አሁን ላለንበት አድርሰውናል። ኤርትራን ከኢትዮጵያ የሚያስገነጡሉበትን ዘዴ አጥብቀው ጣሩ፡ ምሁራን ጠላቶችን እየተለሳለሱ ነፃ አውጪዎቹ ጋር በየአዳራሹና አውሮጳ አሜሪካ “ወንድሞቻችን ናቸው”፤ “ላንደነት በጋራ ቆመናል ፤በጋራ ደርግን ነፃ ከጣልን በሗላ እንነጋገራለን”እያሉ ሲተሻሹ ገንጣዮቹ ግን ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ሴራ ሲጎነጉኑ ነበሩ። እንደናንተው ዓይነቶቹ የፈረስ ስሜቶችም ወገባቸውን ለተገንጣዩች እያለጠለጡ ጋልበው ጋልበው ጋልበው አስመራ እና አዲስ አበባ አደረሷቸው። መጨረሻው የሆነው መዘርዘር አያስፈልግም፡ የምታውቁት መሰለኝ። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ “ኦኖግያም”ሀኑ “የኦጋዴን ጣሊባን ሙጃሃዲኖች”የሚፈልጉት እና የሚመኙት “የኢትዮጵያ ሞት” ነው!! አራት ነጥብ። የጋራ አንድነት የጋራ ንገግር ፤ጋራ ትስስር፤ የጋራ ሰላማዊ ሰልፍ፤የጋራ ጥምረት…ወዘተ…የሚሉት የማታለያ ዝባዝንኬ ጌዜው ያለፈበት ተሞክሮ የከሸፈበት የስሜት ግልቢያና ማዘናጊያ መሽቀንጠር አለበት። ጠላት የሚሞዳሞደው በቂ ሃይል ሲያይልህ እንጂ ውጭ አገር ፓል ቶክ ተወሽቆ ወይንም ዳላስ ቴክሳስ እና ካናዳ አዳራሽ ባንድነት ቁጭ ብሎ ስለለፈለፉና እራት ስለበሉ “ኦነጊያም ሆኑ ሙጃሃዲኒያ” በደማቸው ያደረው የኢትዮጵያ ሞት ከመመኘት ከቶ አይቦዝኑም። የኸን ማወቅ ይኖረባችሗል። እንደገና ልድገመው፤ ኢትዩጵያን የመጥላት አባዜ ደማቸው ውስጥ ስለተሰራጨ “ለ ኢትዩጵ ያ ሞት ከመመኘት” አይቦዝኑም ። ይኸነን ማወቅ ይኖርባችል!!!!!
ከተሰው ጀግኖቻችን ምክር አንድ ነገር ልስጣችሁ። በጠላቶች “አትሞኙ፤ ጠላት ምንም ቢሆን ጠላት ነው!” ብለው ምፅዋ ላይ የቴዎድሮስ ፅዋ አንስቶ የተሰዋው ጀግና ቃል በመዘከር ልሰናበታችሁ። ያ ጀግና ጀርመን ላይ ተውለበለቡ የጠላቶቻችን ባንዴራዎች ኩፉኛ የተፋለማቸው መሆኑን በዚህ አጋጣሚ የስሜት ፈረስ ጋላቢዎች እንዲያውቁት እነሆ። “አንድ ሰው ቤት ሲሰራ የሚሰራው ቤት በርና መስኮቶች አሉት። አንድ ሰው ደግሞ ሞተ እንበል፤መቃብሩ በርና መስኮት የለውም። በርና መስኮት የሕይወት ምልክቶች ናቸው። በመሆኑም ያለ ባህር ብልፅግና ስለሌለ የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ባህር ተነጥቆ የሚኖር ሕዝብ አይደለም። ከሻዕቢያ ጀርባ ሆነው ቀይ ባህር የኢትዮጵ ያ አይደለም የሚሉ አገሮች ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፍላጎታቸው የ ኢትዮ ጵያ ሞት ነው። የባሕር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ሰው የምተለየው በትንሹ ነው። ምክንያቱም የባህር ሀብት ከማጣቷም በላይ ምርቷን ወደ ውጭ የግዴታ ወደብ ስለምትከራይ ለወደብ ክፍያ የምትከፍለው የገንዘብ ውጭ ዜጎቿን ያደኸያል። በአኳያው ጠላቶቿንና ባለወደቦቹን ብቻ ያበለፅጋል። ይህ ዕድል ለኢትዮጵያ እንዳይደርስባት ቀይ ባሕርን የኢትዮ ያ ትውልድ ይፋረድ”ሲሉ እንደጨረሱ ፊታቸውን ወደ ቀይ ባሕር አድርገው ወታደሩ እያያቸው እንደ ቴዎድሮስ ራሳቸውን ገድለው ወደ ባሕሩ ወደቁና ሞቱ። " ጀኔራል ተሰማ ይባላሉ!
ያ ጀግና ጀኔራል ከመሞቱ በፊት በህይወቱ እያለ በበርካታ አጋጣሚዎች የተፋለማቸው የጠላት ባንዴራዎች በሙሉ ጀርመን ውስጥ በዛ ሰላማዊ ሰልፍ ውስጥ ሲውለበለቡ አይተናል። ቅጥረኛውን ፀረ ኢትዩጵያ መለስ ዜናዊን ለመቃወም ሲባል ብቻ ጀኔራሉ ከተፋለማቸው የለየላቸው የኢትዮያ ጠላቶች ጋር እየተሞዳሞዱ “የጋራ አንድነት” ፈጥረን መለስ ዜናዊን ለመጣል ሰልፍ አደረግን በማለት የኢትዮጵያ ዳር ድምበር እና በከርሰ ማህጸኗ ውስጥ የተካለሉና የታቀፉ ሃብቶች ሁሉ ለማውደም እና ለመቆራረስ ከሚጣጣሩ ጠላቶች ጋራ አንድነት መግጠም ማለት ያለ መብሰልና ያለፉት ትግሎች ያለ ማጠን የተነሳ ችግር ነው። በኤሊባቡር በጂማ በሓረር በባሌ…ክርስትያኖችና አማራዎች በገጃራ አንገታቸው እየተቀላ ጀርመን ውስጥ ለገጀራ መግዢያ ከሚያቀብሉ ጋር የጋራ ግምባር ፈጠርን ማለት የወንጀል ተባባሪነትና አሳፋሪ አንድነት ስለሆነ ለወደፊቱ ከ እንዲህ ዓይነት ዘገባ ከማተላለፍ መቆጠብ ያስፈልጋል። በስሜት ፈረስ መጋለብ አቅጣጫን ያስታል። ሰላማዊ ሰልፉን ማስተባበሩ ጥሩ እያለ መለስ ዜናዊን ለመጣለ፤ኢ ሲባል መጨረሻ ላይ ከጠላቶች ጋር አንድነት ፈጠርን ስትሉ ነገረ ስራችሁ “ወጡን በሚየስጎመጅ መልክ ከሽና ስታበቃ መጨረሻ ላይ ውሃ ሞላቺው የሚባል ትግርኛ ምሳሌን አስታወሰን።በስሜት ፈረስ መጋለብ አቅጣጫን ያስታል።
ኢትዩጵያን ሰማይ አርታኢ ጌታቸው ረዳ my advice to those untrained Horses is “stop flirting with Ethiopian Mujahedeen and Talibanist terrorists” Editor www.ethiopiansemay.blogspot.com or simply Google it (Ethiopian Semay.)