Tuesday, October 28, 2008

ጉልቡጥ ፖለቲካ


ጉልቡጥ ፖለቲካ
ጌታቸዉ ረዳ
ወንድሜ አቶ በልጂግ “እኔም ትግሬ ነኝ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አንብቤዉ እጅግ ደስ አለኝ።
ቢሆንም ትናንትና አንዱን ሰሌዳ ላይ ስጎበኝ EEDN በሚባል ዝግ የዉይይት መድረክ ላይ ርዕሱን በሚመለከት ሁለት ጸሃፍት የተቹትን ቀና ትችት ያሰፈሩትን እና አንድ በክዳት ዓለም የዋኘ ግንፍል ሰዉ ያቶ በልጂግ አሊን ማሳሰቢያ አነበብኩ።የEEDN(ኑ) አንደኛዉ ተቺ ገንቢ ሆኖ ባገኘዉም መታረም ያለበት ብለዉ የተቹበት የአቶ በልጂግ አሊን “እኔም ትግሬ ነኝ” በ“እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ” የመተካት ርዕስ፡ ፈረንጆቹ hypcrit የሚሉት አተቻቸት ሆኖ አግንቸዋለሁ።
ጸሃፊዉ አቶ በልጂግ አሊ “እኔም ትግሬ ነኝ” ያሉበት ምክንያት የEEDN-(ኑ)ተቺ የገባቸዉ አልመሰለኝም። ብዙ ተቺዎች እንደሚስማሙት ብዝዎቻችን የኢትዮጵያ ቅድስና ክብር እየሸሸን ወያኔዎቹም ሲወርድ ሲዋረድ የተላለፈልንን የየአንድነት ጸጋችንን እየገፈፉት መሄዳቸዉ ለዓመታት ተተችቶበታል። የአንድነት ስሜታችን፤ ኢትዮጵያዊነታችን እየፈረሰ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃድያ ፤ትግሬ ፤አማራ ዓፋር አኝዋክ……..ሆነናል። ይሄ መሆን አላስጣልም፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነታችን እያስጣሉን እንደመጡ ግልጽ ነዉ(የጣልያኖቹ ፖለቲካን ያጤነዋል)። የማንነተቻን የአንድነታችን ክር ወደ ዉድመቱ እያቀና ያም መሆኑን ስላየን ነበር ሁላችነን በትግሉ ተሰልፈን ዛሬ እየጮህን ያለነዉ። ያለ በለዚያማ የሚያስጮኸን ምክንያትም አልነበረንም።
የአማራ ገበሬ ኦሮሞዎች በሚኖሩበት አካባቢ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዮአቸዉና መንደሮቻቸዉ በዘረኞች/ በኢትዮጵያ ናዚዎች በእሳት ጋይተዉ በሺዎቹ ተገድለዋል። ህጻናት በትምርተ ገበታቸዉ እንዳሉ የ ኦነግ ባንዲራ አወለብልበዉ በመጡ የኦነግ እና የእስልምና አክራሪዎች ተዋጊ ሠራዊቶች (ጦሩን የመሩት ስም ዝርዝራቸዉ ካሁን በፊት ተገልጿል) ያገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቃላማ አዉርደዉ በምትኩ የነሱን ሰቅለዉ ህጻናቱ ክክፍላቸዉ ዉስጥ ዘግተዉ እሳት ለቅቀዉ እንደፈጅዋቸዉ የተዘገበ ነዉ። ወንጀሉ ዛሬም እየጮኸ ፍት የፍትህ ያለህ ይላል። ኢትዮጵያዊያን ምሁራንና ጠበቃዎቹ “ከእጅ አይሻል ዶማ” ስለሆኑ የንጹሃኑ ደም ዛሬም ከኢትዮጵያ ሰማይ ሆኖ ወደ ምድሪቱ ይጮሃል። የወንጀሉ ገጽታ “ናዚዎች ባይሁዶች” ላይ “አስራኤሎች በፍልሰቲኖች” ላይ ያደረሱት ጭካኔ አይተናነስም። ዛሬም “ትግሬዉንና የአማራዉን ቆዳ ገፍፈን የዉሃ ስልቻ/መያዣ እናደርገዋለን” የሚሉ ድምጻቹ በየፓል ቶኩ ተቀድተዉ “በ ኢትዮ-ላዮን ዳት ካም” ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ ለሕዝብ ተላልፋል። ዛሬም “ኢትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም" እያለ ራሱን የሚጠራ ጸረ ትገሬዎች የተሰበሰቡበት ጋጠወጦች የሚፈለፈሉበት የፓል ቶክ መድረክ” ጸረ ትገሬ ፕሮፖጋንዳ ፤ስድበ እና ክርክር እየተካሄደ መሆኑን እየተከታተልነዉ እና ቅጁም ካሁን በፊት ይፋ ለሕዝብ እንደተላለፈ ይታወሳል።
ካሁን በፊት በበደኖ፤ በአርሲ ወዘተ… የተደረጉ የዘረኝነት የጭካኔ ክስተቶችና ባሕሪዎች ከናዚዎችና የአይሁዶች ጭካኔነት “ፓራለል” (ንጽጽር) ማድረግ አይቻልም እያሉ የጸጉር ስንጠቃ አካዳሚ ጨዋታ ትችታቸዉን ለብዙዎች ኢትዮጵያዊን “ሂፕከሪቶች” እያዩ የታወሩ እያነበቡ የማያነብቡ ዕዉራን ናቸዉና ሁኔታዉ አልታያቸዉም። ለዚህም ነበር የ“ኢኢዲኤኑ” ተቺዎች 5 ሚሊዮን አይሁዶች በናዚዎች ስለተገደሉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያን ያህል ቁጥር የለም አይሞትም እያሉ የቁጥር አንጂ የጭካነዉ የጥላቻዉ መረን “ወደዛዉ ወደ ናዚዎቹ እና ወደ ሩዋንዳዉ ቅትለት ሊያመራ እንደሚችል” የተጠቆመዉን የአቶ በልጂግ አሊ ትምርታዊ “ማስጠንቀቅያ” ማናናቅ ብቻ ሳይሆን ጭራሽኑ አንዳንዱማ ለኛ “ግልጽ” በሆነ ምክንያት ላንዳዶቻችሁ ላይገባችሁ ይችል ይሆናል፦በሚከተለዉ የመከላከሉ ሽፋን (ዲናያል)-መልዕክቱ እንደሚከተለዉ አንድ አስገራሚ ፍጡር አንዲህ ሲል በዛዉ በኢኢዲ ኤን” መድረክ ለሃጩን ሲአዝረከርክ ይሄዉ፦
“if he/she can tell me the difference between the Meles Zenawi “ Interhamway” and the “ Enem Tigre Negn” messages. To me both messengers have one thing in common which is to fabricate things and also to divide people as they have been doing for so long”. ከዚህ አጻጻፍ ማንነቱን መገመት በጣም ቀላል ነዉ። ከየትኛዉ ፓል ቶክ እና ከየትኛዉ የፖለቲካ ቁርኝት እንዳለዉ ያጣችሁት አይመስለኝም።የአቶ በልጂግ አሊን ምክር እና መስጠንቀቂያ ከመለስ ጋር ማነጻጸር ወይንም ጭራሽኑ ቢገትሪ/ጸረ ትግሬነት ዘመቻ አያደገ አልሄደም “ፈጠራ ነዉ”-የሚለን ወንድማችን “ግልቡጦሽ” የሚባል የኛ የትግሬዎች ጨዋታ እተጫወተ ይመስለኛል። ጭንቅላትህ መሬት ላይ ተክለህ አግርህ ሽቅብ ሲመለከት ዓይንህ የሚያየዉ የማየት ሃይልን የሚፈትን ጨዋታ ላይ ሆኖ ነዉ የጫዋታዉ ጽሁፍ የጻፈዉ። ወንድማችን “ከግልብጦቹ” አንዱ” ነዉና አቶ በልጂግ አሊን ያያቸዉ በዛዉ “በጉልቡጥ ዓይኑ” ነበር። ግልቡጥየዉ ከጉልብጦቹ ጋር አቆይተን፡ ወደ ሌላዉ ቀናዉ ትችት ነገር ግን “ሂፕክሪት” ወደ ሆነዉ “እኔም ትግሬ ነኝ” ወደ “አኔም ኢትዮጵያዊ ኘኝ” ቢሆን ኖሮ ሸጋ ነበር ሚሉትን ወደ ሌሎች አቃቂረኞች እንመልከት።
ካዘ በፊት ግን አንድ ነገር ልበል።ሁሌም የማከብራቸዉ ወንድሜ አቶ አበራ ሲሳይ አቶ በልጂግ አሊን በመደገፍ “ትግሬዎችን ጥላቻ እያደገ መሄድ “የፈጠራ ጽሁፍ” በማለት አቶ በልጂግ አሊን ከመለስ ዜናዊ ጋር የጨመራቸዉ ከላይ ያየነዉ “ጉልቡጥ” ጸሃፊዉን በጥሩ እንግሊዝናቸዉ አንዲህ ሲሉ ማጠናገራቸዉ ደስ አለኝ። ልጥቀስ ‘Targeting a certain group or organization for political gain is not new but a standard practice to Ethiopian politics. That is what the writer mainly concerned with. The writer supported his case with objective facts. It is up to you to disprove it. Your problem, I surmise is rather the author not the essence of the article. በጅ! አደረጉልኝ የጥንቱ የጥዋቱ ወንድሜ አቶ አበራ ሲሳይ።
አሁን ወደ ሌላኛዉ ተቺት እናምራ። “እኔ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” መሆን ነበረበት ያሉት ተቺ- ከ “እኔም ትግሬ ነኝ” የሚለየዉ ትግሬዎች ላልሆኑ ኢትዮጵአዊያን የተላለፈዉን መልክት የተምታታባቸዉ መሰለኝ። እነዲህ ይላሉ “The author has forgotten the development of seventeen years of self isolations of ‘ Tigrewoch’ in the Diaspora. Let us face the truth and place the blames where they belong. The ‘ Tigrewoch’ left the Ethiopian Halls in every city around the world and established their own ‘ Tigrewoch’ halls and effectively separated themselves from the rest of the Ethiopians. They minded their own businesses and their existences separate from the others. They developed their own issues and concerns, and initiated new development different from the rest of the Ethiopians. Their ideas about democracy and development in Ethiopia became different from the rest of Ethiopians. They participated in no human rights issues and other national issues along with the Ethiopians. They invented different perspectives about democracy and how government should be formed democratically in Ethiopia different from the rest of the Ethiopians. The blame must not be against those innocent ‘ Tigrewoch’ but those few leaders who led the good Ethiopians in that direction. Those who orchestrate the rejection of ‘ Tigrewoch’ from the rest of their fellow Ethiopians must be condemned and crashed. They are no less destructive than TPLF. The innocent ‘ Tigrewoch’ must not be blamed, but they must be guided by the principles and philosophy that made Ethiopians one people and one indivisible nation. Ethiopians individually or in groups must think of uniting the Ethiopians where ever they are and reestablish its land and inhabitants the way they have been for centuries. The author should begin to fight by joining the forces that would bring down to the ground the notion and the system of ‘ KILIL’ . The author should also teach and show his fellow country people that self-isolation is destructive and must advocate and encourage people to rejoin the halls of Ethiopians every where in every city around the world. He should rewrite ‘ enem Tigre negn’ to read ‘ enem Ethiopiawi negn’ .“እኔም ኢትዮጵያ ነኝ” ማለት የነበረባቸዉ ራሳቸዉን ላገለሉ “ትግሬዎች” መሆን ነበረበት ይላሉ ከተቺዉ እንደተረዳሁት ።
ሁለቱም አባባል በጣም ይለያሉ። አቶ በልጂግ አሊን ያሳሰባቸዉ የኔን ኢትዮጵያዊነት መካድ አለመካድ ሳይሆን ወይንም ራሳቸዉን ያገለሉ ኢትዮጵአዊን/ት ትግሬዎች ወደ ኢትዮጵያዊነት የመምጣቱ ጉዳይ ሳይሆን እየተቹት ያሉ፡ የመልዕክታቸዉ ዋና “ስጋት“በ ኢትዮጵያዊነት ስም”-ባንዳንድ ጋጠወጥ የሞሉበት ፓል-ቶክ መድረኮች የሚፎክሩት ፎካሪዎች- ከትግራይ ሕዝብ ይልቅ ልዩ የላቀ ኢትዮጵያነት ያላቸዉ የመሰላቸዉ ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን/ት ነን ባዮች ሌሎች (ከትግሬዎች ዉጭ የሆኑ) ኢትዮጵአዊያን “የትግራይ ሕዝብን”-እደግመዋለሁ “የትግራይ ሕዝብን”ለመጨፍጨፍ፤ለማሳለቅ፤ለማሸነፍ፤ለማንበርከክ፤ ለማሳደድ፤ “ንምጽናት” (ትግርኛ ትርጉሙ ethnic cleansing) ዘርን ለማጥፋት ግድያ ለመፈጸም፤ቤቶች እና ንበረቶቻቸዉ ለማቃጠል፤ ከሚኖሩበት አካባቢዎች ወደ ትግራይ አንዲጋዙ/እንዲባረሩ የቀሰቀሱ በየፓል ቶኩ ካሁን በፊት ተደምጧል እና (ከሞላ ጎደል አንዳንድ ክስተቶች በግበርም ተደርጓል እና 1991-1992 እና በ1997) ዛሬም “ኢትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም እና ባንዳንድ ፓል-ቶኮችም - ጋጠ ወጦች የሕዝብን ክብር ቅዱስና የማያዉቁ ይህንን የዘረኝነት የተላበሰ ዛቻ እና ዘለፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እያሰሙ እያደመጥን ስለሆነ፤ ጋጠዎጦቹ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚደረግ ዛቻ እና ዘረኛ ዘለፋ ሁላችንም “ጎረቤትህ ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ” ኑዉና እኛም ኢትዮጵያዊያን ስለሆንን ትግሬዎችም (ምንም የማያዉቀዉን የትግራይ ገበሬ አዛዉንት፤ሴቶች ህጻናት ..) ኢትዮጵያዊን የደም አጥንታችን ቁራጮች ስለሆኑ “ጋጠዎጦቹ ልቅ ተለቅቀዉ በየፓልቶኩ ዘረኝነት እንዲረጩ ሲለቀቁ ዛቻዉ እኛኑም ጭምር ስለሚነካ “አኔም ትግሬ ነኝ” ብለን ኩሩዉ የትግራይ የኢትዮጵያ የሃይማኖታችን የፊደላችን ትምርት ፈልሳፊና መሰረት የሆነዉ የትግራይ ሕዝብ ሲነካ በአንድነት ቆመን መከላከል ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለብን! ነበር የአቶ በልጂግ አሊ የማያሻማ መልዕክት ያስተላለፉት።ሆኖም አብዛኛዎቹ የአገራችን ሙሁራን “በሂፕክርት ሱስ ናላቸዉ አናዉዞታልና” ይህንን የማያሻማ መልከትና ማስጠንቀቅያ ትግሬዎቹስ ለምን “እኔም ኢትዮጵአዊ ነኝ’-ለምን አይሉም ተብሎ መቀየር ነበረበት ወደ ሚለዉ “ዉዥምብርነት”-መግባቱ በበኩሌ አልወደድኩትም።
የመልክቱ መነጽር ለማየት የታለመዉ ኢላማ ያወላግደዋልና አልወደድኩትም። መልዕክቱ ለትግዎች ሳይሆን አፋቸዉን ዘግተዉ በቸልተኝነት ለሚያዳምጡ ወይንም የፓል-ቶክ ሰሌዳዎች/መድረኮች ለ“ ኢትዮጵያ “ስኪን-ሄዶች” እና “ኩሉክስ- ክላኖች” ደቀመዛሙርት ያለ ሴነሰር-ሺፕ ያለ ቁጥጥር በስመ “ዲሞክራሲ” ለሚለቁዋቸዉና ለተቀሩት አፋቻዉ ዘግተዉ ጀሮአቸዉ ከፍተዉ ለሚያዳምጡ ኢትዮጵአዊያን “ደጎች”ን ነዉ።ኢትዮጵያ ከቶዉንም እንደሩዋንዳ አንደ ጀርመን አትሆንም የሚሉን “ሂፒክሪቶች” የማሰተላልፍላቸዉ መልክት ቢኖር የ1991-1992 የዘር ማጥፋት ታሪክ ዕሪታዉ፤ ቶክሱ እሳቱ ሽብሩ በምድሪቱ የወረዱ እምባዎች የፈሰሱ ደሞች “ብልታቸዉ በሰላ ተቆርጦ ተገድለዉ በሞቱት ዓይነስዉራን በሬሳቸዉ አፍ ላይ ተጎርሶ እንዲታይ የተደረጉት “የትኢትዮጵያዊያን ናዚዎች” ስራ በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር የተመዘገበ ነዉ። ያዉም ትናንትና!ማህደሮቹን ገላብጡ። የስሜት እሩጫ የትም አላደረሰንም። ታሪክን መርምሩ። እያልኩ የትግርኛዉ ምሳሌ “ትማሊ ትማሊ ከይወረደ ጻሕሊ” (የወጡ ሽታ ዛሬም እየሸተተን፤ ያዉም የትናቱ፤ ገና ከምጣዱ ሳይወርድ)ልጥቀስላችሁ።
የዋሃኑ ያገሬ ሰዎች፤ አስከመቸዉ “ነገር”-እየረሳችሁ ልብ ሳትገዙ ትኖሩ ይሆን? መጪዉን አስተዉሉ። ቁስላችን ዘወትር ለማስፋት የሚከጅሉ “ጋጠወጦችን”-በብርቱ ተከታተሉ። እያደጉ እየተበራከቱ አዳዲስ ወጣት “ናዚ ኢትዮጵያዊያን/ት” ወደ ፖለቲካዉ መድረክ ብቅ እያሉ ዛሬም እንዳሉ ካሁኑኑ እየመከርን ነዉ። የናዚ አስተሳሰብ መጸሃፍ ጽፈዉ ለሕትመት እና ለንባብ ያበቁ “ኢትዮያዊያን ናዚዎች” በቅስቀሳቸዉ “ዛሬም የሚኮሩበት”-ተቃዋሚ የፓሎቲካ ድርጅቶችን እየመሩ ናቸዉ።በነሱ ዱካ የሚራመዱ ተናዳፊ ንቦቻቸዉ ደግሞ በየፓልቶኩ የምተዳምጡት አፋቸዉ ምን እያወራ እንደሆነ መታዘብ ነዉ። ይሄን ማን ይረሳዋል? ዴቪድ ድዩኮች አሉን። “ድዩክ’ ለፕረዚዳንትነት ምርጫ ሲቀርብ የክሉክስ ክላን እምነቴን ጥየዋለሁ እያለ በመንገድ ላይ ትንንሽ ህጻናት ተማሪዎች እያስቆመ ግምባራቸዉን እያሻሸ ሲያነጋግር በዘመቻዉ ፕሮፖጋንዳ ማስታወቂያ ቀርቦ እንደነበረ ታስታዉሳላችሁ።
ዛሬም የኛዎቹ ናዚዎች ትልልቁን መድረክ ይዘዋል።የሻዕቢያ እና የወያኔ ትግራይ የጥላቻ የጎሳ ፖለቲካ እኛኑን በምንናዉ ዓይነት የጦርነት/የሞኞች የመተላለቅ እልቂት አስገብቶ ከ70,000 ከሰባ ሺህ በላይ ሕይወት እንደበላ መጻህፈትና ጋዜጦች ስለ ህዝቦች ምን ይሳደቡ እንደነበር፤ ድረ ገጾች በጦሩነቱ ጊዜ ምን ይሉ እነደነበር፤ የኢሳያስ አይሮፕላን መቀሌ ላይ በህጻናት ላይ የፈጸመዉ የናዚ የፋሺስቶች ስራ ከመቸዉ ተረሳ እና ነዉ በኛም አገር አይደረግም ተብሎ ክርክር ዉስጥ የተገባዉ?-ከመቼዉ ረሳችሁት?-ከናዚዎች ባሕሪ የተሻልነዉን የዛሬዉ ምልክታችን በምንኛችን ነዉ? የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሕዝበብ ጠላት ነዉ እያሉ የሞሶሎኒ ቅስቀሳ የሚያካሂዱ የሚጽፉ የሚናገሩ የዘረኞች ድርጅት መሪዎች በሰላም አየር ጥላቻን ሲነዙ በምንሰማበት ምድር? አይፈጸምም! ብሎ ምክርን ማጥላላት “ደግነት” ይመስለኛል።
በመጨረሻም በዛዉ በኢትየጵያን ካረንት አፌይርስ በተባለዉ የጋጠወጦች እና ጸረ ትግሬ ፕሮፖጋንዳ በሚለቀቅበት ልቅ መድረክ ላይ ታዋቂዉ ጋዜጠኛዉና የጋዜጠኞች ማህበር ተጠሪ “አቶ ክፍሌ ሙላት” ለቃለ መጠይቅ ይቀርባሉ ተብሎ እየተወራ ስላላ አቶ ክፍሌ ሙላት በዚህ አጋጣሚ የጋጠወጦችንና የጸረ ትግሬ መድረኮችን የመኮነን ሃለፊነት አለባቸዉና መድረኩን ላለማክበር “ቦይኮት” እንዲያደርጉ ጥሪየን አቀርባለሁ። አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ www.ethiopiansemay.blogspot.com

Saturday, October 25, 2008

ብርሃነ መስቀልን ዝለፉት ዋለልኝ ግን አትዝለፉ ብሎ



ብርሃነ መስቀልን ዝለፉት ዋለልኝ ግን አትዝለፉ
ብሎየፈቀደላችሁ ፍርድ ቤት ብታመለክቱን!? ጌታቸዉ ረዳ ብዙ ጊዜ የታዘብኩትና ያስገረሙኝ ነገሮች ሁሉም እንኳ ባይሆኑ አንዳንድ የተማሩ፤በትግል የተፈተኑ የሚባሉት ፊዉዳሎችን ታግለናል የሚሉን ሰዎች፡ከታገሉዋቸዉ መሳፍንትና ጉልተኞች ባልተሻለ ወገንተኝነት ሲያንጸባርቁ ስመለከት እስከ ዕንጥላቸዉ የሞሉትን ዕዉቀት እየፈሰሰ ሊናገሩት የፈለጉትን ቀና ነገር እያኮላተፋቸዉም ይሁን ወይንም ቋንቁኛዉ ባልገባኝ ነገር መስተንክር እየሆኑ ሲመጡብኝ “አንታ ዝዘበን እንታይ ዘበኑ?” (አናንተየ፤ይሄ ዘመን ምን ከሚባለዉ ዘመን ደረስነዉ?) በል ያሰኘኛል።
ባለፈዉ ወር ፍካሬ የተባለዉ የኢሕአፓ መጽሄት- ዋለልኝ መኮንን- ን አስመልክቶ በእኔ የሚዘጋጅ “የኢትዮጵያን ሰማይ” የሕዋ ሰሌዳን ያለ ምክንያት ጣራዉን በከዘራዉ ወደ ላይ ቀስሮ ለመኮርኮር ቃጥቶት “በማዕለሽ አለፍኩት።ሳልፈዉ ግን፤ አንድ ነገር ልበል፡ ኢትየጵያ ሰማይ የግለሰዎች ወይንም ድርጅቶች “ቀጭን ትዛዝ” ተቀባይ ወይንም አክባሪ አንዳልሆነ ይታወቅ።
ቀጥሎ ሰሞኑ ደግሞ ዋለልኝን አትንኩ! ያትዉልድ እና ዋለልኝን ለቀቅ! የሚል ጽሁፍ ደግሞ ተለጥፏል። እኔ የገርመኝ ያ ትዉልድ የሚባለዉ ማንን ያካተተ ነበር? በያትዉልድ ጊዜ እነሱ ብቻ ተገረፉ?ቆሰሉ?ሞቱ፤ታረዙ?ተጋዙ? ሌሎቻችን ግን አልታሰርንም?አልተደበደብንም? ስለ ሕዝብ በመድረክ እና በመንግሥት ፊት ለፊት አለተጋፈጥንም?፤ አልታረዝንም?-አልተታኮስንም?-አልተጋዝንም?፤አልተሰቃየንም?፤አልተሰደብንም?-አሳረችን አላየንም-ቤተሰቦባችን አልተበተኑብንም? አልተገደሉብንም? ተማሪው እና የገበሬዉ ብሎም ሰራተኛዉ አይዞህ አላልንም?ወታደሩን በቁርጥ ቀን ከጎኑ አልቆምንም? ስለሱ ኣልጮህንም? በዛ ሁሉ ትዕይንት እንዳልነበርን ተመስሎ የሚቀርብ ትዕቢት በጣም ይደንቀኛል።
እኛም እኮ የዛ የ ያትዉልድ ዘመን ልጆች ነን። የክብር መዳልያ ሽልማት ቢኖር እኮ ሽልማቱ ለነሱ ብቻ አድርገዉ እኛኑን እከክ እንደ ፈጃት ላም ቆጥረዉ ከማዕረጉ ያስቀሩን ነበር ማለት ነዉ። ደግነቱ ሽልማት እና ዕደገት ያለመኖሩ ገላገለን። ለዚህ ለዚህ እማ ወያኔ ከዚህ የተለየ ምን አደረገ? ወያኔ እኮ አትንኵኝ በኔ ዘንድ እሸት እሸቱን እንጂ የተከልኩትን መርዘማ እሾሄን አታርሙ፤ አታንሱት፤በኔ ዘንድ ብጹዕነት እንጂ አመኬላነት አላስተማርኩም ስለሚለን ነዉ። ታድያ በዚህ መልክ ከተኬደ የፖለቲካ ምጥቀት እንዴት ሊከሰት ይችላል? ዉይይት፤በታሪክ መከራከር፡ እርማት፤ ነቀፌታ፤ በ ያትዉልድ መጥፎ ጎኑ መተቸት ለምን አያስፈልግም? ። እኔ የገርመኝ ያ ትዉልድ የሚባለዉ ማንን ያካተተ ነበር?
ዋለልኝን ስለነቀፍን የተሰጠን በጣም ያስገረመኝ ትችት ልጥቀስ፦“የለየላቸዉ አድሃሪዎች እየመሩና የቀይ ሽብር አራማጆች አጀብ ሆነዉ ዘመነ ትምክህት ናፋቂዎች ሁሉ ድነገት አዋጅና የክተት ትዛዝ የመጣባቸዉ ይመስል ለለዉጥ በታገለዉ ትዉልድ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተዋል።በዚህ መሰረት ሕይወቱ ለሃገሩ እና ላላማዉ ሰጥቶ ያለፈዉን ዋለልኝን በተለይ መዝለፍ አብዝተዋል።በ ዋለልኝ ሽፋን የአንድ ጊዜዉ የተማሪዎች እና ተራማጆች እንቅስቃሴ በአድሃሪዎች እየተወነጀለ እና እየተጠቃ ነዉ።” …..ይል እና ዋለልኝንም ሆነ ተራማጅ የሚባል ክፍል የነቀፈ ሁሉ “አድሃሪ፤የቀይ፡ሽብር ወንጀለኞች፤ የአፄዉ ዘመን የስልጣን ተካፋዮች፤ትግሉ ሲካሄድ በቦታዉ ያልነበሩ ወ ይንም አድሃሪ ሚና የነበራቸዉ…ወዘተ ይለናል። ወቸዉ ጉድ!
በመሰረቱ ተቺዉ እና ሌሎቹ በብርሃነ መስቀል ረዳ ሌት ተቀን ሲዘምቱ አንድም ሰዉ ከእኔ ጀምሮ ትንፍሽ አላልንም። ለምን? ምክንያቱም ብርሃነ መስቀልን የምንከላከልለት ነጥብ ታጥቶ ተዛላፊዎቹ ድንግሎች ስለሆኑብን ሆነዉ ሳይሆን ወቃሾቹ የመዉቀስ መብታቸዉ ነዉና ተለቀቁ። (ልቅ ሄዱ ልበለዉ!?)። ብርሃነ መስቀልን የሚያሞግሱት ጽሁፎች እና ስራዎች (ግንፍል በህሬነቱን የሚያጎሉለትንም በተጻራሪ “ካሪዝማቲክ-በህሪ እንደነበረዉ የመሰከሩለት ጸሃፍት)” ባህሪዉ እና መስዋእትነቱን በተጻራሪ ማቅረብ ይቻል ነበር። ሆኖም የትግል ጓዶቹ ነበሩና የመዝለፍ መብታቸዉ አስከ ዛሬ ተጠብቆ ነበር። ብርሃነ መስቀልን ሲዘልፉ (አስኪ ሰለቸን) በቃችሁ ሳይባሉ ዛሬ ደርሰዉ ዋለልኝን በታሪክ ማሕደር በአምዳችሁ ነካካችሁብን ብለዉ ዋለልኝን የተቸ ሁሉ “ነብሰ ገዳዮች፤አፄዎች፤ሃሁ ያልቆጠሩ፤በቦታዉ ያልነበሩ፤ ኢሕአፓን ሊያጠቁ የተነሱ………..ወዘተ” ሲሉን እንዴ? ወዴት ወዴት ነዉ ነገሩ!
ዋለልኝ በሕይወት የለምና፤ራሱን መከላከል በማይችልበት ጊዜ ስለሱ ስራዎች ማንሳት ነዉር ነዉ ሲሉ ተከራክረዉናል።አንዳንዱም በአካል መጥተዉ ይህንኑ ቃል ለኔ ደግመዉልኛል።እኔ ደግሞ የምለዉ- አዋጅ የመጣ የክተት ትዛዝ የተላለፈ ይመስል በብረሃነ መስቀል ላይ የዘለፉ ዘመቻ አልቦ ዕረፍት አለ አዋጅ ሲዘለፍ፤ “በሕይወት ስላለ ራሱን መከላከል የሚችል መስላቸዉ ኖሯል ልበል? ይሄ ወገንተኝነት ነዉ ወይስ ምንድነዉ? ብርሃነ መስቀልን የመዝለፍ ተገቢነቱ ዋለልኝን ግን አትንኩት ብሎ የፈቀደላችሁ ፍርድ ቤት የትኛዉ ነዉ? ብታመለክቱን!?
ዘለፋዉና ወቀሳዉ በዋለልኝ ሲደርስ ሕጋዊነት የሚያጣ በብርሃነ መስቀል ላይ ግን ሕጋዊነት ሚላበስበት መበት ማን ነዉ የሰጣችሁ? ይሄማ የትገርኛዉ ምሳሌ “ሳዕሪ አጉዶ ብማይ ዓብያስ ማይ ከይአቱ ትካለኸል” (የጎጆ ሳር በዉሃ አድጋ ዉሃ እንዳይገባ ትከላከላለች” እንደሚባለዉ ነገር ብርሃነ መስቀል ኮትኩቶ ባሳደገዉ ኢሕአፓ ሲዘለፍ፤ ሳሯም ዉሃን ጠጥታ ዉሃን አለስገባም የምትለዉ ዓይነቱ እኮ ሆነ ነገሩ። እኛ ብርሃነም ይሁን ዋለልኝን በታሪክ ማሕደራቸዉ እኩል ፍርድ ሚዛን እንጂ በወገንተኝነት ወይንም በግል ጸብ ወይንም ዝምድና፤ ትዉዉቅ፤ ደም አጥንት፤አዉራጃ፤ ጎጥ ፖለቲካ፤ ሐረግ ዉስብስብ ዉስጥ ገብተን አይደለም የሚዛን መነጽራችን የሚመዝናቸዉ። ሁሉም በሚመሰላቸዉ ታግለዋል፤፡ በታገሉበት ማሕደር ደግሞ ዘለፋም፤ስድብም፤ ዉግዘትም ምሬትም ወቀሳም እንደየስራቸዉ ይከተላቸዋል። እነሱ ሞተዋል፤ ታሪካቸዉ አልሞተም።
ስለዚህም ታሪካቸዉ አስካለ ድረስ አስካነሳነዉ እና አስካስታወስናቸዉ ድረስ በመጥፎም በደጉም ይነሳሉ።በእኛዉ ትዉልድ ካልተነሱ “ሞተዋል የምንልበት ጊዜ” ሳናነሳቸዉ ከቀሩ በሗለ ነዉ የሚሞቱት። የቀብራቸዉ ግብአተ መሬት የመጨረሻዋ ምስማር ተመታች ማለት ነዉ። ያ ሲሆን አዲስዩ ትዉልድም ማን መሆናቸዉ ሳያዉቅ ይቀርና; የ ያኔ ትዉልድ ታሪክ ታሪክም አብሮ ያኔ ያከትማል።ያ እንዳይሆን በእኛም በእናንተም የምናቀዉ እና ያነበብናቸዉ ታሪኮቻቸዉ እያነሳን አለፍ አለፍ እያልን መመራመሩ ማዉሳቱ ተገቢ ነዉ። ያ ስላልን “ሳንገድል አንበሳ ገድለናል እና ጎፈሬያችነን እዩልን አላልንም። ገዳዮች፤ታዛዦች..ሃሁ ቆጣሪዎች..ወዘተ” ሆነንም አይደለም።የስደቡ ናዳ ሳያስፈልገን በላያችን ላይ ማንዣበቡ ባልንባቸዉ ትችቶች የተሰደብነዉን ስድብ የሚያስሰድበን አይመስለኝም።
ዋለልኝ የኦነግ የወያኔ የተገንጣዮች አቀንቃኝ መምህራቸዉ ነዉ የሚለዉ አቋማችን አሁንም ያዉ ነዉ።ተሳስቶ አሳስቶናል ነዉ አቋማችን። አሁንም በሱ ብዕርና ድጋም የሚደግሙ ወያኔዎችና ተገንጣዮች መከራከራችን አልቀረም።ለመሆኑ ዋለልኝ ማን ነበር? በሚገባ ወንድማችን አቶ ዜግ ፋንታ ገልጾታልና ያንኑ አልደግምም።ይህ አቀራረብ የዋለልኝን ማንነት ትዉልድ ዕደገት ወዘተ..አይደልም። ባጠቃላይ ግን ዋለልኝ እና በዋለልኝ ዙርያ የነበሩ ፖለቲካ አማካሪዎቹን ይፈትሻል። ጀብሃ በ1958 ተመሰረተ ወይንስ በ1960 ተመሰረተ? የሚል ጥያቄዎች እንካ ስላንትያ የትምርት ጨዋታ ዉስጥ አልገባምና በ1958 ተመሰረተ በ1960 ተመሰረተ ዋለልኝ እና በዋለልኝ ዙርያ የነበሩ ሰዎች ከመገምገም ሊያግደን አይችልም።

በዋለልኝ ዙርያ የነበሩ ኤርትራዊያን ጃንደረባዎቹ አብዛኛዎቹ “ህዝባዊ ሓይልታት (ቡድን 2) ተብሎ የሚታወቀዉ የኢሳያስ ተከታዮችና ተዋጊዎች ነበሩ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ስንት ጊዜ የአይሮፕላን ጠለፋ ሙከራ እንደተደረገ እና አብዛናዎቹ በጠለፋዉ ዉስጥ የተሳታፉት እነማን እንደነበሩ ታሪኩን ሚያዉቁት ሊግልጹልን የፓልቶክ አዘጋጆች አፈላልገዉ ቢጋብዙልን እና እንድንማርበት ቢደርጉ ለመጠቆም አወዳለሁ። በተረፈ በእኔ በኩል ያዘጋጀሁላችሁን አነስተኛ ማሕደር አቀርባለሁ ከዛ ዋለልኝ ማነዉ ማን ነበር ሚለዉ የናንተ ግምገማ አስገቡና በዛ እንቀጥል።

ከዚያ በፊት ግን “ተራማጅ” የሚባል ቃል እያስቸገረኝ ስለመጣ እሱን ልነካካ። ተራማጅ ምን ማለት ነዉ? እኔ አልመልሰዉም። ተራማጆቹ ይንገሩንና እንከራከር። የአገሪቷ ሕዝቦች እንዲገነጣጠሉ ሌሊናዊ ቅስቀሳ/ኮሚኒስታዊ ቅስቀሳ ማሰራጨት ማስተማር በአዋጅ ማጽደቅ ወንጀል እንጂ አፍራሽ አንጂ ተራማጅ አይደልም እላለሁ። ያ ትዉልድ የሚባለዉ ወይንም የምንባለዉ የሰራናቸዉ ስራዎች ሁሉ ድንግል/ታቦት ሆኖ አይነካካ ማለት ተራማጅነት አይመስለኝም? ያ ትዉልድ የሚባለዉስ ስንቱ ነዉ ንጹህ ተራማጅ (የተራማጅ ትርጉሙ ከተራማጆቹ ብንጠብቅም)? መሬቱ ላይ የፈሰሰ ደም ሁሉ ደሙ ስለፈሰሰ ንጹህ ነዉ? ተራማጅ ነዉ? በዛ ያ ትዉልድ የተሰለፈ ሁሉ ንፁህ ነዉ? ተራማጅ ነዉ?
ላስፋዉ መሰለኝ። ጀኔራል መንግሥቱ ንዋይ ተራማጅ ነበሩ እየተባለ ይነገራል። ተጽፏል።

አንዳንዶቻችን ንጉሡን ደግ ስራ ስናነሳ ጀኔራል መንግሥቱን የገደሉ እገሌን እንዲህ ያደረጉ ይላሉ። ማለታቸዉ መብታቸዉ ነዉ። ያልገባኝ ነገር ግን “ጀነራል መንግሥቱ ንዋይ ንጉሡን ለመገልበጥ ሲሉ በርካታ ሚኒስትሮች እና መኳንንት እና ልዑላን በአንድ ቤት በአንድ ጣራ በአንድ ወለል ዉስጥ አስገብተዉ ረሽነዋል”” ይህ ወንጀል አንጂ፤ ይህ ነብሰ መግደል እንጂ ይህ ሰብአዊ መብት መግፈፍ አንጂ ፤ይህ አምባገነንነት እና ደመ ፍሉነት አንጂ፤ የተራማጅ ባህሪ ሊሆን በፍጹም አይችልም (መራመድ በጥሩ መልኩ ብንተረጉመዉ ማለቴ ነዉ)። መራመድ -ዕድገት ነዉ፤ግስጋሴ ነዉ፤ ወደ ፊት መምጠቅ ማለት ነዉ። ታድያ 15 ስቱን ባለስልታኖች ሲረሽኑ “ተያዝ-አልያዝም” በቶክስ ልዉዉጥ ሳይሆን የገደሉዋቸዉ ትዕዛዝ አስተላልፈዉ ራሳቸዉን በግድያዉ ተሳትፊ ሆነዉ በተካፈሉበት “የጅምላ ግድያ” በምን መልኩ መገስገስን አድገትን ተራማጅነትን ያሳያል? አነዚያ ጀኔራሎች ኮሎኔሎች እንያ ተራማጅ የተባለላቸዉ መፈንቅለ መንግሥት አካሃጆቹና ተካፋዮቹ የ ያ ትዉልዶች አከላት አይደሉምን?

ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም 57 (?) ሚኒስትሮች፤መኳንንት እና ልዑላን ራሶች ወዘተ… በአንድ ክፍል በአንድ ወለል ግድግዳ ላይ አስጠግተዉ ፈጁዋቸዉ። የኮለኔሉ እና የጀኔራሉ ስራ ወታደራዊ ኩዴታ/የመንግስት ግልበጣ ነዉ። በሰዉ ሕይወት ላይ የጅምላ ግድያ ፈጽመዋል። ኮለኔሉ እና ጀነራሉ የሚለያቸዉ ኮሎኔሉ በዕድሜ ኖረዉ ብዙ ሕይወት እና አገር አጠፉ ፡ጀኔራሉ ግን ዕድሜ ሳያገኙ በጥቂት ደቂቃዎች ጊዜ 15 (በርካታ) ሕይወት ቀጭተዉ አሳቸዉም ዕደሜ ሳያገኙ ለሞት ስለተዳረጉ ብቻ ነዉ፡፤
ታድያ ይሄ ተራማጅነት ነዉ? ሌላዉን “የብሄር ብረሰብ መብት አስከ መገንጠል” የሚለዉ እና እራሱ “ብሄር” የሚለዉ ባገራችን የማይታወቀዉን በዛሬ ትርጉሙ አፍራሽ እና መዘዘኛ መሆኑን እንጂ ዲሞክራሲያዊነት ወይንም ተራማጅነት እንደሌለዉ በክፍል ሁለት በሌላ አርእሰት ስለማቀርበዉ እርሱን ትተን፡አሁን ወደ ተራማጁ ወደ ዋለልኝና በዙርያዉ ከነበሩ ኤርትራዊያን ጃንደረቦቹ ጋር እናምራ።ዋለልኝ በወንድማችን በአቶ ዜግ ፋንታ በሰፊዉ እንደተብራራዉ የወሎ ሰዉ መሆኑን አንብባችሗል።ዋለልኝ ተራማጅ ከሚባሉት የ ያኔዉ ተማሪዎች አንዱ ነበር። ንቁ ተማሪ ይሁን እንጂ እያጥላሉ ከሚሰድቡት ካሪዘማቲኩ ብርሃነ መስቀል ረዳ መድረክ ይዞ ለመናገር ሲሞክር እንደ ዓእዋፍ ሰማይ ወደ አሱ ሲበርሩ የነበሩ ታመሪዎችን አያክልም። ያ ተፈጥሮ የለገሰዉ ብርታቱ ተናጋሪነቱ እና የተማሪ ቤት ንቁነቱ ማንም ሊነጥቀዉ እንደማይችል፤ ዛሮም ያንኑ ተፈጥሮዉ የነጠቀዉ ተነጋሪና ንቁ የለም የሚሉ ጸሃፍት አሉ። አኔም አስማመለሁ ። ምናልባት የትግራዩ (በወያኔ እና በደርግ ካድሬዎች መሃል ተገደለ የሚባል -ለኔ ግን ዓባይ ፀሃየ እንደነገረኝ ወያኔ እርምጃዉን እንደወሰደችበት ነዉ የነገረኝ) ገዳዩ ያልታወቀ “አብርሃ ፓትሪስ” (አብርሃ በርሀ) ካልሆነ ሌላ ብርሃነ መስቀልን የሚያስከነዳ ፍጡር ያለ አይመስለኝም (መስክር ብባል ግን የንግግሩ ፍሬ ነገር ትተህ በፈጣን ተነጋሪነቱ ተምቤን እና መቀሌ ያደገዉ የዓድዋዉ ተወለጅ “አብርሃ ፓትሪስ” (“ፓትሪስ መቐለ” ወላጅ አባቱ እንደሚጠሩት)ከብርሃነ መስቀል በእጅጉ ማራኪ ድምጽና እጥፍ መስህብ እንደነበረዉ አዉቃለሁ። በነገራችን ላይ “ተሐህት”ን “የመንደር አይጥ” ብሎ የሰየማት አብርሀ ፓትሪስ ነበር። ከዚያ በሗላ ገደሉት። ዋለልኝ እንደ ብርሃነ መስቀል አንደ መለስ (በደርግ የተረሸነዉ መለስ) ከኤርትራ ተማሪዎች ዙርያ መልከስከሱን አልታጣዉም።

ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በጣም የዋሃን (በራቸዉ መዝጋት የማያዉቁ) ስለሆኑ፤ በተንኮል የተካኑ አብዛኛዎቹ የኤርትራ ተማሪዎች ይሄነን ስለሚያዉቁ የግንጠላዉ ጉንጎናቸዉ ለማካሄድ እንዲያመቻቸዉ (በወቅቱ ግቢዉ አስከ 600 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ም ጨምሮ ያስተምር ነበር) አራት አልጋ በ አንድ ክፍል ካለ አራቱንም ክፍል በታቻለ መጠን ሁሉም ኤርትራዊያኖች በአንድ አንዲሆኑ አንዱን የዋህ ኢትዮጵያዊ እማሃላቸዉ ከነበረ፤ መኝታ ክፍሉን አንዲለዉጡት ይለምኑትና ሁሉም ተሰባስበዉ ከበረሃ የሚላከዉን ዜና “ጥሕሻ” (bully, bulldozer, trace passer-ናደዉ) በተባለዉ ቡድንና መጽሄት የግንጠላ ሴራቸዉ ያራምዱ ነበር። ልብ ልትሉት ምፈልገዉ ነገር ዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ ሲማሩ የነበሩ ኤርትራዊያን ተማሪዎች ግቢዉን ጥለዉ በ1965 በፈረንጆች አቆጣጠር ወደ ሜዳ /በረሃ በመሄድ የግንጠላ ዉግያ ያካሂዱ ስለነበር የበረሃ ግንኘነታቸዉ ከዛ ጊዜ ጀምሮ አንደነበር የራሳቸዉ መሕደር ይመሰክራል።
እስከ ‘ዚህ ድረስ መሰረቱ ሥር እንደነበረዉ ካወቃችሁ አሁን እነ ዋለልኝ እና መሰሎቻቸዉ “በተራማጅነት”-የአገራቸዉን ህልዉና ከግንጠላ ሃይሎች ጋር በማቆራኘት “የግንኙነቱ ዘር በመዝራት”-ለፕሮፖጋንዳቸዉ መጠቀምያ እንዳደረጉዋቸዉ አንመለከታልን።ዋለልኝ የገዛ አገሩን አምርሮ ይቃወማት ነበር።

እርሱ አማራ ሆኖ ኢትዮጵያን የአመሮች ነች! ኢትዮጵያዊ ለመሆን መታወቂያዉ ያማራ ስም መያዝ ነዉ፤ካልሆነ ዜግነትህ አይከበርም፤ አይታወቅልህም እያለ የሚነዛዉ ጸረ-ኢትዮጵያ ዉዥምብር ፕሮፖጋንዳዉና ያማራ ጥላቻዉ ከኤርትራዊያን ተጨምቆ ወደ እሱ ተላልፎ እንደ ራሱ ቅባት ሲጠቀምበት የነበረበት ጸረ አትዮጵያ አፍራሽ ነት (አሱ ፌክ-አትዮጵያ ይላታል የገዛ አገሩን) መረን የለቀቀ ነበር። ምንም አንኳ ፈረንጂኛ ችሎታዉ የደመቀ ቢሆንም በአስተሳሰቡ ግን እኛ ትግሬዎች “ተርባብ “ የምንለዉ ፈረንጁ “ዱዋርፍ/ሚጂት- ነበር። ይህ እንዲሆን ያስገደደዉ ደግሞ ከኤርትራዊያኖቹ ያላሰለሰ ምስጢራዊ ረዥም ጓደኝነት ከነዚህ የዋህ “ተራማጆች” ጋር ስለተቆራኙ እና “የአጠባዉ” ሥራ በመካሄዱ ነዉ። የእነ ሌኒን የእነ ማኦ እና ስታሊኖች የራስን በራስ አስከመገንጠል የሚባለዉ ስንኝ (ሆሆያት ልበለዉ?) የረዢሙ የህሊና ያጠባ ሥራ በመካሄዱ ነዉ። በዛ ትምርት አልታጠበ የለም ይመስለኛል፡ ነገር ግን ታጥበናል እና አጣቢቡንና አመንጪዉን አትዉቀሱ ፤አታንሱ! ማለት ስህተት ነዉ። ወያኔ ሲያሳስተን ለምን አሳሳትከን ብላችሁ አትዉቀሱት እንደማለት እኮ ነዉ።ዋለልኝና የወያኔ ስነ ሃሳብ/ቲኦሪ ለየብቻ ናቸዉ እንዳትሉን ብቻ!@
አዎን-ኤርትራኖች በወቅቱ ሁለት የሽብር ዉግያዎች በኢትዮጵያ ላይ አዉጀዉ ነበር። በምድር የቦምብ ቀበራ፤ በሰማይ ደግሞ የአይሮፕላን ጠለፋ_። በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ እኔ ባነበብኳቸዉ ታሪኮች የተመዘገቡ 3 (በገንጣዮችና ከገንጣዮች ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ጠላፊዎች ጠለፋ ተካሂዷል) ጠለፋዎችና እና በርከት ያሉ የከተማ ቦምብ ጠመዳዎች በኤርትራ ተግንጣይ ቡድኖች ያጠቃለለ ነበር ።
የምደሩ የሽብር ጥቃት ማለት በእግር እየገቡ የቦምብ ፍንዳታዎች ለማካሄድ የተላኩ “ፈዳይን” የሚሏቸዉ የሽብር ቡድኖችን ወደ አገሪቱ እየላኩ ጥቃት ለመፈጸም የተሞከረዉን እንመለከት ።ለምሳሌ የሚከተለዉ መረጃ ያገኘሁት ከ1959 ዓም ጀምሮ ጀብሃን ያገለገለ፤ በፈዳይን ስራዎች፤በዓረብ አገሮች በዉጭ ጉዳይ ሃለፊነት አስከ 1983 ድረስ ከጀብሃ ጋር ቆይቶ በ1991 ወደ ሻዕቢያ በመቀላቀል በሚኒሰትርነት እና በ ኢሚግረሽን ጉዳዮች በሃለፊነት እየሰራ ከሻዕቢያ ጋር የሚገኝ ከፍተኛ ባለስልጣን ባሳተመዉ የመጀመሪያዉ የግሉ የገድሉ ታሪክ አምና አሥመራ በገበያ ዉሎ የተዘገበ ጠቃሚ ዶክዩመንት ዉስጥ ነዉ። ሰዉየዉ በጀብሃ የገዳሪፍ ጽ/ቤት ሃለፊ ስለነበር በስራዉ ላይ ተሳታፊነት ስለነበረዉ የገለጸዉን ነዉ።

ወቅቱ በጋ 1968 በፈረንጅ የጀብሃ አመራር አርስ በርስ የተዳከመበት ጊዜ ስለነበር ፈዳይን ወደ ኢትኦጵያ አዲስ አበባ በመለክ የ“አለሁኝ አልሞትኩም” ዮፕሮፖጋንዳ ጥቃት እና ተቀሜታ ለማግኘት ሁለት ታጋዮች መሓመድ ዑመር ሃቢብ (ወዲ ሓቢብ) እና ገብራአብ ዓንደብርሃን (ወዲ ዓንደ) የተባሉት ታጋዮች ኡዚ መሳሪያዎች ቦምቦች እና ጥይቶች በመያዝ ከገዳሪፍ ተነስተዉ በደማዚን አድርገዉ በኮሮኮን በኩል አልፈዉ ወደ አሶሳ ከተማ ሲገቡ በኢትዮ ጵያ ጸጥታ ሃይሎች ተይዘዉ እያንዳንዱ 17 ተፈርዶባቸዉ 17 ዓመት ታስረዉ መሓመድ ዑመር ሓቢብ እስራቱን ፈጽሞ ሲለቀቅ ገብራአብ ግን እስረ ቤት ዉስጥ ታስሮበት ከነበረዉ ክፍል ሞቶ ተገኘ። ይህ አንቅስቃሴ ሲካሄድ ወንድሞቻችን “ተራማጅ ኤርትራዊያን ሃይሎች” በሚሏቸዉ ተማሪዎች ዘንድ በ “ጥሒሻ” ቡድን ይታወቅ ነበር።
ይህ የተቀነባበረ ሴራ በ አገሪቷ ላይ ሲፈጸም ተራማጅ የሚባሉት የያኔዉ ትዉልድ ዲሞክራቶች እነ ዋለልኝ ስለ ኤርትራ ፍትሃዊነት በሕሊናቸዉ ሲያምጡና በስታሊን ትኩሳት ሲነድዱ ኢትዮያ ግን “የአማራዎች አገር!ፌክ ኢትዮጵያ” “የሚኒሊክ የሃይለስላሴ የፈጠራ ስራ” እያሉ እየቦተለኩ ተጨማሪ በሽታ እና ብሄራዊ ዉጋት ይሆኑ ነበር። ዓረቦቹ ያነን የነ ዋለልኝን ቡትልክና አሳምረዉ ያደምቁት ነበር። እነ ዋለልኝ አንድም ቀን ለ ዓረቦቹ ያስረዱት ጽሁፍም ሆነ ያሳዩት መከላከል የለም።
እንቀጥል!፦
አትዮጵያን ለማጥቃት ከአዲስ አበባ ዉጭ አየር መንገዶቿን ኢለማ በማስገባት በወቅቱ በፍራንክፈርት በሚላኖ እና በካራቺ እንዲከናወን እና የ ኤርትራ ትግል በመላ ዓለም ለማስተዋወቅ ከሚል መርሆ የታቀደ እንደሆነ መዛግበቱ ያስረዳሉ።እነ ዋለልኝም ይህንኑ አይጠፋቸዉም።ፓኪስታን -ካራቺ ዉስጥ የተካሄደዉ ጠለፋ እኔ ያቀረብኩት በጦቢያ መጽሄት “ኤርትራ ያመጸኞች የነዉጠኞች የእሪታ፤የሽምብረተኞች ምድር”በሚል አዲስ አበባ ታትሞ በመላ ዓለም የተሰራጨዉ ዶኩሜንታሪ ጽሁፌን ያንብቡ (የእትሙን ቅጽና ጊዜ በትክክል አላስተዉሰዉም)።ስለ የካራቺዉ የጠለፋዉ_ታሪክ፡-
በትንሹ የተከናወነዉን በጨረፍታ ላስታዉሳችሁ።በጋ 1969 በፈረንጆች አቆጣጠር ከላይ የታቀደዉ ጸረ ኢትዮጵያ ሽብር ለማካሄድ ታች አምና በሞት ከተለየዉ የያኔዉ ጀብሃ የሗላ ሗላ የሻዕቢያ የዉጭ ጉዳይ የነበረ ብዙ ሰዉ በመግደልና በመሰወር የሚከሰሰዉ የኮማነዶዉ የጸጥታዉ ክፍል ሃላፊ የነበረዉ ሲሞት ጊዜ የወያኔዉ ስብሐት ነጋ እንባዉ ያፈሰሰለትን ለቀብሩ የሃዝን ደብዳቤ መግለጫ ወደ አሥመራ በመላክ ከላይ ከምታዩዋቸዉ 4ቱ ህንዶች/ፓኪስታኖች ተመስለዉ ከሚታዩት ፎቶግራፋቸዉ፡ አንዱ በ“ዓሊ ሰይድ ዓበደላ” መሪነት ካራቺ ከተማ የኛዋን አየር መንገድ ለማቃጠል ከተላኩት ዓሊ ሰይድ ዓብደላ፤ፍስሃ አብራሃ (ካራቺ)፤ መሓመድ እድሪስ የተባሉ የጀብሃ ኮማንዶ ተዋጊዎች አይሮፕላናችን ካራቺ ከተማ እንዳረፈች ዉስጥ ገብተዉ ከጸጥታ ሃይሎቹ ጋር ተታኩሰዉ ቦምብ በመወርውር ካቃጠሉዋት በሗላ (ዓሊ ሰይድ በፀረ-ጠለፋ መንግሰታዊ ሃይላት በቡጢ ተመትቶ ወድቆ ሕሊናዉ ስቶ በነበረበት የሰከንዶች ወቅት ኢትዮጵያን ወክለዉ የተቀጠሩ ትግርኛ ተናጋሪ ሆስቴሶች “ኣጆዃ!!! ኣጆዃ!!! (በርታ አይዞህ!! አይዞህ!! በማለት የኮማንዶ ቡጢ ባደነዘዘዉ ራስ- ቅሉ ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ በማፍሰስ ያበረታቱኝ ሆስቴሶች አልረሳዉም ብሎ ዓሊ ሰይድ በቃለ መጠይቁ አረጋግጧል) በወቅቱ በቶክስ ልዉውጡ በፓኪሰታን ፖሊስ ተይዘዉ እያንዳንደቸዉ 14 ዓመት ጽኑ እስራት ሲፈረድባቸዉ ኢትዮጵያ ወደ እኔ ይተላለፉ በማለቷ የቻይና መንግሥት ስትደግፍ ዓረቦች በሙሉ ግን አይሆንም ከማለት አልፈዉ፤ በብዙ ሺህ ዶላር ጠበቃ ከዉጭ ቀጥረዉላቸዉ በፍርድ ቤት ተካራክረዉላቸዋል። መጨረሻ ግን 11 ወር ከታሰሩ በሗላ በወቅቱ የፓኪስታን የጠቅላይ ሚኒሰቴሩ ልጅ የነበረችዉ የፓኪስታኗ ወጣሁ ወጣሁ! ባይዋ ሴትዮ “ወ/ሮ በናዚር ቡቶ” በወቅቱ የተማሪዎች ንቅናቄ አመራር ስለነበረች፤ 12 እራሷ ሆና የ72 ሰዓት የራሃብ አድማ በማድረግ ልጃችን ከምትሞትብን ይለቀቁ ተብሎ ከ14 ዓመቱ ቅጣት 11 ወራቸዉ ብቻ ታስረዉ “ሰላም አሊኩም! /“አሊበደርቺ!” ሙያቸዉ ፈጽመዉ በኛዉ ላይ አክታቸዉን “ትፍ” ብለዉብን ወደ ግድያ ጫካቸዉ በሰላም እንዲሰናበቱ ተደርጓል።
ይህ ሲደረግ፤ ተራማጆቹ እነ ዋለልኝም ሆኑ ሌሎቹ ተራማጆች አነ የ ያትዉልዶች (ፈርጦች) ይህ ታሪክ ያወቃሉ፤ያነብባሉ፡ ቢቢሲ እና ዶቾቤሌ ራዲዮን ያዳምጣሉ። ለይግረም ግን ፤ትስስሩ ከነሱ ጋር ይበልጥ እየጠነከረ፤ ወደ ዓረቡ ዓለም እነሱም ማምራት እንደጀመሩ ይታወሳል። ኢትዮጵያ “ፌክ” ነች ! የምኒሊክ “ባምቡላ”-የሃይሌ፤የሸሜዉ፡ በአማሮች ድሪቶ ተደርታ የተጠጋገነች ፤“ፌክ”-የዉሸት ስራ ዉጤት እያሉ አገራቸዉን ታሪካቸዉን ራሳቸዉ ሲያግማሙ፡ ባንጻሩ ግን እነ በናዚር ቡቶ የራሃብ አድማ አድርገዉ ተገንጣዮቹ በተራ ወንጀል መከሰስ የለባቸዉም፡ የሃይማኖት ታጋዮቻችን ናቸዉ፡አስላሞች ናቸዉ፤ “ኢትዮጵአያ ምትባል “፡ፌክ” ጨቁናቸዋለች እና ይለቀቁ ብላ የራሃብ አድማ ስታደርግ የና ተራማጆች ግን ለኢትዮጵያ የጻፉላት “ፕሬስክሪፕሽን” ዲሞክራሲ ሚባል ፈዉስ ሆኖ ምጥ ተይዞ ዲሞክራሲ ሚወለደዉም “ግንጠላ”-የሚባል በ‘ዛርቲ/በደቂ ሕድርትና’-(በኤሊያን ፎርስ) የተሰራ ፈዉስ የመሰነጣጠቂያ የተሳለ ጩቤ ነበር የሳሉላት። ያኔ የተሳለዉ ጩቤ ዛሬም አልጎተመም፡ ስራዉን በዋለልኝ ዘመቻ እየተቀላጠፈ እያየነዉ ነዉ።
ወደ ዚህኛዉ ወዳ ‘ዲስ አበባዉ ጠለፋ እናቅና፡ በወቅቱ የተመዘገቡ ይፋ የሆኑ ጠለፋዎች 3 (ሦስት) ጊዜ ተከናዉነዋል። አንዱ እኔ ከነበርኩበት ከተማ ያርፋል ተብሎ ፕሮግራም የተያዘበት በረራ ነዉ። ካልተሳሳትኩ የመጀመሪያዉ ጠለፋ ብርሃነ መስቀል እና ወንድማችን እያሱ ዓለማዮህ የነበረበት ከአዲስ አበባ ወደ ካረቱም ቤሳ-ቢሲቲን ሳይከፍሉ “በነጻ ቲኬት” የተሳፈሩበት ብሎም ወደ አልጄሪያ የተሸጋገሩበት የጠለፋዉ ትዕይንት ነዉ።

ሌላዉ ሁለተኛዉ ጠለፋ ወደ ሊቢያ እንዲጓዝ ተገዶ- በ አማኑኤል ዮሃንስ የተጠለፈዉ ነዉ። ሦስተኛዉ እና የመጨረሻዉ ህጋዊ ስሙ “አማኑኤል ዮሃንስ” የተባለዉ በተለያየ የዉሸት /መሸፈኛ ስም ሲጠቀም የነበረዉ በሜዳ/የፈረስ ስሙ “ራዲዮ” ተብሎ የሚታወቅ፤ ትምርቱን የመዲሲን /ምዲካል ተምርቱን አቋርጦ ወደ ህዝባዊ ሓይሊታት በመቀላቀል፤ የህዝባዊ ሓይሊታት ተዋጊ አባል የነበረ። ወደ ሊቢያ በተካሄደዉ ጠለፋ ተሳታፊ ኖሮ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ከገረግር -ሱዳን በረሃ የአይሮፕላን ጠለፋ ለማካሄድ ታዝዞ፤ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በመሄድ በንግድ ሥራ እየተሰማራ የሚኖር በማስመሰል ዋለልኝን በፍቅር ያኖሆለለችዉን መልከመልካምዋ “ፍያሚታ-ጊላይ” በማርታ መብራህቱን በኩል ዋለልኝን ለጠለፋዉ ስራ እንዲስማማ እና ጃንደረባዎቹም እንዲቀላቃሏቸዉ በማድረግ የተገንጣዮቹን የጠለፋ ስራ ለ ኤርትራዊያኖች ጥቅምና ተጨማሪ ሃይል እንዲሆኑ አድርጓል።ጠለፋዉ ሲካሄድ ጠላፊዎቹ እነማን እና ለምን አላማ እነደነበር ተገንጣዮቹ ባስተላለፉት የራዲዮ መልዕክት በወቅቱ ተገልጿል። አማኑኤል ዮሃንስ ለማን እየተጋለ እንደነበር ማን እንደላከዉ ከዛ በፊት በሊብያዉ የጠለፋ ተልእኮ የተሳተፈ መሆኑን በጠለፋ ስራ መሰማራቱን ዋለልኝ በሚገባ ያዉቃል።ሃሎ!!!!ኵሩሩር!!!!
እንደተባለዉ የሶሻል/የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ሆኖ ያን መሳይ ጽሁፍ እየጻፈ አንዴት ይሄን ምስጢር ሊደበቀዉ ይችላል? (በሌላ ሃይል ተግፈቶ ነበር የሚጽፈዉ ሲባል- የለም-ገፊ አልነበረዉም-“ሊቅ ነዉ” የምንትስ ምንትስ 4ኛ ኣመት ተማሪ ሆኖ አንዴት ይህን ትንተና ያጣዋል ስለተባልን ነዉ ጥያቄዉን ለመጠየቅ የተገደድነዉ)።

በጠለፋዉ ወቅት የተሰማሩት 3 ኤርትራዊያኖች እና 4 ኢትዮጵአዊያን ነበሩ።ማርታ መብራህቱ፤ አማኑኤል ዮሃንስ ( “ራድዮ”) እና ዮሃንስ ፍቓዱ። በዚህ በኩል ደገሞ ዋለልኝ መኮንን፤ጌታቸዉ ሃብቴ ፤ተስፋየ ቢረጋ፤ታደለች ኪዳነ ማርያም። ነበሩ። (ከደጅም ከዉስጥም ሁኔታዉን የሚያስተካክሉ እና የሚቆጣጠሩ ለጊዜዉ ታሪክ ያላቀረባቸዉም አንደነበሩ ጥርጥር የለዉም)። በ3ቱም ዙሮች የተካፈሉ ኤርትራዊያን ስም ዝርዝር አንደሚከተለዉ ናቸዉ።አማኑኤል ዮሃንስ (በሁለተኛዉና በሦስተኛዉ ዙር ጠለፋ ከነ ዋለልኝ የተሳተፈዉ ነዉ)ደበሳይ ገብረስላሴሙሴ ተስፋሚካኤልዮሃንስ ስብሃቱሙሴ ተስፋሚካኤል (አይሮፕላናችንን ጠልፈዉ ሊቢያ የገቡ ናቸዉ)።ዮሃንስ ስብሃቱ እና ሙሴ ተስፋሚካኤል በ1973 (ፈረንጅ) በተነሳዉ የዉስጥ አመጽ/እንቅስቃሴ (መንካዕ- ተብሎ የሚታወቀዉ የኢሳያስ የአፈና አርምጃ እነደተገደሉ ይታመናል።)

የዋለልኝ የጠለፋ ጓደኛ አማኑኤል ዮሃንስን የእጅ ቦምብ እና ሽጉጥ አሥመራ ድረስ ሄደዉ በማምጣት በጠለፋዉ ዝግጅት እጅ ነበራቸዉ የሚባሉት አንዴ በአሲምባ ፓልቶክ ቀርበዉ የነበሩት ደ/ር መስፍን አርአያ እንደሚታሙ አንዳንድ ማህደሮች ያማሉ። በዚህ ጉዳይ የፓልቶክ አዘጋጆች ስለጠቅላላ ሁኔታዉ የሚያዉቁት ካለ ተጋብዛዉ ቢያስተምሩን ማለፍያ ነበር። እያለኩ “ዋለልኝን አትንኩት፤ ብርሃነ መስቀልን ግን ዝለፉት ያለችሁ ፍርድ ቤት ካለ እኛም መብታችን ያለ ተቃዉሞ ለማስከበርና ዋለልኝን ለመዉቀስ ያመቸን ዘንድ ብትጠቁሙን ምስጋናችን የላቀ ነዉ። አንባቢዎችን ለማስረዳት የምፈልገዉ_ ይህ ዉኢኢት አንጂ ጸብ አይደለም።ዉይይቱ ወንድማዊ እንጂ በእኛ እና በተማጓቾቻችን በኩል የቆሙት ወነድሞቻችን መሃል “ጸብ” እንደሌለን እና ዛሬም ትግላችን በጣምራ እንደምንቀጥል ላሳስብ እወዳለሁ። አምላክ-ኢትዮጵያን-ይጠብቅ።/--www.ethiopiansemay.blogspot.com

Friday, October 17, 2008

በትግራይ ሕዝብ ላይ ስትጮህ የሰማሗት የከረንት አፈይርስዋ አራዊት





 በትግራይ ሕዝብ ላይ ስትጮህ የሰማሗት የከረንት አፈይርስዋ አራዊት
ጌታቸዉ ረዳ የጎሳ ድርጅቶች የሆኑ ኦነግ እና ህወሓት በ1991 ዓ.ም በአሜሪካኖችና በእንግሊዞች እርዳታ በጋራ ወደ ሥልጣን ከወጡ ወዲህ የጎሳ ግጭቱ ከጥላቻ አልፎ ወደ መገዳደል እና ወደ ዘር ማጽዳት ዘመቻ የተሸጋገረበት የዓይን ምስክሮች፤የዘመቻዉ ሰለባዎች፤ታሪክ ዘጋቢዎች የሰብአዊ መብት ጠበቃዎች እና የዜና ወኪሎች የዘገቧቸዉ ሰነዶች በተለያዩ ወቅቶች ለሕዝብ እንዲነበቡ ተደርገዋል።
የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ጎሳቸዉን ለይተዉ ጥብቅና ለምን እንደቆሙ የማሕበረሰብ-የስነልቦና ሊቃዉንት ሲገልጹት፡ባጭሩ የጎሳ ፖለቲከኞች ዓላማ የአንድን ቋንቋ ተናጋሪ ክፍለ ህዝብ በቀረዉ ሕዝብ ላይ የበላይ ለማድርግ መፈለግና መብት በማስከበር ሥም ወደ ሥልጣን ቁንጮ መረማመድ ነዉ ይላሉ።ይህ እንዳለ ሆኖ፤ያብዛኛዎቻችን ችግር ጎሰኘቹ ወዳዘጋጁልን ወደ ዝብርቅርቁ ጨዋታቸዉ ገብተን በማወቅ የገዛ ራሳችንን ለማጥፋት ታይተናል።
 
አለፍ አለፍ ብየ ለትዝብት በጊዜ ሰሌዳ የምጎበኛቸዉ የፓል-ቶክ መድረኮች አሉኝ። ሰሞኑን ተራ ደርሶት የጎበኘሁት “Ethiopian Current Affairs Discussion” የሚባለዉን የፓል ቶክ መድረክ ነበር። መድረኩን ሦስቴ ያክል የጎበኘሁት ይመስለኛል። ከሦስቱ ሁለቱ ጊዜ ከተሳታፊዉ ይልቅ አዘጋጆቹ ለምን እንደሚጮሁ ባይገባኝም ሃይለ ቃል እየተጠቀሙ ፤የቀይ መብራት ቁልፍ በመጫን ጎብኚዎችን የማባረር ሥልጣን እንዳላቸዉ አስኪ ሰለች ደጋግመዉ ሲዝቱ ዛቻዉ ቡረቃዉ ከመጠን በላይ ነዉ። በአመለካከት የተቃወማቸዉ በተለይም ከረር ያለ እንደሆነ ቅጽበታዊ-ቁልፉን ተጭነዉ ከመድረኩ ያስወግዱታል።ባጭሩ “ይገድሉታል!” በነገራችን ላይ ይህ ነገር በሳላ በተባሉ መድረኮችም ይህ ጸባይ ሲያደርጉ ታዝቤአለሁ። ከዚህ ፍርሃት የተነሳ ሌሎች የሚወያዩትን ሃሳብ እንዳያመልጣቸዉ በመስጋት ከመድረኩ ላለመባረር በተለይም አዘገጆቹን ወይንም የአዘጋጆቹ ቅርብ ተዋዳጆች(ጉሩፖች) ላለመተናኮል/ላለመነካካት በመጠንቀቅ ሃሳብ ከመስጠት ተቆጥበዉ ሃሳብ ከመሰንዘር ይልቅ አድማጭ መሆንን ይመርጣሉ። አዘጋጆቹ በተለይም (ሴቲቷ) በመንግሥት ሥልጣን ተቀጣሪ ቢሆኑ ኖሮ የደርግን ካድሬዎች ዓይነት ጋጠወጥ ማን አህሎኝነት ባሕሪ ቅጂ ከመሆን አያልፉም ነበር የሚል ግምት አለኝ።
 
ይህ ዘመኑ የለገሰን ጥበብ ልቅ-መብት ተሰጥቶ ያለተቆጣጣሪ ማንም ለፍዳዳ መድረኩን እየከፈተ “የመሸታ ቤት ዲሞክራሲ” ፈልስፎ ሕዝብን ሲዘለፍ ስናደምጥም የጥቡበ መጥፎ ገጽታዉ ተጠያቂነት ያለመኖሩ በእወነቱ ይህነን የሚያስቆም መንገድ መፈጠር አለበት እላለሁ። ሰሞኑን በእኛ በትግሬዎች ላይ ስትጮህ የሰማሗት የካረንት አፈይርስዋ አራዊት ምን ስትል እንደሰማሗት አንዳፍታ ላዉጋችሁ።
 
በመድረኩ ላይ የመነጋገርያዉ ርዕስ በሸራተን ሆቴል ዉስጥ ትግራይን ለመገንባት በተደረገዉ ዓለም አቀፍ የትግሬዎች ማሕበር የገንዘብ መዋጮ ላይ ነዉ።ልጅቷ ከአዘጋጆቹ አንዷ ነች። ትጮሃለች፤ትሰብካለች፤ስሜቷ ሰማይ ደርሷል። አዋጊም አዛዢም ትልም አዉጪም ሆናለች።ስለ ሸራተኑ እና ስለ ትግራይ ሕዝብ የምታዉቀዉም የማታቀዉም የተቻላትን ሁሉ እየዘበራረቀች ታወራለች። የሕዝብ ቆጠራዉ ከየት እንደለቀመቺዉ ባለዉቅም የትግራይ ሕዝብ 5ሚሊዮን መሆኑን ታስረዳለች። “እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በቁጥር ሲነጻጸር እጅግ ስለምንበልጣቸዉ ተባብረን 5ሚሊዮኖቹን ትግሬዎች ማሸነፍ አለብን!” እያለች ትእዛዝ እና ቅስቀሳ ታካሂዳለች። አብዛኛዎቹ የድጋፍ ጽሁፍ፤ አንዳንዶቹም በሕዝብ ላይ የብልግና ትችት ሲጽፉ አንዱም በሁኔታዉ ተገርሞ “ይህች ሴት አደገኛ ነች! ሲበዛ ማይምነት አይሏታል! የሩዋንዳን ዓይነት ግጭት በእኛም ዘንድ እንዲነሳ እየሰበከች ነች!..ወዘተ በማለት 5ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ “እናሸንፈዋለን” ማለት ብልግና እና ወንጀል ነዉ፤ ነዉር ነዉ” በማለት ሕዝብን እናንበርክከዉ ስትል በጮኸችዉ በዛችዉ አራዊት ላይ ቅዋሜዉን የገለጸዉ ሰዉ ቅጽበታዊ የማስወገጃ ቁልፉን ተጠቅመዉ ከመድረኩ አስወገዱት። ሌላዉም እንደዚሁ አስወገዱት፤ሁኔታዉ አላማራቸዉ የተቀሩት ቀስ እያሉ ከመድረኩ ራሳቸዉን አስወገዱ። በዚህ ጊዜ እኔም ቅሬታየን ልተነፍስ ብል ምን ዕጣ እንሚደርሰኝ ስላወቅኩ ነጻነትን በሚቃወም ሽብር በሚለቀዉ ቁልፋቸዉ “ሳልገደል” ራሴን አስወገድኩ።
 
ይህ መድረክ ካሁን በፊት ተመሳሳይ ጸረ ትግራይ ሕዘብ ቅስቀሳ ተደርጎ የመድረኩ አዘጋጆች ሰበካዉን ባለማስቆም በነጻነት እንዲተላለፍ በማድረጋቸዉ ያንድነትና የሰላም ወገኖች ያንኑ ቀድተዉ ለሕዝብ እንዲደመጥና ጥላቻ እና ጎሰኛነት ወንድም በወንድም ላይ እህት በእህት ላይ ምን የት ያህሉ እየተሰፋፋ መሄዱን ለማስገንዘብ ይፋ ሆኖ በየህዋ ሰሌዳዉ ተለጥፎ አንደ ነበር ይታወሳል። ይህ መድረክ የብርሃኑ ነጋ፤የብርቱካን መዲቅሳ፤ብርሃኑ መዋ እና የአንዳረጋቸዉ ጽጌ የፕሮፓጋንዳ መፈንጫ እንደነበረ እና ዛሬም ካልተሳሳትኩ ፖለቲከኞቹ ከሚጠቀሙበት ሚዲያቸዉ አንዱ ይህ ጎሰኞችና በስሜት የሚነዱ እንሰሳዎች የሚበዙበት “ኢትዮጵያን ካረንት አፌይርስ ዲሰካሽን” ይመስለኛል። በዚህ ሚዲያ ሕዝቡ አትኩሮቱ እንዲጥልበት ሳሳስብ ቀጥሎ ወደ ፖለቲካዉ ሂሱ በመግባት ትንሽ ልበል እና ልሰናበት።
 
ብዙ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እና መግለጫቸዉ ምንም እንኳ ወያኔ ጎሳዉን ለመጥቀም ቢሯሯጥም በሰባዊ እና በዲሞክራሲአዊ ምብቶች ሕዝቡ እንደኛዉ በወያኔ መሪዎች እና ፖሎሲ የተረገጠ በመሆኑ ሕዘቡን ጠላት አናደርገዉም ቢሉም ዛሬም በርካታ “የሰዉ-አራዊቶች” በዙርያችን ስላልታጡ የትግራይ ሕዝብ እንደጠላት እያዩ “እናሸንፈዉ! እናንበርክከዉ! እናጥፋዉ! እንማርከዉ..” የሚሉ አልጠፉም።ልጅቷ ከሆዷ ዉስጥ አስራ አፉን ከፍቶ የተራበዉን አራዊቷን እኛኑን 5 ሚሊዮናችን ለመዋጥ እፈታዋለሁ እያለች የምታስፈራራን ዛቻዋን ለምን እሰከዚህ ድረስ በድፍረት መድረክ ላይ ወጥታ የሕዝብ ፍጅት ለማየት እንደናፈቃት ራሴን ስጠይቅ በወቅቱ ቅስቀሳዋ አስቆጥቶ-ቢያሳዝነኝም፡ ልጅቱን ቀጥተኛ ተጠያቂ አላደረግኳትም።ምክንአቱም ከፋፋይ ሃይል ብለን የምንጠራዉ ብቻ አይደለም ተዋናያንና መሪ ወንጀለኞች። ለምሳሌ “በኦኖጎች እና በመሰሎቻቸዉ እንዲሁም የእስልማና አካራሪ ሃይላት በአማራዉ እና በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ ያላቸዉን ጥላቻ እንዴት እና ወዴት እንዳመራ ማንስ አንደመራዉ ጸሐፊዉ አቶ ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ሲገልጹ እንደሚከተለዉ አቅርበዉታል
 
“ወንጀላቸዉ አማራ ገድለዉ አርደዉና ከገደል ጫፍ ወደ ታች በመጣል በጭካኔ ብቻም አይደለም። በሰዎቹ መርዝ አብደዉና ያበደ ፍልስፍና እንግበዉ ያልሆኑትን ሆነዉ፤ያልሆነዉን ረግጠዉ ከዚህ መሬት ማህጸን ዕኩል የተወለደዉን የእናትም የአባትም ልጅ ጠላት አድርገዉ በማየታቸዉ ሌሎችም እንዲያዩ በማድረጋቸዉ አዝናለሁ።ታሪክ አያዉቁም አልልም።ያዉቃሉ። በእነዚህ ተለማማጅ የፓሎቲካ ሰዎች ላይ የምናየዉ ጉድፍ ግንባሩን ግን በክፋ ክፉ የታሪክ ገጽ ላይ ለማተኮርና በክፉ ክፉ መፍትሔ ላይ ዓይናቸዉን በመጣላቸዉ ነዉ። ይህ ሕዝብ ስለሚቀጥለዉ ትዉልድ ሕልዉና ሲጨነቅ እነሱ ዛሬ ሊያገኙ ስለሚጓጉት ሥልጣን እንቅልፍ አልባ የሚሠሩት ተንኮል አልተገጣጠመም እንጂ ሰንደቅ ዓላማችን ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ሕልዉና ዋስትና ሊኖረዉ አይችልም ነበር። በደኖ ይሉናል። አርሲ ይሉን ይሆናል። ቀጥሎ ግምቢ ይሉን ይሆናል። አሶሳስ?...”
 
በእርግጥም እሳቸዉ እንዳሉት ማንነታቸዉን ሲጸየፉና ያልሆኑትን ካልሆኑበት ሥፍራ ሲፈልጉ ማን አለመሆናቸዉን ለማወቅ ሳይችሉ በጨለማ ሲዳክሩ እያነጣጠሩበት ያለዉን ወዳጅ ይሁን ጠላት መለየት ሳይችሉ ቀርተዉ እንዲሁ በደፈናዉ ራሳቸዉን እና የራሳቸዉንም የሆነዉን የዒላማቸዉ ተጠቂ ያደርጉታል። ስለሆነም በከረንት አፌይርስ ፓልቶክ መድረክ ላይ ወጥታ በ5ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ ላይ የዘመቻ ጥቃት ጥሪዋን ስታስተላልፍ የሰማሗት አራዊት የአንድ አገር ሕዝብ ክፍል በሌላኛዉ ክፍለ ሕዘብ ላይ ተሸናፊ እና አሸናፊ አንበርካኪ እና ተምበርካኪ የሚታይበት መድረክ መቀስቀሷ፤ በወየኔ እና በሻዕቢያ መሪዎች ፉክክር ምክንያት የመረብ ምላሽ ህዝብ እና የትግራይ ሕዝብ ተላልቆ አንዱ በሌላኛዉ የአሸናፊነት ስሜት እንዲኖረዉ የተጫረዉ “የሞኞች- ጦርነት” ከዚህ የማሸነፍ እና የተሸናፊነት ስነ ልቦና አስተሳሰብ የመነጨ አደገኛ አስተሳሰብ መሆኑን ይህች ልጅ የብዙዎቹ ደንቆሮች ናሙና መሆኗን አልተጠራተርኩም። በተለይም ልጅቷ የጠራ አማርኛ ስትናገር በመስማቴ አመራ ትሆን? የሚል ጥያቄ ስላደረብኝ፤ ከሆነችም ተባብረን እናሸንፈዉ ምትለዉን የትግራይን ሕዘብ ለአመራዉም ሆነ ለተቀረዉ የኢትዮጵያ ክፍለ ሕዝብ ምኑ መሆኑን ላስረዳ።
 
አታዉቀዉ ሆና “እኔ አማራ እንጂ እኔ ጉራጌ፤ እኔ ኦሮሞ እንጂ፤ እኔ አደሬ እንጂ እኔ ዓፋር እንጂ.. ሶማል አንጂ…ትግሬ አይደለሁም ብትለንም” ወያኔም “በጎሰኛ መጽሃፉ ትግሬነት ለዕገሌ… እንጂ .. ለዕገሌና ..ለእገሊት … ምኑም አይደለም ቢለንም” እሱም እነሱም አናንተም አንቺም አሷም እኔም ሁላችንም ትግሬዎች ነን።ከትግራይ እና ከአማራዉ ደም እና አጥንት ባህሪና ባህል ያልተቀላቀለ ጎሳ ከቶ ማንም የለም። ትግራይ እና አማራዉ ያገሪቷ መሰረታዊ መስራቾች ሆነዉ በግንባር የተሰለፉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ መሆናቸዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ መገንዘብ የታሪክ አዋቂነት ይመስለኛል። -መሬቷን-ድምበሯን ሰማይዋንና ወለሏን ማለትም የአገሪቱን ግምብ ሲገነቡ በተዛማጁ የእነኚህ ማሕበረሰብ ደም እና አጥንት ከሌላዉ መሕበረሰብ ቋንቋ፤ባሕል፤ደም እና አጥንት ጋር እየተዛመዱ እየተጋቡ እየኖሩ እና እየተገበያዩ በሰላሙና በጦርነቱ “የተዋሃደ-ማህበረስብ” ዘርተዉ አብቅለዉ አሰሳድገዉ ይሄዉ እስላሙም ክርስትያኑም ተዋህደዉ ኦሮሞዉ ጋምቤላዉ ቤንሻንጉሉ ጉራገዉ አማራዉ ትገሬዉ… ወደ 75 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት ደርሰናል። እኛ ያለፉት የነሱ ዉጤቶች አብረን እነጋገራለን።ባስደናቂ ጥበባቸዉ በ አንድ መሬት ባንድ አገር ወለልና ጣራ አኑረዉን ሄዱ።ሂደቱ ሻዕቢያዎች፤ኦኖጎች ወያኔዎች ላማስቆም ቢሞክሩም ተፈጥሮን ማስቆም አልተቻላቸዉምና ዛሬም ከማንኛቸዉም ቁጥጥር በላይ ወጥቶ ዕድል በተገኘ ቁጥር ዉህደቱ በመቀጠል ላይ ነዉ። ቋንቋዉን መናገር የደም ትስስሩ ማንነቱ መለያ ሊሆን አይችልምና ሁላችንም የአንድ ፈጣሪ የፈጠረን ፍጡር ወንድም እና እህትማማቾች ነን።በዚህ ላይ አንድ ልበል እና ልሰናበት።
 
“አማራ በነገድ በዘር በቋንቋ በባሕልና በዕምነት ከአክሱማዊያን/ትግሬዎች ጋር ተቀራራቢ እና ተመሳሳይ ከሆኑት ወገኖቹ የአማራ -ብሔረሰብ አንዱ ነዉ። የአክሱምን/የትግሬዎችን መንግሥት በቀጣይ ያዋቀሩት አማራዎች ናቸዉ። ስለሆነም ነዉ “የአማራ/ትግራይን (ኢትዮጵአዊነት) ከባድ የዘር ሚዘን ተሸክመን ከምፅዋ አስከ ቦሮና ከጋምቤላ አስከ በርበራ ከሚያደክም እና ከሚፈትን ጉዞ ቤጃዎች አገዎች ኦሮሞዎች ገላግለዉን ቁጭ!! የአማራም ሆነ የትግራይ ዘረ-ድንግልነት እና ዘረ-ንጹህነት ከብዙ ዘመናት በፊት መፈራረሱን አረጋግጠናል” {ዋሕድ (የሕብረት ልሳን) ቅጽ -ቁጥር 4 ገጽ 9}። //-// አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

Sunday, October 12, 2008

ኤህ! ዕድሜህ ይጠር! ቪኦኤ -ይሄን ጉቶ ደግሞ ከየት ጎተቱብን? አልኩኝ-




ኤህ! ዕድሜህ ይጠር! ቪኦኤ -
ይሄን ጉቶ ደግሞ ከየት ጎተቱብን? አልኩኝ-
ጌታቸዉ ረዳ
“መቆየት ደጉ” የሚሉት ለካ በዕድሜያቸዉ ያላዩት አስገራሚ ነገር ለመስማት ሲጓጉ ነዉ። ዕዉነትም መቆየት ደጉ።
ሁሌ ይሁን፤አልፎ-አልፎ-ብቻ፤-የታሪክ ፍጻሜ - የሚባል ነገር አላቸዉ ጸሐፍት ሲጽፉ። ዓለም ሸጋ-ሸጋዉን በልታ በራሷ ላይ ዘመቻ ከፍታ መጨረሻ ራሷን ስታጠፋ የሚታየዉ የመጨረሻዉ ትዕይንተ-ሕወት መሰለኝ ይሄ የታሪክ ፍጻሜ የሚሉት ጸሐፍቱ። ደርሰንበታል-እኮ!አልደረስንበትም አትበሉ። ላንዶቻችን እኮ አርማጌዶን ነዉ። ከሀገር የሚያስኮበልል ጠላት በተቀመጠበት ምድር መኖር ሌላ “እንግላቴራ” (የእንግሊዝ ቋነቋ) ፍጠሩና ስሙን ስጡት እንጂ “ከአርማጌዶንነት አያልፍም።እኛ ትግሬዎች “ምጽኣተ-ዓለም” የምንለዉ እኮ ነዉ አርማጌዶኑ። ወይ እሩብን መንግድ ላይ አልያም ግማሹ ላይ የደረስን መሰለኝ። ሃማ ቱማ “ቃለ አጋኖ” የሚለዉ ዓይነት ባትሉኝ ሙሁራን ወደ “ጉቶነት” ሲለወጡ ወደ አርማጌዶን/ወደ ምጽኣተ-ዓለሙ የሚወስደዉ መንገድ ግማሽ መንገድ ጠረጋ እየተጠረገ መሆኑን እመኑኝ። ብርቱ ሥራ ጠምዶኝ ነበር። ቪኦኤን ካዳማጥኩ ቆይቻለሁ። አረፍኩና ዳሰስኩት።ስለ ማዕቀብ መጠናከር በኢትዮጵያ ወቅታዊነት ይናገራል። ያዉም የማከብረዉ፤ዉዱ የቁርጥ ቀን ሰዉ፤ የምርጫዉ ስንሻዉ የዛ ምኡዝ ቃና፤ የኢትዮአዊነት ድምፅ! ደስ አለኝ! የቪኦኤዉ አዲሱ እና ወንድሜ አቶ ምርጫዉ በቃለ ምልልስ ይወያያሉ። ምርጫዉ ከእንጀራ መግዛት አስከ የወያኔ ምግብ ቤቶችና ትልልቁ የወያኔ የንግድ አዉታሮች ላይ ማዕቀብ ማድረጉ ካሁኑ መጀመሩ ወቅታዊ ፤ሞራላዊ እና ሕጋዊ መሆኑን ያብራራል። ስለ ጤፍ ጉዳይ ብንመለከትም “ወያኔ በኮንተይነር እየጫነ “ኦሃዮ ሰቴት” በሳምንት ሁለት ጊዜ እያራገፈ ያከፋፍላል። ህዝቡ ተርቦ እያለ፤ ጤፍ እየጫነ ወደ እዚህ መላኩ በሰብአዊነትም በሞራልም ያስወቅሳል። ተከራካሪየ ካነሱት ዘንዳ ላይቀር አየር መንገዱንም በሚመለከት፡ በኢትዮያ አየር መንገድም ይሁን በማንናወቸዉም ማዕቀብ እንዲደረግ እንፈልጋለን፡ አስከ ዛሬ ድረስ ማዕቀብ በማድረግ አገዛዙን አልታገልነዉም። ሕበረተሰቡን ማለማመድ አለብን።ሕዝቡ ነገሩን አዉቆት፤ገብቶት፤ ለምን እንደሚያደርግ አዉቆት፡ከትንሹ ወደ ከፍተኛዉ የአገዛዙ ተቁዋሞች መሸጋገር አለብን። ደረጃ በደረጃ እየገለጽነዉ ነዉ እንጂ ብሎም ህዝቡ አስኪለማመደዉ ብለን እንጂ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በፈቀደዉ መንገድ አገዛዙ ላይ ማኢቀብ አርጎ አገዛዙን ብያዳክምልን ደስታችን ነዉ”። ይላል ምርጫዉ። “አየር መንገዱ ላይ ማዕቀብ መጣል አገሪቱን ለማንኮታኮት ነዉ። አየር መንገዱ ቢወደቅ ተመልሶ እሱን መሳይ ለማግኘት የሚወስደዉ አመታት አና ጉዳት ኢሕዴግ ከሚወድቀዉ በላይ ጉዳት ይደርሳል። ማእቀብ በወያኔ ላይ አይሰራም እና ወያኔን ተንከባክባችሁ ኑሩ የሚል ተማጓችም የደመጣል።
ተናጋሪዉ ምርጫዉ ስንሻዉንም በፊደላዊ ትዕቢት ሲጎንጥ -የአስተሳሰብ ጥረት ይጎድለዋል። ሲሉ ራሱን ባለ ጥራት አድረጎ ይመጻደቃል። "…ቃላት መደርደር ይቻላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለቀ ነዉ! ሰዉ እየሞተ ነዉ! ሰዉ እየተቀበረ ነዉ! የኢሕአዴግ መንግሥት እየገዛዉ ነዉ! እየጨፈጨፈ ነዉ!.. የሚሉት ስሜታዊ ቃላቶች መደርደር ይቻላል። ነገር ግን እኔ የምለዉ ነገር አይገባቸሁም። "input out put የሚባል ፈረንጂኛዉ የማይገባችሁ “ፋራዎች” ትግሉ ዉስጥ አትታገሉ። የኔ ልምራችሁ። እኔዉ ዶክተሩ! ይላል።
 
'አቶ ምርጫዉ ኢክኖሚከስ ትምርት እንዳላቸዉ አላቅም። (አዲሱ ጣለቃ ገብቶ- ለተራዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ እየተናገርን ያለነዉ እና ለተራዉ ሕዝብ ልናስረዳዉ ያስፈልጋል። በዚህ ብንነጋገር”? 'እሺ.. እሺ…የምቀንኝነት እና የድህነት ፊሎሶፊ ነዉ ወይስ ፑር ፊሎሶፊ ነዉ? ወይስ ፊሎሶፊ ኦፍ ፖቭርቴ? ነዉ የሚናገሩት?። ድሃዉ ገበሬዉ ስሜቱ እየቀሰቀሱት ነዉ። አንዲንገነፍል! አንተ ድሃ ነህ ይሄዉ ..ይሄዉ ኢሕአዴግ ስልክህ እየተጠቀመብህ ነዉ ….እያሉ።…’ “ ማእቀቡ በአየር መንገዱን በሚመለከት፤ የሰዉ ሃይል ትሬይኒግ ለማድረግ አገሪቱን ያለ አየር መንገድ ሊያሳጣት ነዉ። በተለይ የካርዱን ስልክ ይሁን የእንጀራዉ ማእቀብ ማድረግ የኔን መብት መጋፋጥ ነዉ።የፈለገዉ ሰዉ ሄዶ መብላት ይችላል። ይህ ለወያኔ “ኤ ድሮፕ ኦፍ ዋተር ኢን ዘ ኦሽን” ነዉ።ለመሆኑ የሄ ጥሪ የሚያደርገዉ ማን ነዉ? ይህ ማዕቀብ መሣርያነቱ “ታንክ ነዉ? ጩቤ ነዉ? ምንድ ነዉ የሚያደርገዉ? ስለዚህ ለኔ ስሜት አይሰጥም። ማዕቀብ አይሰራም፡ ጊዜዉ አይደልም። ወያኔንን መተንኮሻም አይደልም። ገፍቶ መጣያም አይደለም። የፕርንሲፕል እጦት ነዉ!>> ብሎ ሲጨርስ ፈረንጁ “ፓራፍሬዝ” እንደሚሉት ነገር ላጠቃልለዉና...
ጉቶዉ ጉቶ ብቻ መሰላችሁ? ያዉም “ዶክተር!”፡ ብቻ መሰላችሁ ከታራ ሕዝብ መነጋገር የሚጠየፍ ዓባይ ወንዝ ተሸክሞ አዙሮ አዙሮ ከሕዝብ አስርቆ ዕሩቅ የወረወረዉ “ጎቶ”።ያዉም መለስ ዜናዊ እና ካሱ ኢላላ ለካቢነት አጩኝ የሚለን ደ/ር ጎቶ! “አየር መንገድ ሰርቼ ነበር” ይልና ደርግን ወቅሶ ወያኔን ሲሸልም ይደመጣል።አላወቀዉ-እንዶህ-እንጂ መዝገቡ የሚለዉ ሌላ እሱ የሚያወራዉ ሌላ። አስኪ- “የምሁራን መራቆት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በጦቢያ ላይ ከዓስር ዓመት በፊት በ1991 የቀረበዉ አቶ ወልዱ ሃይሉ የተባሉ ጸሃፊ ስለ አየር መንገዱ ያሉትን በጥቂቱ ልግለጽ። &ltየኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎሳ ፖለቲካን በመቃወም በገዛ ፈቃዳቸዉ ሥራቸዉን የለቀቁ ከ5 በላይ የሚሆኑ አብራሪዎችም ነበሩ። <<አምባገነን እና ጭራቅ> እተባለ በወያኔ በሚወገዝዉ በደርግ ሥርዓት እንኳን የአገራቸዉ አንድነት ጥያቄ ዉስጥ በለመግባቱ፤ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ባላቸዉ ፍቅር፤ በዝቅተኛ ደሞዝ አየር መንገዱን ያገለግሉ እንደነበር ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ የሌላ አገር አይሮፕላን ያበራሉ።
ጉቶዉ ይህነን ታሪክ ያዉቀዉ ይሆን? የዉሸት ቃላት እየደረደራችሁ “ወያኔ ሕዝብ ጨረሰ ፤ሰዉ አለቀ እያላችሁ በስሜት በምቀኝነት ገበሬዉን ትቀሰቅሱታላችሁ የሚለን ይህ “ጉቶ” “የጎሳ ፖለቲካ አላሰራም አለን ብለዉ ያነን በመቃወም ከ 5በላይ የንግድ ኢይሮፕላን አብራሪዎች አገሪቱን ለቀዉ ለባዕድ ተቀጥረዉ ሲሰሩ አየር መንገዱ አልተጎዳም ሊለን ሊሆን? የነዚህ አገር ጥሎ መሰደድሳ የኛ የስሜት የዉሸት ቅስቀሳ ይሆን? The worlds 20 worst living dictators ተብሎ በዓለም ምድር ዉስጥ ከተመዘገቡት ጭራቆች ባንዳዉ “መለስ ዜናዊን” በጦርነትም አትዋጉት፡ በኢኮኖሚ ማዕቀብም መታገል ሕዝብን ማደህየት አገር ማራቆት ነዉ ብሎ ሲከራከር፡ “ጉቶዉ” በሰማዩ-ዓለም ዉስጥ እየኖረ ወይንስ የሀገሩን ሁኔታ አያቅም? አየር መንገዱን በማዕቀብ ማንኮታኮት በሰዉ ሃይል ሥልጠና ምክንያት ወደ ሗላ ልንሄድ ነዉ ይቅርብን እያለ ሊሰብክ ይሞክራል። አስተማሪዎቹ ያላስተማሩት አሱ ያልገባዉ የማያዉቀዉ አነድ ነገር አለ። አገር እየለቀቀ የሄደዉ በጣም አንቱ ሚባሉ ወደ አምስት ሺህ ሳይነቲስቶችና ሃኪሞች ጠበብቶች ኢትዮያን ለቀዉ ባእድ አገር እያገለገሉ መሆናቸዉን አያወቅም!? እነኚህስ በእኛዉ ማዕቀብ ወይስ ጉቶዉ እንደሚለን ቃላት ደርድረን ከሀገር አንዲወጡ ያደረግናቸዉ ናቸዉ? እስኪ ልጨምር 'ስደተኝነት በፓለቲካ ወይም ባኮኖሚ ችግር ምክንያት ሀገር ለቆ መዉጠት ብቻ አይደለም። መዉጫዉ በር እየተዘጋበት እንጂ ቢወጡ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ባለማወቅ እንጂ በመንፈሳቸዉ የሸፈቱ የሞራል ስደተኞችና የሕሊና ድርቅ ያጠቃቸዉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ከ50ሚሊዮን በላይ ነዉ።>> ጦቢያ፤ቅጽ 5፤ቁትር 8/1990)' በሚል ርዕስ አዲስ ትርቢዩን ጋዜጣ በአምዱ ላይ ቀረበ ያሉትንም ልጥቀስ። << የተሻለ ዕዉቀትና ብሩሕ አእምሮ ያላቸዉ ሰዎች አገራቸዉን ጥለዉ ወደ ዉጭ አገር ከተሰደዱ እንዴት ነዉ የአገር መሪዎችን ማግኘት የሚቻለዉ?>> “በጉቶዉ” ጭንቅላት አገሪቱ እየተራቀተች ያለችዉ ጤፍን ወደ ኦሃዮ ማስጋዙ ብቻ መስሎታል። ለወያኔ ሥርዓት አይበጁም የተባሉ ለፓርቲዉ ዓላማ ዕንቅፋት ናቸዉ የሚባሉ የሕክምና፤የሳይንስ፤የሕግ፤የኢኮኖሚክስ፤ወዘተ፤ባለሞያዎችና ጋዜጠኞች በረቀቀ ስልት አገራቸዉን ለቀዉ እንዲሄዱ ግፊት ተደርጎባቸዉዋል። ቢወጡም ጤና አይሰጡኝም ያላቸዉን ምሁራንም በሰበብ አስባቡ ወህኒ አጉሯቸዋል። እንዲህ ዓይነቱ አፈራሽ ዕርምጃ አገሪቱን ያወደማት መሆኑን በዛዉ በጉቶዉ ጭንቅላት ዉስጥ የለም። ይህ ሁሉ ምሁር በእኛዉ የስሜት ቅስቀሳ በቃለት ድርደራ ከተጋዘ እማ ዶክተርነቱ ለእነ ምርጫዉ ለእኛዉ ለተራ ህዘቦች እንጂ "ለጉቶቹ አይገባም ማለት ነዉ። ያች አገር እየተገዛች ያለችዉ በዉጭ ሃይሎች የተደገፈ አገር አፍራሽ “ኤርትራዊ ቡድን” መሆኑን እናዉቃለን። ለዚህ ነዉ አየር መንገዱ ቢወድቅ ነጮች ቢሊዮን ዶላሮች ወያኔን (አሱ ኢሕአዴግ ይለዋል) በማግስቱ ያሰታቅፉታል። የሚለን “ዶክተር በሉኝ” ዶክተር ክንፈ ሚካኤል አስራት-!
ህዝቡ “ኤርታረዊዉ የጭራቁን ቡድን” የተቆጣጠራቸዉ ምጣኔ ሃብት በማእቀብ ሲያንቀዉ ፈረንጆቹ ከረዱት ለፈረንጅ ያደረን መንግሥት አታሰወግዱትም አትድከሙ፤ ጊዜዉ ዛሬ አይደለም፡ ሌላ 17 ዓመት አስቲ ስጡት፡ የፈለገዉ ይንቀባረርበት!ብሎ የሕዝብን ትግል የሚያጣጥል አደናቃፊ “ምሁር” በቁሙ የተገነዘ ተንቀሰቃሽ ሬሳ መሆኑን መቀበል አለበት።
ይሄን ትልቅ ከረጢት ክፈቱና ያገሪቱን ችግር ዳስሱት። በዝሁ ልሰናበታችሁ። “ከትልቁ ያገሪቱ ዩኒቨርሲቲ 42 ሙሁራን << በብቃት ማነስ> ሽፋን ተባርረዉ ከአለም ቀዳሚ በሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች በአዉሮፓ እና አሜሪካ ምድር መጥተዉ ሲቀጠሩ አገር እንዲፈርስ ያደረገዉ የተባረሩት ምሁራን ወይስ “ጉቶዉ” አትንኩት እያለ እተካላከለለት ያለዉ “የጉቶዉ” አለቃ “ወያኔ”?
ቅድም ያነሳሁዋቸዉ ምሁር አቶ ወለዳይ ሃይሌ በወያኔ ምክንያት ሙሁራን እየተሰደደዱ አገሪቱ እየፈረሰች እንዳለች ያመለከቱበትን አንዱን ልድገም እና ላጠቃል።”በእርሻ ኢንዱስትሪ ልማት በባንክ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ 15 የሚሆኑ የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሞያዎች ተባርረዋል። እነዚህ ባለሞያዎች በምጽዋትና በእንስሳት ሳይንስ ስምንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉ አራት ሁለተኛ ዲግሪያቸዉ የፈጸሙና ሦስት በዶክትሬት ደረጃ የተመረቁ ናቸዉ። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ ዜጎች ኑሮአቸዉ በአሜሪካ እና ባዉሮፓ መስርተዉ ዕዉቀታቸዉም ለባዕድ ሲሳይ ስለመሆኑ ይታወቃል። ይህ ጉድ ያሳሰባቸዉ አንድ የመንግሥት ባለስልጣን እንዲህ አሉ። የተባለዉ እናንብበዉ የኢትዮጵያ የትምህርት በጀት በሙሉ ለአሜሪካ ትምህርት በጀት ድጋፍ ሰጪ ከመሆን ዉጭ ምንም የፈየደዉ ነገር የለም ብሎ ማሰብ ይቻላል። ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ሃብቷ ያዋለችዉ ወደ አሜሪካ ለሚነጉደዉ ዕዉቀት ነዉና። ይህም ከተማረዉ ሰዉ ሃይል ዉስጥ የተሻሉትን የሚነጥቅ ሂደት ነዉ' ይላሉ። እንግዲህ በወያኔ ንግድ እና የገቢ ምንጮች ማእቀብ ማስተላለፍን አገር ያፈርሳል ወይስ ግማሽ ሚሊዮን ምሁር እና 4ሚሊዮን ኢትዮያዊ ዜጋ ለስደት ዳርጎ፤ሀገሪቱን ምርጥ ምሁራኖቿን አሳጥቶ ሀገሪቱን እያፈራረሰ ያለዉ ቅጥረኛ ስርዓት የሚያደርሰዉ ጉዳት ይበልጣል? “ጉቶዉን” ትቼ ፍርዱን ለናንተዉ ለአንባቢያን ልተዉ። !አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ! www.ethiopiansemay.blogspot.com


Thursday, October 9, 2008

በገብሩ አስራት ላይ እመሰክራለሁ ያለን በቀለም ያበደ በጥንቃቄ የተደጎሰዉ ታሪክ ለምስክርነት ቀጠሮ ያስያዘዉ ባለ 160ዉ ገጽ መጽሐፍ

በገብሩ አስራት ላይ እመሰክራለሁ ያለን
በቀለም ያበደ በጥንቃቄ የተደጎሰዉ
ታሪክ ለምስክርነት ቀጠሮ ያስያዘዉ
ባለ 160ዉ ገጽ መጽሐፍ
ጌታቸዉ ረዳ ወያነ ትግራይ ለጎሳዉ እያዳላ ሌሎቹን በእኩል ዓይን እና በልበ ርሕሩህ አልተመለከታቸዉም። በዚህ ምክንያት ከሌሎቹ ይልቅ በተለያዩ-ጠቀሜታዎች/የማሕደረ ትምሕርት (ስኮላርሺፕ) ዕድሎችና እንደዚሁም ልማትም ጨምሮ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ ሆኗል። የሚለዉን አቋማችን ገብሩ አስራት (ወያኔዎች እና ተከታዮቻቸዉ) እና በጠቅላላዉም የወያኔ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጭምር “ከ.. እስ..ከ በሙሉ” ክርክራችንን ተቃዉመዉታል።
የመንግሥት ሥልጣን ተጠቅሞ ለቤተስብ እና ለብሔሩ ሲያዳላ የተገኘ ባለ ስልጣን ወንጀል በመሆኑ ለወደፊቱ በሕግ ፊት እንደሚያስቀጣ ያዉቃል እና አልተደረገለትም ብለዉ ወያኔዎች ቢከራከሩ የሚአስገርም አይደለም። የሚያስገርመዉ ግን “ተቃዋሚዎች” የተባሉት በዚህ ረገድ ከወያኔዎች ጋር መስማማታቸዉ እና ሲከላከሉላቸዉ ማድመጥ ለምን ተብሎ አንደሆነ ትንሽ ይገርመኛል።ገብሩ ‘’ከአማራ፤ ከኦሮሞ፤ከአፋር ከአደሬ…..ወዘተ የወያኔ ባለሞያዎችና አሽቃባጮቻቸዉ ሃበታም ሆነዋል..ወዘተ፡ ነገር ግን እነዚህ ወገኖች ትግራይን ለመጥቀም ተነስተዋል ወይም እየጠቀሙ ነዉ ብሎ በአድልዎ መክሰስ ልክ አይደለም። በማለት የተደረጉት ልማቶች ከሌሎቹ አካባቢዎች ምሳሌ እያመጣ ሊከላከል ተደምጧል።
ካፍንጫ የማይርቅ የገብሩ አስራት እነ መለስ ዜናዊ፤ጸጋይ-በርሄ፤ቴድሮስ ሐጎስ፤ስብሐት ነጋ ወዘተ በልማት በኩል ለትግራይ የጠቀሙት ነገር የለም፡ አድለዎ አላደረጉም ይለናል። የነሱ ተከላካይ መሆኑን ወደ ጎን እንተወዉና፤ ወደ ራሱ ወደ 10 ዓመቱ ዘመን እሱ የሚያዉቀዉ የአድልዎ ዘመን ላንዳፍታ እንጓዝ እና ራሱን አንዲከላከል እንጠይቀዉ።
ከዚያ በፊት ግን አንድ ልበላችሁ።“ትግራይ ኢንዱሰትሪ ቢተከል እኔ ችግር የለብኝም፤ ሌለዉም -“ክልል”-አብሮ ይጠቀማል ማለት ነዉ”- የሚለዉ የገብሩ እና መላዉ የወያኔ ተከታዮች አነጋገር ሳትረሱ ወደ ሰፊዉ ክርክር በሗላ ስለምመለስበት በልቦናችሁ ያዙት። የትግራይ ተወላጆች በለስ ቀንቷቸዉ በብረት መንግሥታዊ ሥልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በላይ ያገኙትን ሥልጣን መከታ አድረገዉ ለጎሳቸዉ ለትግራይ ክፍለሀገር ኗሪ በተለያዪ መንገዶች ጠቀመዉታል እና አድገናል ካሉ አብረን አላደግንም። በሚሉ እና “የለም አልጠቀሙትም” ከሌሎቹ ጋር በዕኩል ይመለከቱታል፤ልየ ትኩረት አልሰጡትም”። በሚሉ አቋሞች የጠራ ክርክር አስካሁን ድረስ አልተደረገ የሚል።ያልተደረገበት ምክንያትም “ፈራ -ተባ” የሚለዉ ተቃዋሚዉም “ተጠቅሟል ብንል የትግራይ ሕዝብ ሊቀየምን፤ሊነጥለን ነዉ፤ ደጋፊ አናገኝም” እያለ አንደሚዋቃዥቅ ጥርጥር የለኝም።
ወይንም በትግራይ ክፍለሃገር ተወላጆች የመካራከሪያ “ሦስት” መካራከሪያ ነጥቦቻቸዉ። (1)“ይህንን ካልን ለወደፊቱ ህዝባችንን ለጥቃት እናጋልጠዋለን” (2)ይህችን ካልን ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ ሊያሳጣን ነዉ።ለነፍጠኞቹ ቂም አጋልጠዉ ሰጥተዉ ለወደፊት ጥቃት እያጋለጡሁ ነዉ ወዘተ.. እያለ የትግረይን ሕዝብ ድጋፍ ሊያሳጣን ነዉ” (3) የፈለገዉ ቢጠቅመዉም፡ልጆቹን ገብሮ በደሙ ደርግን ገርስሶ ለሌሎቹ “ነፃነት ስላመጣለት” ቢደረግለትም ይገባዋል! ማን በሞተልት ሊጠቀም ነዉ? የሚሉ አሉ። የታቃዋሚዎቹም ሆነ የወያኔ ወይም ወያኔ ያልሆኑ የትግራይ ሰዎች አልተጠቀመም የሚለዉ አቋምና፤ “የራሰው ምታት ይዞህ አስፕሪን እንኳ እንደልብ የማይገኝበት የነበረዉ አካባቢ ትልቁ የአፍሪቃ የመድሃኒት -ፋርማሲ የሚቀመምበት ቦታ ሲያቋቁሙለት አንዴት ሲሆን አልተጠቀመም ይባላል? የሚሉ በተቃራኒ የቆሙ የዜጎች እሮሮ ”ከተደመጠ ወደ16 ዓመታት ሆኖታል። ይህ እሮሮ በከንቱ ለይስሙላ የመጣ እሮሮ አይደለም። ዕሮሮዉ እዉነታን ይዞ ቆሟል።
ክርክሩ ይፋ እንዳይሆን መከላከያዉ አጥር ብዙ ነዉ። በ10 ዓመቱ የገብሩ ዘመን ኢትዮጵያ የምትባል ምድር ከትግራይ ክፍለሃገር አካባቢ በዕኩል እያደገ ነበር? ለሚል ጠያቂ- በእኛ በኩል አላደገም፡ አድሎዎ ተደርጓል ብለናል። አድልዎ የሚፈጽመዉ የትግራይ ህዝብ ሳይሆን ያ በወያኔ ትግራይ ስም ስልጣን የያዘ የዓድዋዉ ቡድን እና የዮሐንስን እና የአሉላን ኢትዮጵአዊ መንፈስና ያስረከቡንን ድመበር ንቀዉ እና አጥላልተዉ ለግማሽ ዓድዋ እና ለግማሽ ኤርትራዊ ትዉልድ ላላቸዉ ጥቂት ድርጅቱን በበላይንት ለሚመሩ አፈጮሌዎችና አታላዮች ጭራቸዉ በመቁላት በተለይም ለከርሳቸዉ ያደሩ፤ ከእንደርታ እና ከራያ-ዓዘቦ፤ከዓጋሜ፤ከተምቤን ከሽሬ’ ከአክሱም ሁለት አዉላዕሎ…ወዘተ…. የተዉጣጡ ጥቂት “ጭራቸዉን የሚቆሉላቸዉ ዉሾቻቸዉ” ወገንተኞች እንጂ ሕዘቡ ዘርፈህ አብላኝ ብሎ ትዕዛዝ አላስተላለፈም እና በሃላፊነት የሚጠየቅበት መንገድ የለም።
ይህነን ስንል የትግራይ ሕዝብ እንዳለ በሞላ ተጠቅሟል ወይም የፍሬዉ ተቋዳሽ ሆኗል ማለት አይደለም። በሌላ አነጋገር ትግራይ ዉስጥ የተቸገሩ የሉም ማለት አይደለም። በሺዎቹ አሉ። ነገር ግን፤ከሌላዉ ሲነጻጸር በፍጹም የማይታለም ነዉ (ሪፖርቱን ማንበብ ነዉ)። አዲስ አበባ ዉስጥ ከትግራይ የመጣ ሰዉ በልመና ተሰማርቶ እየለመነ አገኘሁት ብሎ በጥቆማ ለትግራይ የመልሶ ማቋቋም ድርጅት ባለስልጣኖች ወይም ለሚመለከተዉ ማንም የትግራይ ነክ ቅርንቻፍ ለጠቆመ ጠቋሚ ለእያንዳነዱ ጥቆማ $1000 ብር ፤ ከትግራይ የመጡ 20 ለማኞች ከጠቆመ 1000x20= $20.000 ሃያ ሺህ ብር ሽልማት/ጉርሻ ይሰጠዋል። እንክብካቤዉ እና ለጎሳዉ መስገብገቡ አስከዚህ መጥቋል መለቴ ነዉ(ምንጭ “ገዛ ተጋሩ ፓል ቶክ” እያሉ የሚጠሩት “ ወገባቸዉን አለጥልጠዉ አመቻችተዉ በወያኔ ለመገዛት የተዘጋጁ አዳዲስ ምስኪኖች እና በማህደረ- ትምህርት ለትምህርት ወደ ዉጭ የላካቸዉ የድሮ ታጋዮቹንም ጭምር ያካተተ የጎሰኝነት ትኩሳታቸዉ የሚለቅቁበት የፓል ቶክ መድረክ በእንግዳነት የመልሶ ማቋቋም ባለስልጣኖች ለቃለ መጠይቅ አቅርበዋቸዉ ከተናገሩት “አይጋፎረም” ላይ የተለጠፈ የድምጽ ማሕደር (አዉዲዮ)።
ይህ ለአንድ ጥቆማ 1000 ሺህ ብር የሚከፈለዉ ከትግራይ ለመጣ ለማኝ የሚጠቁም እንጂ ከወለጋ ወይም ከጎጃም፤ወሎ፤ጎንደር ወይም ከሐረር ወዘተ… ለመጣ ለማኝን የሚጠቁም ጠቋሚ ሰዉ አይመለከትም። (እያዳመጣችሁን ነዉ?!)
ልቀጥል። እንግዲህ ከላይ የተባበልነዉን ለማስታወስ ያህል፤ በአድልዎ የመጠየቀዉ ድርጅቱን እና ስርዓቱን የሚመሩ አድልዎ ፈጻሚዎቹ ብቻ ናቸዉ እያልን ስንጠቁም፡ ቡድኑ ራሱን ላለማጋለጥ እና የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሲል እንዲሁም አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆችም “ሕዝባችን ሳይበላ በልቷል-ተጠቃሚ ነዉ እያሉ፡ ለጥቃት እያጋለጡት ነዉ።” እያሉ የተገላቢጦሽ እኛኑን ተመልሰዉ ይከሱናል።አድልዎ አልተፈጸመም ዕኩል እያደጉ ናቸዉ ብለዉ ከሌሎቹ ክፍላተ ሀገሮች የሚከራከሩበት የልማት ማወዳደርያ ሰነድ ግን አስከዚችዉ ደቀቃ ድረስ አላቀረቡልንም! እናቅርብ እንኳ ቢሉም ከየት ይመጣል! አያቀርቡም።እነ ጌታቸዉ ረዳ እና ጥቂት ኢትዮጵያዉያን “ተከሳሹ” “የትግራይ ህዝብ ነዉ” ብለዋል፤ህዝበችን ሊያጋልቱት እየሞከሩ ነዉ ወዘተ… በማለት የማምለጫ እና አምታች ዘዴያቸዉን በመጠቀም ነገሩን ሲያጠ’ሙ እና ወንጀላቸዉን ወደ ህዝቡ በመጣል ራሳቸዉን ለመከላከል ይጥራሉ። ጮክ ብለዉ ያለ ሐፍረት ስለሚናገሩ እና ስለሚጽፉ አንዳንድ ኢትዮጵአዊያን እንዲያፈገፍጉ ሆኖ፤ ደፍረዉ ላለመናገር ምራቃቸዉ ዋጥ ስለሚያደርጉ፡ዘዴአቸዉ ለጊዜዉም ቢሆን አድማጭ ሳያገኙ አልቀሩም። አንድ እንኳ ሳይቀር ተቃዋሚ የሚባል በሞላ -“ኢሕአፓ”ም ጨምሮ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም ፤ህወሓት በዚህ በኩል ወገንተኝነት አላሳየም ቢሉንም፡ ሀቁ የኮሶን ያህል ምርሬት ቢመርም፤ ዕዉነታዉ መድፈን አይቻልም እና “የትግራይ ህዝብ ጠላቶች” ተብለን በወያኔ እና በጭራ ቆሊዎቻቸዉ ዉንጀላ አንደበት ከተፈረጅነዉ ከእኛዉ በኩል የምናቀርበዉ መራራዉ ሀቅ አብረን ይሄዉ እናንብበዉ። ለዛሬ መረጃየ በወቅቱ ከሌሎች አካባቢዎች ለማነጻጸር በእስታትስቲክ የተደገፈዉን ኣእላፍ መረጃ ወደ ሌላ ቀን አቆይቼ- ላጠቃላይ ለክርክር አጋዥ አንዲሆን ጦቢያ መጽሄት ላይ በ1992 (መጋቢት) ላይ የታተመዉ “አብረን እያደግን አይደለም-የብሔራዊ ራእይ ተሸካሚ አልሆኑም” የሚለዉን የጦቢያዉ አምደኛዉ አቶ ጸጋዮ ገብረመድህን አርአያን ይህ ክርክር አስመልክቶ ያተቱትን መለስ ብለን እንቃኝ እና ግምገማዉ ለናንተዉ ሳስተላልፍ ሃቁ ይሄ አይደለም የሚል ሰዉ ካለም የክርክሩ መድረክ ክፍት ነዉ። “ግብዣየ እነሆ”። ከናንተ ለመስማት እጠባበቃለሁ። ጹሁፉ ላይ ብዙ ቁም ነገሮች ታትተዋል-፡ ቢሆንም ረዢም በመሆኑ አንዳንዱን ዘልያቸዋለሁ። እንደሚረዳችሁም ተስፋ አለኝ። ተተከሉ የተባሉት የምርት ዕድገቶች (የአገሪቱ ታለላቅ/ከፍታኛ/ተወዳዳሪ የሌላቸዉ/ዋናዉ አከፋፋይ ቀማሚ/ሰሪ/ መጋቢ…..የሚባሉትን ቃላቶችን ነዉ እንድታተኩሩባቸዉ የማሳስበዉ።) እላይ የተመለከቱት ቃላቶች የፋብሪካዉ/የምርቱ ጉልበት እና ጥራትን ስለሚጠቁሙ፡ እነኚህ ዋሳኝንነታቸዉ በሌሎቹ ክፍለ ሃገሮች ተተከሉ ከሚባሉት ጋር ትይዩ ለማወዳደርም ሆነ ለማነጻጸር ስለሚረዳ ነዉ። ከባዶ/ከምርት አልባነት ተነስቶ በ5 ዓመት ዉስጥ “ትልቁ/ዋናዉ” አካፋፋይ ወደ መባል ተቀይሮ -ሌላዉ ክፍል ግን “ተቀባይ” “ቸርቻሪ” “ገዢ”… ወደ መሆን የታለመዉ ዕድገት ከአድልዎ ሌላ ቃላት መጠቀም ያስቸግራልና ክርክራችን በዚሁ እንየዉ።
ልጥቀስ፦“ ….አንድ የደቡብ አሜሪካ ጸሃፊ “የምናልም መሆናችንን ስናልም የንቃቱ ዘመን ደረሰ ማለት ነዉ።” ይላል። ለቋንቋዉ ዉበትና ለአነጋገሩ ዘይቤ ሲባል በእንግሊዝኛዉ ባቀርበዉ ምናልባት ይትበሐሉን ከነለዛዉ (nuance) ለመጨበጥ ትችሉ ይሆናል። “when we dream we are dreaming, the moment of awakkenin is at hand…” ይላል Novails.
በእጄ አንድ መጽሃፍ አለ። በቀለም ያበደ፤በጥንቃቄ የተደጎሰ፤አገር ለመገንባት የወጡ ብዙ የተማሩ ሰዎች በየገጹ ተደርድረዉ በፈገግታ የሚታዩበት የክልሉ መልክአ-ምድር አረንጓዴ ምንጣፍ የለበሰ የሚመስልበት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያ ክልል ስዊት ዘርላንድን ዴንማርክን፤ኔዘርላንድን ወዘተ፤ወዘተ የሚያስተካክል የሆነበት ነዉ። በሕትመቱ ዓለም ዉስጥ መጠነኛ ሚና ስለነበረን ያነን መጽሀፍ (160 ገጽ) በአሥር ሺህ ቅጂ ለማሳተም እንኳ (በዉጭ አገር ነዉ የታተመዉ) ከመቶ ሺህ ብር በላይ በላይ ይጠይቃል። ስለቅርጹ ትተን መጽሄቱ ስላካተተዉ ይዘት በጨረፍታ እንመልከት። · 1176 ፕሮጆክቶች ተግባራዊ ሆነዋል፤ · በ806 መንደሮች የሚገኝ 1.7 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ ሆናል። ይኸ በመጽሄቱ ሽፋን ላይ ወልል ብሎ የሚታይ ነዉ።በእንግሊዝኛዉም Implimented 1176 projects in 806 vilages benefiting over 1.7 milion people ይላል። · በኢትዮጵያ ትልቁ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ · በኢትዮጵያ ትልቁ የሲሜንቶ ፋብሪካ · በኢትዮጵያ ትልቁ የትምህርት እንቅስቃሴ ማዕከል ·በኢትዮ ከፍተኛዉ የጤና አጠባበቅ ዘመቻ የሚካሄድበትና ታላላቅ
መሰረቶች የተጣሉበት፤ ·በኢትዮጵያ ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ የንግድ የኮንስትራክሽን የማስታወቂያ የባህል የአመራር ማሰልጠኛ ወዘተ ተቋሞች ባለቤት የሆኑ መሪዎችና ደርጅቶቻቸዉ የዳበሩት፡ · ምረምር እና ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ የሚያካሄድበት · ኤች አይ ቪ( ኤይድስ-ን የሚያስከትል ቫይረስ)መከላከያ (ፕሮፊላክቲክስና) ጥናት በሰፊዉ የሚጠናበት · ዬዩኒቨርሲቲዎች እና የሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች መሰረት የተጣለበት (በነገራችን ያ መሰረት ዛሬ(2001ዓ.ም) ትግራይ ዉስጥ የሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ ተጠናቆ በሰዉ እና በአጋዥ ቁሳቁሶች ተሟልተዉ በሥራ ላይ ያሉ እና ሦስተኛዉ አዲግራት ላይ በመከናወን ላይ የሚገኝ ያገሪቱን የትምሕርት ተቋማት የሚያስንቁ ተሰርተዋል። - ኤርትራ እንደ አገር የምትጠራዋ ባለ ሁለት ወደቧ ምጥጢዋ ኤርትራም እንኳ 1ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነዉ ያላት። (በሃጽሮት የተመለከቱት -የኔ-‘ጌታቸዉ’)። · እንደ ወባ መከላከያ ያሉት ከነድርጅታቸዉ ከመሃል ተወስደዉና ጠንክረዉ የሚሰራባቸዉ፤ · ከረሃብ ጋር የተለያየ ክልል እንደ እግዚአብሐር ሳይሆን እንደ እቅዱ!! ስለሆነም አያሌ ታለላቅ ሪቆች (የእህል ዘመናዊ ማከማቻዎች) የተሰሩበት · ለወደፊቱ አገዛዝ መቀጠል ዋስትና ያገኝ ዘንድ የክልሉ ወጣቶች በአገር ዉስጥና በዉጭ ጭምር የአመራር ኮርስ (leadership course) የሚያገኙበት ለሚቀጥሉት አንድ ሺህ ኣመታት (ሚሌኒየም) የአገዛዙ ስርአት የሚሞከርበት ወዘተ፤ ወዘተ ትርዒት በትግራይ ይታያል።
“እንግዲህ…” ይላሉ አምደኛዉ፦ “እነዚህ ከላይ በጥቅልና በናሙና መልክ ያቀረብኳቸዉን ወቅታዊ ጉዳዮች በሌላዉ ኢትዮጵያ ካለዉ ነባራዊ ሁታ ጋር ካስተያየን፤ ስዕሉ ይህን አገር አይወክልም። ማወዳደር ማነጻጸር የተለያየ ትርጉም አላቸዉ። የትግራይን የግንባታ ልማትና የእድገት እንቅስቃሴ በሌላዉ ኢትዮጵየያ ካለዉ ጋር ማወዳደር ማለት በመሰረቱ በሌላ ኢትዮጵያ የልማት እመርታ የእድገት ሰፊ መድረክ አለ ወይም ተጀምሯል ብሎ ማመን ይመስላል።
ማነጻጸር ከሆነ ግን ያለዉ እና የሌለዉን የተተኮረበትን እና የተረሳዉን የተወደደደዉንና ተናቀዉን ጎን ለጎን ማቅረብ ማለት ነዉ። እንግዲህ እንደሚከተለዉ ላስረዳ። እነዚህ የትግራይ ጥጋብ ዘመናት ፤ በሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል ስምንት ሚሊዮን ሕዝብ በድርቅና በረሃብ ይጠበሳል። የስምንትኛዉ ሺህ ተአምር ሆነና አድአ ሲዳሞ፤ጎጃም እየተራቡ በትግራይ ገበያዉ ጠግቦ እህል ጥንቡን ጥሎ ቢያድር አይገርመኝም። በትግራይ አንደ ኤች አይ ቪ ያሉ በሽታዎች በጥራት ለማጥናትና ለመከላከል ከፍተኛ ሙከራ እየተደረገ ሲሆን በሌላዉ ኢትዮጵያ ግን አስታትስቲኮች እንደሚነግሩን በቀን በመቶዎች ሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ መቅሰፍታዊ በሽታ ያልቀሉ። በዚያን ሰሞን በአንድ ጋዜጣ ላይ እንደቀረበዉ በወባ ተዉሳክ የተነደፈዉ ሕዝብ በሚሊዮኖች ይቆጠራል። ይኸም ቢሆን ከሕዝብ ተደብቆ መቆየቱ ለ አንዱ ክፍል የሚታሰበዉን ያህል ሌላዉ ደንታ ቢስነትን የሚያሳይ መሆኑን አያጠራጠርም። ለመሆኑስ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልክ ተቋቁሞ ከመከላከል ወደ ማጥፋት ደረጃ ተሸጋግሮ የነበረዉ የወባ ማጥፊያ ድርጅት የፈረሰዉ ለምንድ ነዉ? የትግራይ ሕዝብ የኢትዮያ ሕዝብ እንደመሆኑ ሁሉ ጎንደሬዉ፤ከምባታዉ ወሎየዉ ሸዌዉ…ከፍቾዉ፤ ወለጌዉ፤ወዘተም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ። ከቶ ለአንዱ ክፍል እልቂት ለሌላዉ ድሎትና ሕይወት የታቀደለት ለምንድነዉ? የዚህ ሥርዓት መሓንዲሶች ወደፊት የታሪክ ፍርድ ይጠብቃቸዋል ተብለዉ በቀጠሮ የሚታለፍና ለእግዚአብሔርም ፍርድ የሚቆዩ አይደሉም። እንዲህ ያለዉ ተግባር በራሳቸዉ ቋንቋ ሲገለጥ በሰዉ ዘር ላይ የሚፈጸም ከባድ ወንጀል ነዉ። ከዚያ በታች ሊወርድ አይችልም። ….በዚህ አንጻር ሀብታሙን እያደኸየ ራሱን የሚያበለጽግ የፖለቲካ ድርጅት፤አሸንፌአለሁና ሁሉም የኔ ነዉ የሚል የፖለቲካ ተቋም ተቀዳጅተናል። ወያኔ ኢሕአዴግ! ይህ ተቋም ገና በትግራይ፤በወሎ በጎንደርና በጎጃም በአማጺነት ሲንቀሳቀስ በእጁ የገባዉን የመንግሥት ንብረት፤ድርጀት ፤ወዘተ፤በመዉረስ ሥልጣን ከያዘ በሗላ ደግሞ ያንኑ መልሶ ለቀድሞ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ሊያከራይና ሲሸጥ መቆየቱን እናስታዉሳለን። የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴና የክለል ኮሚቴዎች ድርጅቶች እንዳሉ ወደ ኢሕአዴግ ንብረትነት የሚዛወሩበት፤የተወረሱ የማምረቻና የማከፋፈያ ድርጅቶች ዕለቱን ወደ ተቋሙ ንብረትነት የሚሸጋገሩበት ሁኔታ ኢሕአዴግ መጥቶ ሒያጅ ወይም ለኢትዮጵያዉያንና ለኢትዮጵያ ባይተዋር መሆኑን ይፈነጥቃል። ከዚህ በላይ በሌሎች ክፍላተ ሀገር ሰዎች ጥሪታቸዉን አጋብተዉ ተስፋ ያላቸዉ የልማት ፕሮጀክቶች ለማቋቋም የነበራቸዉ ሕልም መና ሆኖ የቀረቡትን ሁኔታ አንድ ሁለት ብሎ በማስረጃነት ማንሳት ይችላል። በ1985 በአፋር ክልል (ክልል ሁለት) ብቻ አልመሽን ጨምሮ አሥራ አንድ ታለላቅ ሐዲዶች (በእርሻ ኮንሴሽኖች) በልዩ ልዩ ሥልት ተዳክመዉ መዘጋታቸዉን በትካዜ እናስታዉሳለን። በደርግ ጊዜ ከአዲስ አበባ አስከ ባሕር ዳር ድረስ መሬቱን ደን ለማልበስ “አዲስ ባህ” የሚባል ታላቅ ፕሮጀክት እንደነበርም አይዘነጋም። የዓለም ባንክ በ400.000.000 ዶላር (አራት መቶ ሚሊዮን ዶላር) ሊደግፈዉ የተስማማበት ይህ የልማት እቅድ ለመን ተሰረዘ? …..ነገሩን የአዲስ ዘመን ጋዜጠኛ ጨርሶት ነበር። በ1983 መጨረሻ (1984) መግቢያ አካባቢ) የወጣች አንዲት ግጥም የወያኔን ተልእኮ (ብሉ ፕሪንት) አሸጋግራ በማየት “ትግራይ አስክትለማ፤ሌላዉ አገር ይድማ!) ብላ ነበር።አስቆጣች! አስቆጣች! ሓቁና ጉዱ እያደር እንደ ጅራት የማይደበቅ ሆነና እነሆ ትግራይ፤ እነሆ ሌላዉ አገር!
ትግራይ ለምን ለማች ብሎ የሚያኮርፍና በንዴትም የሚንጨረጨር ሰዉ የለም። የሌሎች የኢትጵያ ክፍሎች (ክልሎች ነዉ የሚሉት?) ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ነዉ አጠያያቂዉ ጉዳይ! ዓይን ያለዉ እንደሚያየዉ፤ጀሮ ያለዉ እንደሚሰማዉ እና ሕሊና ያለዉም እንደሚገነዘበዉ “ፍትሃዊ ልማት የለንም”። ከአሜሪካ የተገኘ የቆየ ቃለ መጠይቅ ያለበት ቴፕ በእጄ ይገኛል።የወያኔ ኢሕአዴግ ሉስሎቭ (የርእዮተ ዓለም ሓላፊ) ጓድ ዓለምሰገድ ገብረ አምላክ “ሰላም” በተባለዉ ራዲዮናቸዉ ቃለመጠይቅ ቀርቦላቸዉ ነበር። “ኢሕአደግ ብዙ የንግድና የኢኮኖሚ ተቋሞች ማቋቋሙ ትከክክል ነዉን?” ጓድ ዓለም ሰገድ ሲመልስ “በትግል ላይ በነበርንበት ጊዜ ብዙ ንብረት አፍርተናል። ዛሬ ስልጣን ይዘናል ብለን ልንከፋፈለዉ አይገባምንም። ስለዚህ ኢንቬስት አደረግነዉ”። አሉ። ይህንን መልስ ነዉ ብሎ ያለ አይጠፋም; ይህ ገንዘብ ራሱ ከየት መጣ? እንዴት ተገኘ? በ1984 መጨረሻ ግድም ጦቢያ መጽሔት የጤና ጥበቃ ሚኒስትርዋን ዶክተር አዳነች ኪዳነ ማርያምን አነጋግሮ ነበር። “ክብርት ሚኒስትር የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ከወያኔ መድሃኒት ገዝታልና 4=7= 11 ሚሊዮን ብር ይከፈላቸዉ” የሚል ዉሳኔ ሰጥተዋል። “”ወያኔ ኢሕዴግ <ታጋይ.> ነበር እንጂ ዓለም አቀፍ የመድሃኒት ነጋዴ አይደለም። አርስዎም የገንዘብ ሚኒስቴርን ደንብ አልተከተሉም። ይህን አህል ገንዘብ ለወያኔ ለማሸከም ሥልጣን የለዎትም>> ደፋር ጥያቄ ነበር። ድፍረት ምን ማለት እንደሆነ ስላለወቅን እንጂ ተራ ጥያቄ ነበር። ዶክተር አዳነች << አሱን አንተ ነህ የምትለዉ። ልትከስሰኝ ትችላለህ!>> አሉ። ለማንኛዉም የኢሕዴግ የሃብት ምስጢር ሲነሳ ኢትዮጵያን በጠቅላላዉ መዉረሳቸዉን መግለጡ ይበቃል።
ለዚህ ሕዝብስ? ለዚህ ሕዝብማ፦ ለምሳሌ በአራዳዉ አካባቢ የሚታወቅ አንድ አፍቃሬ ወያኔ በ1983 ግንቦት ሰዎቹ ሥልጣን እንዲያዙና ያገኙትን “ሹምና ግልገል ሹም” ሁሉ ሽብ ሲያደርጉ አንድ አሳብ አቅርቦ ነበር /በቴሌቪዥን/።
“ይመስገን” ወረዳ 22 ፓሊስ ጣቢያን በማሰራት የቀረበዉ አሳብ፤- ለመሓል አገሩ ሕዝብ በርከት ያሉ እሥር ቤቶችን ማሰራትን ነበር። በእርግጥም-በመሃል፤በደቡብ፤በምዕራብ በምስራቅ ኢትዮጵያ የእስረኛዉ መበርከት ብዙ እስር ቤቶች እንዲቋቋሙ የሚገፈፋ ሆኗል። ትምርት፤ዩኒቨርሲቲዉ ፤የምርምር ጣቢያዎቹ፤ፋብሪካዎቹ፤ከማሳቹስትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲስተካክል የተፈለገዉ የመቀሌ ኢኒስቲትዩት ኦፍ ቴክኔሎጂ (MIT).. ሆስፒታሎች፤መንገዶች፤ብዙ መግለጫ ተሰጥቶላቸዋል። በግፍ የተሰሩ፤ ከኢትዮያ ሕዝብ በተቀማ ሀብት የተቋቃሙና በፍርደ ገምድልነት የተቆረቆሩ ስለሆኑ የታሪክን ፍርድ አያመልጡም ብለን ልናልፍ አይገባም። የግፍ ብድራት(poetic of justice) አጋጥሞ በመቀሌ፤በአዲግራት፤በአድዋ፤በ አክሱም፤በሽሬ፤ የተቃቋሙት የልማትና የባሕል ማዕከሎች ሻዕቢያዎች በጥቃታቸዉ ዒላማ ሊያደርጉላቸዉ ይችላሉ። በጠባብነት እና በስግብግብነት ካልሆነ በቀር፤ በስትራቴጂዉ ረገድ እንኳ በትግራይ ላይ ይህን ያህል የአገሪቱ ሀብት በዚህ ሰዓት ሊፈስስ አይገባምዉም ነበር። ከኢኮኖሚዉ ኢፍትሀሓዊነት በተጨማሪ የሰላም ኪሳራነትና ከላይና ከታች ተቃዉሞ ያለበት ነዉና። በጠቅላላዉም ተግባሩ ራሱ ይሉኝታ ያልታየበት፤የሕዝብን አስተያየት ከመጠፍ ለመቁጠር ያልተፈለገበት ነዉ።
ለፈረንጆችም ቢሆን ንጽጽሩ አሳፋሪ እዉነታ በመሆኑ ከእኛ ይልቅ የበለጠ እነሱ ይበልጥ ይነጋገሩበት ጀምረዋል። ለትግራይ የትግል ፍጻሜ ሆነና ለትግራይ ዲሞክራሲ የታገሉ ወያኔዎች ናቸዉ ተባለና በ አያሌ ሚሊዮን ብር በሃወልት ስም የድንጋይ ካብ ይታነጻል። በሚሊዮን በሚቆጠር ብር የተጠናም ሆነ ያልተጠና (ወይም ለማዕከል ተብሎ የተጠና ፕሮጀክት) የልማት ዕቅድ ይዘረጋል። በፍጥነት ወደ ፈረንጅ ኣዕምሮ የሚመጣዉ ንጽጽር <<በፍጥነት ለ8 ሚሊዮን የኢትየጵያ ረሃብተኛ በ860,000 ቶን እህል ያስፈልጋል>> የሚለዉ ነዉ። << በፍጥነት መቶ ሺህ ቶን መድሃኒት መድረስ አለበት>> የሚለዉ እርዳታ ሰጭ በተባሉት በ አሜሪካኖች፤በካናዳዊያን ባዉሮፓዉያን መንግሥታት ተወካዮች ጀሮ ዉስጥ ይይጮሃል። የኢትዮጵያ ገዢዎች መሰሎቻቸዉን ሰብስበዉ በመቀሌ ግብር ሲያስገቡ ፤መጠጡ ሲረጭ፤ዲስኩሩ ሲገጠገጥ ኢትዮጵያ እሳት እየበላት ነበር። ባሌ፤ኤሊባቡር፤ኦጋዴን፤ሲዳሞ፤ ባለቅኔ ሲራቀቅበት፤ፋኖ ወገቡን አጥብቆ በጓደኝነት “ጥራኝ-ጥራኝ ጥራኝ….ደኑ > ሲልለት የኖረዉ ደን እየነደደለት ነበር። አገር ነድዶ ነድዶ ሌላ የሚነድድ ወደ መጥፋቱ ገደማ የመጣፊያ ባለስልጣኖች ሰምተናል። <<አዲስ አበባም እኮ ወያኔ በገባ በሳምንቱ-ግንቦት 27-1983 ነድዳ ነበር። አሁን ተረኛዉ ደኑ ሆነ እንጂ!>> ታዲያ ይህ የአስረሽ ሚቺዉ ከረሃባችን ከሕመማችን አብሮ ይሄዳልን?
ከእነዚህ የኢትዮጵያ ገዢዎችና አጋፋሪዎቻቸዉ ጋር አብረን የ ኢትዮጵያን መካራ እየቀመስን አይደለም። አብረንም እያደግን አይደለም። የነደደዉ የደቡብና የምዕራቡ ደን ከፍተኛ ቃጠሎ፤ ንብረትና የሕይወት አደጋ የደረሰበት የዚያች አገር ክፍል በትግራይ ዉስጥ ቢሆን ኖሮ ምን እናደርግ ነበር ምን እንሆን፤ምን እንታዘዝ እንደነበር አገምታለሁ። ኒሮ እና ኮላዉዲዮስ ተባሉ የሮማ ቄሳሮችን የሚያስታዉስ ድርጊት በአሳፋሪ ተዉኔት መልክ እየተከሰተ ነዉ። ልሰማዉ የማልወድደዉና ለግንዛቤዮ እንደ ስድብ ይቆጠራል ብየ የምጠላዉ የሰዎቹ ክርክር <<ትግራይ ልማት በራስ አገዝ መልክ የተቀየሰ ነዉ>> የሚለዉ ነዉ። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፤ከኢትዮጵያ ኪሶች የተገኙ የወያኔ የንግድና የኢኮኖሚ ተቋሞች፤ ወፋፍራም ደመወዝ የተቆጠረላቸዉ የወያኔ-ባለሥልታኖች ለመንዝ ነዉ ወይስ ለወለጋ? ለከንባታ ነዉ ወይስ ለጋሞጎፋ? ሌላም እኮ አሳዛኝ ድርጊት አለ። አሜሪካኖች ራሳቸዉ ያወጡት ሪፖርት እንደሚያስረዳዉ USAAID በየዓመቱ ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የእህል እርዳታ ወደዚህች አገር ይልካል። USAID እና Michigan State University በጋራ ባወጡት የአቋም ሰነድ መሠረት ከሚላከዉ መካከል ስድሳ-ከመቶዉ ወደ ትግራይ ይሄዳል። እሱም ቢሆን በቁሙ ሦስት ጊዜ ይሸጣል (ለ አዉሮፓ ሕብረት፤ምናልባት ለካናዳ ምናልባትም ለጃፓን፤ወዘተ)። ይኸም ማለት <<እህሉ ስላለን ገንዘቡን ብቻ ላኩ>> በሚል ነዉ። ይኸ የሚያኮራ አይደለም። ሌብነት ነዉ ለማለት ደግሞ ድፍረትን ይጠይቃል። ባጠቃላይ ለመናገር ከመነሻዉ ጀምሮ በሕዝቡና በዚህ ሥርዓት መካካል መተማመመንና ልብ ለልብ መፈቃቀድ ባይኖርም በሂደት ደግሞ ርቀቱ እየሰፋ ይሄዳል። አረጋዊ በርሄ ጥሩ ይከራከራል፤ ወ ያኔን ከራሷ የበለጠ ያዉቃታል። ይሁንና ከአረጋዊ ጋር የማልጋባበዉ "ለትግራይ አንድም ነገር አልተደረገላትም" በሚለዉ ሀሳብ ነዉ። ቁሳዊ መሰረቱ በመጣልና በመሳሰለዉ ረገድ ግን ከማንም ኢትዮጵያዊ ይልቅ የፈረንጅ ነቃሽ ለማምጣት ይቻላል። ከአረጋዊ ይልቁንስ “ስብሐት ነጋ” የተባሉት ከወያኔ ግንባር ቀደምቶች አንደኛዉ ለሪፖረተር መጽሔት የሰጡት መግለጫ አይናችንን ትክ ብለዉ እየተመለከቱ የሚያፌዙብን ይመስላቸዋል።
ከተባለዉ መጽሔት ቅጽ 3 ቁጥረ 24 የሚከተለዉን ልጠቅስላችሁ እፈልጋለሁ። “ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይቶት በሕይወቱ ፤ በታሪኩ የማያዉቅ የልማት ጎዳና ተዘርግቷል። የልማት እንቅስቃሴም ጀምሮአል።ምንም እንኳ በሚገባዉ መጠን ባይሆንም ተጀምሯል። ትግራይ ደግሞ እንደማንኛዉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፓርላማ፤መንግሥት የመደበለትን በጀት መሰረተ ልማት እያፋጠነበት-ነዉ።…ትግራይ የተሰጣቸዉ በጀት በብቃት ስራ ላይ ከሚያዉሉት ክፍሎች አንዱ ነዉ።… የሲሚንቶ ፋብሪካም ቢሆን የሀገር ሲሚንቶ ነዉ። ጨርቃ ጨርቁም የሀገር ጨርቃጨርቅ ነዉ። ምርቱ ሁሉ የሀገር ምርት ነዉ። ባሕር ዳር ይሰራ ትግራይ የሀገር ምርት ነዉ":: ይላሉ።
ለትግራይ የተደረገዉ ሁሉ ለመላዉ ኢትዮጵያ እንደተደረገ ቁጠሩት እያሉን ነዉ። በዚያዉ ልክ በትግራይ ላይ የፈሰሰዉን ሁሉ እየካዱ ናቸዉ፡ ዓይን አዉጣ አትበሉት። ሰዉየዉን የልብ ዉፋሬ ከይሉኝታ መሰናበት የሃላፊነትን የሐፍረትን የመጨረሻ ድንበር መጣስን ያመለክታል። ንግገራቸዉ አለላለቀም << ስለሌላዉ አያገባኝም። የተነሳነዉም ለትግራይ እንጂ ለሌላዉ አለመሆኑ ይታወቅ>> የሚለዉ ዓረፍተ ነገር ቢጨመርበት ከአስመሰላቸዉ ሎጂክ ርቆ አይሄድም ባይ ነኝ። (እኔም -“ጌታቸዉ ረዳ”- አዚህ አንድ ነገር ልጨምር።ሗላ እንመለስበታለን ብየ ከመግቢያዉ ጽሁፌ ላይ የተዉኩትን -ይህነን የገብሩ አስራት ንግግርም ባለፈዉ አድምጣችሁታል። እሱ ያለንም ልክ የስብሐት ነጋ ንግግር ነዉ። ተቋቁመዋል የተባሉት የልማት ድርጅቶች የትግራይ ሕዝብ ቢጠቀምበት ችግር የለኝም! (ለንግግሩ ጭብጨባ ተለግሶለታል) ትግራይ ዉስጥ የተቋቋሙት ልማቶች ለሌሎቹም ስለሚጠቅም ትግራይ ዉስጥ ቢቋቋም ልዩነት ተደረገ አያሰኝም”።ብሎ ነበር።ለትግራይ የተደረገዉ ሁሉ ለመላዉ አገሪቱ እንደተደረገ ቁጠሩት ሲሉን ፦ገብሩም ሆነ ስብሐት፦ነፍጥ አንግበዉ ወደ ጫካ ሄደዉ “ተሓህት”ን ለመመስረት ያበቃቸዉ የክሳቸዉ መነሻ ምክንት ያደረጉት- በሌሎቹ ክፍለሀገሮች ትምህርትና ፋበሪካ ሲቃቋም/ ሲስፋፋ ለትግራይ አልተደረገለተም ነበር የክሱ ምክንያታቸዉ። ያኔ የነበሩ ተቋማት ሸዋም ሆነ ባሕር ዳር ቢመሰረት ትግራይም ስለሚጠቅም ያገሪቱ ሀብት ነዉና ለትግራይ እንደተቋቋመለት አስቡት ተብሎ መልስ ሲነገራቸዉ አልተቀበሉትም። ይልቅኑስ “ብረት አንገቦ መዋጋት እና አሁን ካለበት ሂደት መድረስ ”ነበር መልሳቸዉ!! አሳዛኙ ነገር _እነሱ ጋ ሲደረስ ትግራይ ተመሰረተዉ ልማት ለማላዉ አገሪቱ እንደተሰራ አስቡት ሊሉን ሌሎቹ ስርዓቶች በሌሎች ክፍል በገነቡበት ወቅት ግን አካባቢዉ አንጂ ለትግራይ ምኑም እይደለም ሲሉዋችሁ- የማጭበርበር እና የዉሸት የመጨረሻ ድንበር መጣስ ከዚህ ወዲያ ምን ሊኖር ይችላል?)
..ልጨምርላችሁ -
ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይም ቅድም በተጠቀሰዉ በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቀዉ ባለ 160 ገጽ (TDA) ባሳተመዉ የትግራይ ልማት ሪፓርት ላይ በመጀመሪያዉ አንቀጽ ላይ እንዲህ ይላል። "ትግራይ ለብዙ ዓመታት ከተገፉት የኢትዮጵያ ክልሎች አንደኛዉ ነዉ;። ከሚኒሊክ አስከ መንግስቱ ድረስ የነበሩት ተከታታይ መሪዎች ክልሉ እንዳይሻሻል ዓላመቸዉ አድረገዉት ቆይተዋል”። እንዲያዉም ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት ሕዝቡን በሌሎች አካባቢዎች ለማስፈር በመመሞከር ልማት እንዳይኖር አሉታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ትግራይ በየጊዜዉ በድርቅ ቢጎበኝም የሚያስከትለዉን ሁሉ ለመቋቋም ምንም እርምጃ አልተወሰደም"
ያለፉት መንግስታት በዚህ ረገድ ትግራይን ነጥለዉ አይተዉ በሕዝቡ ላይ የሕሊና ጭንቀት አድረሰዉ ከትግራይ ዘርፈዉ ሌላዉን ክልል አልምተዉ ከሆነ ኮናኒም፤ነፃ አዉጭም ሊሆኑ ታሪክ ዕድል እንስጠዉ። ታሪክ ደግሞ እንደ ጅረት ፈሳሽ ነዉና ሌላ ምዕራፍ ላይ አድርሶናል። የዛሬዉን በዓይኑ እያየ እና በእጁ እየዳሰሰ የሕሊና ዳኝነቱ የሚኮንነነዉ ሰዉ ስለ ትናንቱ ማንሳት አይገባዉም። ማመዛዘን፤ማመሰካርና ማስተዋል (reason) ጋር መጣጣም ይኖርበታል። ስለዚህ ልናቀርበዉ የምንገደደዉ መከራከሪያ ትግራይን ከሌላዉ የትዮጵያ አካላት(ክልል)ጋር ማወዳደር ይሆናል። የትግራይ መጨቆን፤ ከዕድገት ይሁነኝ ተብላ ወደ ሗላ እንድተቀር መደረግ፤ የተሰሩትን እንዲፈርሱ ወይም ያሉት እንዲዘጉ መንግታቱ (መስተዳድሮቹ) ባወጡዋቸዉ ፖሊሲዎች መወሰናቸዉ አስከተገለጠ ድረስ ሌሎቹ ክፈላተሀገር ከትግራይ ቀድመዉ ሄደዋል ማለት ይሆናል። ሸዋ ለምቷል፤ጎንደር ለምቷል፡ ወለጋ በልጽጓል፤ወሎ መንገሰተ-ሰማት መስሏል ማለት ይሆናል።ዶከተር ሰለሞን ዕንቋይ ትናንት በትግራይ ላይ በደል ተፈጽሟልና የዛሬዉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ኢፍትሓዊነት ትክክለኛ አፀፋ ነዉ ባይ ናቸዉ። ማንኛዉ ክልል ነበር ተጠቃሚ የነበረዉ? ማንኛዉ ሕዝብ ነዉ የትግራይን ህዝብና ትግራይን የበደለ? ከሆነስ የበደልን ብድራት መበቀል ያለበት በቀል እናስተካክለዋለን የሚል አቋም መያዝ ነዉ?
ያኔ ትግራይ ከባሌ፤ከኤሊባቡር፤ከወለጋ ከጎጃም፤ ከአርሲ ከሲዳሞ ከወሎ ትሻል ነበር።;… በጠቅላላዉ ግን በአመለካከትም በዕድገትም ከመንግሥት ጋር ብቻ ሳይሆን ከደጋፊዎቹም ጋር እየተራራቅን ሄደናል"።
በገብሩ አስራት ላይ እመሰክራለሁ ያለን በቀለም ያበደ በጥንቃቄ የተደጎሰዉ ታሪክ ለምስክርነት ቀጠሮ ያስያዘዉ ባለ160ዉ ገጽ የልማት መጽሐፍ አፈላልጉ እና አንብቡት። በዛ ጊዜ ሌሎቹ ክፋለተ ሀገር በምን ሁኔታ እንደ ነበሩ ሌሎች ዘገባዎችም ጨምሩበት እና አገናዘቡት። ብዙ ትገነዘባለችሁ። ከመዝጋቴ በፊት ወደ አቶ ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ መደምደሚያ አስተላልፌ ልሰናበታችሁ። በዚች አጋጣሚ እንለያይ።
"… በአንድ ትምህርተ ቤት ጥቂት የሕዝብ ልጆች በርከት ያሉ አዳዲስ የመኳንንንት ልጆች ይማራሉ አሉ። አንድ ቀን የክፍሉ መምህር <<ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት የምትፈልጉ ሁሉ አስኪ ቁሙ እና ልያችሁ?>> ሲል አነዚያ የሕዝብ ልጆች ተቀምጠዉ ቀሩ። መምህሩ አንዲቱን ተቀምጣ የቀረች ልጅ ስም ጠርቶ "አንቺ ለምንድነዉ ያልተነሳሺዉ መንግስተ-ሰማያት ለመግባት አትፈልጊም ማለት ነዉ?" ይላታል። ልጅቹ ያለምንም ድንጋጤ "እፈልጋለሁ። ግን ከእነዚህ ልጆች ጋር ለመሄድ አልፈልግም" አለችዉ አሉ። አብረን አላደግንምሕልም አልተካፈልንምአብረን የምንሄድበት ቦታ የለም።//-// ---// http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

Tuesday, October 7, 2008

ክፍል -2- የዓድዋዉ ቡድን ህወሐትን እየመራ ነዉ

Adwans are the Chiefs of the Chiefs among the TPLF ክፍል -2- የዓድዋዉ ቡድን ህወሐትን እየመራ ነዉ
ጌታቸዉ ረዳ ወደ ዋናዉ አርዕሰት ይዤአችሁ ከመሄዴ በፊት፤ በክፍል-1- (የመጨረሻዉ ሐተታየ- የግልፍተኝነት የእንካ ቴስታ…በሚለዉ) ገብሩ አስራት በተገኘበት መድረክ ተደርጎ በነበረዉ የጥያቄ እና መልስ ላይ ባለፈዉ አንስቼዉ ከነበረዉ አንድ ዋናዉ ለሐተታየ መነሻ በአንድ የትግራይ ሰዉ እና አቶ ጌታቸዉ… በተባሉ ሰዉ በአስተያየት መረዳት ላይ ያለ መግባባት እንደበረ ገልጨ ነበር። ፡አንባቢዎች በኢ-ጦማር ጽፈዉ “ዋን ሞር ታይም-“ በሚለዉ የፈረንጅ አባባል “አንዴ ደግመህ ግልጽ ብታደረገዉ?” ብለዉ ስለጠየቁኝ ያኔ ተዘንግቶ ያልጠቀስኩት የመጀመሪያ የአቶ ጌታቸዉ…. ንግግር (ጥያቄ) ዛሬ የአቶ ጌታቸዉን አባባል ቃል በቃል ምን ብለዉ ገብሩን እንደጠየቁት ልግለጽ ።
ባጭሩ ሰዉየዉ የጠየቁት <ከገዢዉ የህወሓት አመራር መሃል ዉስጥ አንቀጽ 39 ኝን እንዲቆይ የሚፈልጉት የመገንጠል ፍላጎት ያላቸዉ ስላለቸዉ ነዉ ወይ..? ብለዉ የጠየቁትን ጥያቄ፡ አስተያየቱ ለትግራይ ሕዝብ ነዉ ብሎ የተቆጣዉ አድማጭ ስሕተቱን ለማሳየት የአቶ ጌታቸዉ ሙሉዉን ጥያቄ ይሄዉ። የአቶ ጌታቸዉ… ጥያቄ ቃል በቃሉ እነሆ፦ <<…ካማራዉ እየለመነ የሚኖርበት ሁኔታ እንቀበልም፡ ስለዚህ በመገንጠልም አማራጭ የሆነዉን ኢንፍራስትራክቸር እና ሌሎች መደላድሎች አዘጋጅተን መቆየት አለብን፤ ከሕገ መንግሥቱም ዉስጥ እንቀጽ 39ኝን መቆት አለበት የሚለዉ አመለካከታቸዉ ከዚህ ነዉ ወይ የሚመነጨዉ? የዚህ ዓይነት የመገንጠል ስሜት አመለካከት ከሚመሩት ሰዎች መሃል አለ ወይ?>> የጥያቄዉ መጨረሻ። እንግዲህ ይህ ነበር የተጠየቀዉ። ይህ እንደ ጥያቄ ነዉ የቀረበዉ (ያዉም ሁሉንም አመራር አላሉም -ህወሐትን ከሚመሩ ሰዎች መሃል አለ ወይ? ነበር ጥያቄዉ። የተቆጣዉ ትግራዩ ሰዉ ምን አለ?
ልጥቀስ <<“….. ያለዉ ነገር ሰምታችሁታል? አንድ የተናገረዉ መርዝ አለ።ምንድ ነዉ ያለዉ!? አማራዉን አስከ መቸ ጊዜ ድረስ ልንለምን ነዉ ብላችሁ ልትገነጠሉ ነዉ ወይ? አለን!.. Right at our face!!! How dare!? አንዴት?... እንደዚህ እየተናገርን ነዉ መለስን ምናወረደዉ?.......... አሜሪካ ዉስጥ ያለዉ ከ-----አስ.. ከ አፍራሽ ነዉ። ሕዝብ እና መንግሥት መለየት አልቻልንም!” በወገንተንነት ስሜት ተደግፈዉ ደማቅ “ጭብጨባ”ተለገሰለት። መንግሥት እና ሕዝብ ለይቶ የቀረበ ጥያቄ መረዳት ያቃተዉ ማን ነበር?፡ መለየት ያቃተዉ ሰዉ እና ዕዉራን አጨብጫቢዎቹ ወይስ የአቶ ጌታቸዉ ጥያቄ? አስቲ ይህነን የመገንጠሉ እና የልማቱ ወገናዊነት የግንባታ ጥድፍያዉ እዉን መሆኑን አኔን ካላመናችሁ በሌሎች መረጃዎች መልክ ላቅርበላችሁ። ልጥቀስ TPLF's secret document According to information obtained in Addis Ababa by The Indian Ocean Newsletter, the Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi has written a 22 page document entitled Tigray in the new Millenium calling for a strengthening of the construction of a Tigray Regional State which is in a position to “survive on its own means if necessary”. This text was approved by Seyoum Mesfin, Abay Tsehaye and Sebhat Nega and is now circulating in the executive circles of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF, hard core of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front in power in Addis Ababa) as a confidential document. According to our sources, it lists the various infrastructure projects already completed in Tigray, laying special emphasis on the Tekezie hydro-electric dam for its role in the electrification of the country, calls for the expansion of other sectors of activity in this region in the North of Ethiopia and praises the close relations between the Tigray Regional State and China. This text also considers that the Tigrayan Diaspora abroad should be “educated and mobilized to invest” in this regional state. Finally, it stresses the need to establish close relations with certain Eritrean opponents. This theoretical assemblage is similar to the thesis in favor of creating an independent state, coupling Ethiopian Tigrayans and Christian Eritreans from the high plateaux. The idea of such a Tigray-Tigrigni State was favored two decades ago by certain Ethiopian Tigrayan and Eritrean nationalists. .ምንጭ Ethiomedia.comይችንም ጣል ላድርግላችሁ፡Addis Engineering Consulting 10,000,000; Mesfin Industral comp 500,000,000; SUR Construction 150,000,000; Star Pharmacculicals 53,000,000 Almaden Garment Factory 660,000,000 እያለ በጠቅላላ 50 እንዱስትሪዎች/ፋበሪካዎች/ኢነሹራንስ ኩባኒአዎች/የጭነት ታንክ መጠገጫ እና መለዋወቻ ዕቃዎች የሚገልጽ list of TPLF Companies established between the year 1992-1997 EC“ የሚለዉ ዘገባ አንብቡት እና በሌሎቹ ግፍለሀገራት ኢትዮጵያ ጋር የእሴቱ ክምችት ኣና የኩባንያዎቹ ብዛት እና ፍጥነት አወዳድሩት።
ወደ ሁለተኛዉ ጥያቄ ልዉስዳችሁ። ገብሩ አስራት፡ አሜሪካ አገር ነዉ ያለዉ ብያለሁ። እየተዘዋወረም ስለ ጎሳ ድርጅቱ ገለጻ እያደረገ ነዉ። በእገረ-መንገዱ በዝርፍያም በሕግም ያከማቹትን ሃብት ለሌላዉ ሳትቆጩ ልትግራይ ብቻ እያዳላችሁ ትግራይን አበልጽጋችሗል፡ የሚሉትን ክሶች ገበሩም ሆነ ባጠቃላይ የወያኔ መሪዎች እና ፡ይግረም ብሎም፤ የመለስ አብዛኛዉ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያምኑት ለትግራይ አልተደረገልትም አድልዎ አልተፈጸመም እያሉ ይከላከሉላቸዋል።ኩባኒያ ካለ ተጠቃሚዉ ከፍጆታ እና ከቀረቤታዉ ሕግ (ኢኮኖሚሰት ባልሆንም -ተራ ዕዉቀት የሚያዉቀዉ ነዉ እና…) ህዝቡ የሚሸምተዉ ጎንደር ይም ወሎ በኮሎኛ ወይም በወረፋ እየጠበቀ ሳይሆን በቀጥታ እቤቱ ደጃፍ የተተከለለትን ኢንዱስትሪዉ የሚያፈራዉን ሸቀጥ /ዉጤት ነዉ እሩቅ ሳይጓዝ ለወራት ሳይጠብቅ ሚያገኘዉ(ሓዋርያ ላይ ያቀረብኩትን ጽሁፍ አንብቡት)። ምንም ብትሉ ምንም በፍጆታ እና በቀረቤታ ሕግ የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ነዉ! መቀሌ ከተማ እያንዳንዱ የቤተሰብ መኖርያ ብታዩት (መረጃዉ እንደደረሰኝ ሳሎን ያልነበረዉ ዘመናዊ ሳሎን፤የቤት ዕቃዉ ዓይነት በጣም ንጹህ እና ዘመናዊ አንደሆነ ነዉ። የመቀሌ ሱቆቹ በሙሉ የኤሌከትሮኒክ ዕቃዎች ተገጥግጠዉበታል…የታክሲዉ ብዛት “በጃጅ” እየተባሉ የሚጠሩት (የአስመራ ልጆች-ላመብሬታ ብለዉ ሚጠሯቸዉ) የሞተር ሳይክል ታክሲዎች ከተማዉ ኣእላፍ ታክሲ መኪኖች እሽቅድድም አጣብበዉታል። ፈራ ተባ ለምንድ ነዉ ሃቅ መናገር ያስፈራል? አንወያይ!
አለማፈራቸዉ 10 ሺህ አና 20 ሺህ ዶላር ከስንት ዓመት አንዴ ከትግራይ ተወላጆች ከዚህም ከዛም የምትጠረቃቀመችዋን ገንዘብ (ኮንትርቢዩሽን- እርጥባን ) በቢልዮኖች ዶላሮች የሚንቀሳቀስ አሁን ላለዉ ሰፊ የትግራይ ልማት ዕድገት ምንጩ ከኪሳችን የተወጣጣ ነዉ፡ በማለት ወያኔዎች የደለሉዋቸዉን መሸፈኛ ቅጥፈት ተመልሰዉ ያንኑ ሞኝነታቸዉ በማስረዳት የወያኔ አድልዎ እና ዘረፋ ለመከላከል ይጥራሉ።
ይህንን በሚመለከት በክፍል -3- ከጥቂት ቀናት በሗላ ስለሚቀርብ አዚሁ አንተዉና ወደ ሁለተኛዉ የአቶ ጌታቸዉ ሌላኛዉ ስለ ዓድዋ ቡድን ስልጣን የመምራቱ ጥያቄ እነሆ፦ <<በመንግሥቱ መዋቅር ላይ በተለያዩ ሥራዎች ከአማራዉ፤ከ ኦሮሞዉ..ወዘተ ግለሰዎች በአምባሳደር ደረጃ አና ሌላ ሌላ ስልጣን ቢኖሩም ዉሳኔ የሚሰጡ እና የሚቆጣጠሩት ሰዎች የትግራይ ከትግራይም ደግሞ ከዓድዋ ምናልባትም ደግሞ የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ዲቃላዎች መሆናቸዉ አጠራጣሪ ነዉ ወይ?>>
የሚለዉ ጥያቄ አቶ ገብሩ አስራት አጣምሞ ያልተባለዉን ነገር የዓድዋ ሕዝብ ተጠቅሟል የተባለ አስመስሎ ያልሆነ መልስ ሰጥቷል። አዎን ስርዓቱን በበላይነት የሚመሩት በዋናነት የዓድዋ ልጆች ናቸዉ ላለማለት ፈርቶ “አልለማንም፤አላደግንም፤ተቸግረናል ብሎ የሚጨሆዉ ያዉም የዓድዋ ሕዝብ ነዉ። እንትጮ፤የዓዲ ዓፍሮም፤የነበለት. የገጠር ሕዘብ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል..ወዘተ…> በማለት ዝባዝንኬ አነብንቧል። የተጠየቀዉ ቀጥተኛ ጥያቄ ገብፋ በአዉራጃዊነት፤ የመቧደንና ትሸሽት የመኖሩ ለመካዱ ለመሸፈኛ ወደ ሕዝቡ አቤቱታ እያንተራሰ ላለመመለስ ሲሸሽ ተደምጧል። በበላይ የሚመሩት በዋናነት ዓድዋ ናቸዉ ። ይሄ ደግሞ አጠራጣሪ አይደለም። አቶ ገብሩ እንዴት ትመለከተዋለህ? ነዉ የተባለዉ። ይሄ ለኛ በጣም ግልጽ ነዉ።ጎጠኞች ናቸዉ። ብሎም መንደርተኞች ናቸዉ፡ ነበር የጠያቂዉ መልእክት። ገብሩ ይህ ሁኔታ ከካደዉ፤ የበረሃዉ የድሮዉ የ “አሽዓ” “ሕንፍሽፍሽ (ዓድዋ አኽሱም ሽሬ” ) አንደለመደዉ ሊክደዉ መመኮሩ ነዉ። ዶ/ር ሃይሉ መንገሻ (ሎስ አንጀለስ) እና ግርማይ ለማ (ግርማይ በህሊ)- (ችካጎ) እና ሌሎች ሺህ ታጋዮች ለሕንፍሽፍሽ መነሻዉ አዉራጃዊነት እና ጎጠኝት እንደነበረ በደምብ ያስረዱት ጉዳይ ነዉ። አሁን በገብሩ መደምደሚያ እነ ስብሐት ነጋ ከዓድዋዊ ስሜት ነጻ ናቸዉ እያለ እየሞገተን ከሆነ፤- አቶ ገብሩ ማን ነበሩ? የሚለዉ ብስራት አማረ “ከዚያ አስከ እዘህ ድረስ ያደረሰዉ መንገድ” በሐዋሪያ ጋዜጣ መመለክት ነዉ። ካስፈለገም፤ አንባቢዎች እንዳቀርብላቸዉ ከጠየቁኝ ላቀርበዉ እሞክራለሁ።
ስለዚህ ገብሩ የተጠየቀዉን ትቶ “ዓድዋዉ ቡድን ስርዓቱን እየመራ ይሆን? ለሚለዉ ጥያቄ “ ቡዱኑ ለዓድዋ ሕዝብ እየጠቀመ ነዉ እንደተባለ አስመስሎ ዉዥምብር ዉስጥ መግባቱ - ግራ አጋቢ ነዉ።መንግሥቱ ሃይለማርያም የራሱን ኮርሶች (አብረዉ ከእርሱ ጋር የተመረቁ ዋና ዋና ቁልፍ ቦታዎችንና የምስጢር ስራዎችን እንዲሁም የሚዋሹለትንም ሲመለምል እንደነበረዉ እና የሗላሗላም ሲመናመን ወይም ሲክዱት ፤ሌሎች ለሱ ተገዢ መሆኑን ሲያረጋግጥ፤ ቦታ ሰጥቷቸዉ ነበር። ልክ መንግሥቱን ከከዱት የኮርሱ ልጆች መለስም ከዓድዋዉ የከዱት እነ ዓለምሰገድ ገብረ አምላክ (የወያነ የርእዮተ-ዓለም ሃለፊ የነበረዉ) እና እነ አዉዓሎም ወልዱ/ትኩእ ወልዱ (የኤርትራ አምባሳደር የነበረዉ-በአባቱ ኤርትራዊ- አሁን ገብሩ አስራት ምክትል የዓረና ሃላፊዉ ያሉበት) ታናሽ ወንድሙ ለመለስ ዜናዊ ያደረዉ አባይ ዴራ/አባይ ወልዱ (ትግራይ ዉስጥ ከፍተኛ የህወሐት ባለ ስልጣንና የመአከላዊ ኮሚቴ አባል)። ልክ ገብሩ ዳር ዳሩን ነካ ነካ እንዳደረገዉ ከዚያም ከዚህም ስልጣን ላይ ያሉ አሉበት። ያዉም የአሉላንና የዮሐንስን ቃል የከዱ ከያካባቢዉ የተጠረቃቀሙ ሆዳሞችና ሚጢጢዎች ባለስልጣኖች የእንደርታ፤ራያ ዓዘቦ፤ተምቤን፤የዓጋመ አዉራጃ ችዋዋዎች (ቡችሎች) እና በጣም ጥቂት ከ አክሱም፤ከሽሬ ተሰግስገዉበታል፡ ነገር ግን ዋናዎቹ ፊታዉራሪዎቹ የኤርትራዉና የዓድዋዉ ጋንግስተሮቹ ነዉ ብለን በ እርግጠኝነት አሰምርበታለሁ። ለዚህም ነዉ በጣም አስገራሚ የሆነ መረጃ (ለጊዜዉ የት እንደሰወርኩት አጥቸዋለሁ ሆኖም ፈልጌ መዋቅሮቹን ላቀርብላቸሁ ነዉ። “ፈራ ተባዉ!” አልገባኝም። ይህንን በአንድ አክሱማዊ የተጻፈ እሮሮ “ጊዜ ስታገኙ ያሁ.ካም ገብታችሁ አንብቡ Another Axumite Victim - Kinfe G/Medhin! By: Gobezay Wedi-Tigray, M.A
እነ ገብሩ የተጠየቁትን ጠለቅ ብለዉ ሚስጥር ለመግለጽ የማይፈልጉበት ምክንያት ለምን እነደ ሆነ ልንገራቸሁ? ልጥቀስ፦ “They were mute, and their muteness was rather hailed as "iron-discipline. People would openly say "there is no slip of the tongue with TPLF leaders. If they want, they can listen to you all day long - if necessary for days and weeks - and in the end, you haven't heard a word from them while they have gone away with tons of information about you."…….” "TPLF leaders never leak secrets. They never knew that transparency –“------“Both the Ethiopian and masked Eritreans lived as members of the TPLF family for nearly 30 years. When the Ethiopians woke up from their long slumber, and asked Meles, "Who are you?"…” ምንጭ ኢትዮ-ሚድያ “TPLF’s Secret Document.” ሌላዉ ስለ ትግራይ እድገት እና አድልዎ የተናገረዉ ሁኔታ ምን ለማለት እንደፈለገ ግራ ገብቶኛል። የሚቀጥለዉ አባባሉን ልጥቀስ << አዲስ አበባ ወደ እሩብ ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ አለ። 90-95% በድህነት አረንቋ ዉስጥ የሚገኝ እንጂ እንደሌላዉ ሕዝብ ሃብትም ያፈራ አይመስለኝም። ስለዚህ በተለየ አጠቃቀም ተጠቃሚ ነዉ የሚለዉ እኔ አይገባኝም>>። ይላል ገብሩ አስራት።
በዚህ አነጋገሩ ከሄድን “እንደ ሌላዉ” ህዝብ “ሃብትም ያፈራ” አይመስለኝም ሲል- ሌላዉ ሃበት አፍርቶ እነኚህ ሰዎች ሃበት ያላፈሩበት ምክንያት መለስ/ህወሓት ሌላዉን ሕዝብ እየጠቀመ /ሀብት እንዲያፈራ ሲያደርግ/ሲረዳ ትግሬዎቹ ሃብት እንዳያፈሩ እያዳላ ነዉ ለማለት ይሆን? የትግራይ ሕዝብ በልማት የተራመደዉ ታታሪ በመሆኑ እና አስተዳዳሪዎቹም ከሌሎቹ አስተዳዳሪዎች ብልህ እና ታታሪዎች በመሆናቸዉ ነዉ! ተብሎ ነበር “በዘመነ ገብሩ” ትዝ ይ ላችሗል? መለስ እና አርከበ እንዲሁም ቱባ ወያኔዎች ፤ታታሪ የወርቅ ልጆች በሚያስተዳድሩት ከተማ አዲስ አበባ እንዴት 95% ትገሬዉ ድሃ ሆነ? በዚህ ስሌት 95% በድህነት አረንቋ ወለል እየኖረ ከሆነ ትግራይ ዉስጥ ያለዉ ኗሪም 95 በመቶ በድህነት አረንቋ ነዉ ማለት ነዉ ወይስ ስሌቱ ይለያያል? ክፍል 3 ከጥቂት ቀናት በሗላ ወደ ዋናዉ ክርክር እንገባለን።-….. ይቀጥላል

Sunday, October 5, 2008

ከግልፍተኝነት የእንካ-ቴስታ ጸባያችን ወይንስ ከዘረኝነት ባሕሪያችን?
ጌታቸዉ ረዳ
ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች። ትፍም ብትልባት ትጠፋለች።ሁለቱም ከ አንድ አፍ የወጡ በመሆኑ ነዉ።…መጽሐፈ ሲራክ ም/28። ከላይ በርዕሱ የተጠቀሰ የመጀመሪያዉ ሐረግ የተበደርኩት ከጦቢያ መጽሄት ነዉ።በወያኔ እና በሻዕቢያ ተፈጥሮ በነበረዉ ያፍንጫ ለፍንጫ ደም መፋሰስ ሕዘቡ ገርሞት ለጸባቸዉ የመነሾ ምክንያቶችን ሲያፈላልግ “ከኢትዮጰያ ጠባቂዉ አምላክ ጣልቃ ገብነት አስከ ትግርኛዉ ተናጋሪዎች ደርሶ-“እንካ-ቴስታ” ግልፍተንነት ባሕሪ እንደሚሆን ምክንያቶችን ተደርድሯል…”።ከሚለዉ ካነበብኩት ትዉስታ ነበር። ህሊናቸዉ ከወገንተኝነት ረግረግ መንቀል አቅቷቸዉ ዛሬም እዛዉ የሚላወሱ ጎሳ ሙርኮኞች ገብሩ አስራትን ከኪሳቸዉ አዉጥተዉ ዋሽንግተን ድረስ አስመጥተዉ በየአሜሪካን ክፍለ ሀገሮች እያዟዟሩ ከአፈንጋጩ አፍቃሬ አንቀጽ 39ኙ እና ከተምበርካኪዉ አፈቃሬ አንቀጽ 39ኙ ከሁለት መልከ ጥፉ ዝንጆሮዎች መሃል ዛሬም ለምርጫ ዉደድር አቅርበዉልናል። አንድ ጸሃፊ እንዳሉት ሱዳኖች “ዝንጆሮዋ በእናቷ እይታ-ሚዳቋ- ናት”። ይላሉ፡ ያሉትን ነገር አስታወሰኝ እና ከመልከ ጡፉዎቹ አፈንጋጮቹ እና ከተምበርካኪዎቹ መልከ ጡፉዎች መሀል “ሚዳቋዉን” ገብሩ መርጠዉ አምጥተዉልን፤ ዛሬም ጠጥቁት ይሉናል። ከጦቢያ ጋር ፍቅር ያዘህሳ ባትሉኝ፡ “ሙሻ ዘር” በተባለዉ አምዷ ያኔ ገና ድሮ ገና ከአስራ ምናምን ዓመት በፊት የወያነዉ የኢትዮጵያ ራድዮ “ምን እንጠይቃችሁ? የሚል ፕሮግራም ልናዘጋጅ ነዉ” ብሎ ነበር መሰል። ጦቢያ ደግሞ “የጠየቅነዉ መቸ ተመለሰልንና ነዉ!” ብላ መልሳችላቸዉ ነበር። ገብሩን ጠይቁ የሚል መልክት አይቻለሁ። ከዚያም ከየት አስከ የት ባሕር ተሻግረዉ አዚህ ድረስ እኛን አክብረዉ እንድንጠይቀዎት በመምጣትዎ ምስጋናየ የላቀ ነዉ፡ እያሉ በስብሰባዉ ዉስጥ እጅ መንሳት የቀራቸዉ የዋሃንም አድመጫለሁ። መጠየቁ መች ከፋ? የቸገረዉ ነገር የቀሳዉስቱ፤ድያቆናቱ፤የ አረጋዊያኖቹ፤ትላልቅ ባላበቶች፤ አገር ወዳድ የከተማ እና ገበሬዉ ለዓመታት ያቀረበላቸዉ ጥያቄ መቸ ተመለሰለት እና ነዉ በጥያቄ ላይ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቡ ሚባለዉ? ምነዉ በወያኔ የተጎዱ የወያኔ ሰለባ የሆኑ ወንድም ዘመድ ወዳጅ የሉዋችሁም? በሰዉ ቁስል ላይ ግራጫ ባትሰድዱ ምናለበት? በደም መቀለድ እኮ ሃጢያት ነዉ፡ በነዚህ አን ጠየቅም ባዮች፤ የተጠለፈዉ የታረደዉ፤በእሳት የተቃጠለዉ የተገረፈዉ፤ አካለ ስንኩል የሆነዉ የነሱ ታጋይ እና ተራ ህዝብስ ምን ይለናል አትሉም? “ለሰላባዎቻቸዉ” አክብሮት ስጡ አንጂ? ፈጣሪን ፍሩ አንጂ? ከበስተጀርባ እየጨኸ ያለዉ የሙታን እና የቁም ሰለባዎች ቁጨት እና ጭሆት አስቲ ላንዳፍታ በሕሊናችሁ አስታዉስት? ዘሎ ለነገብሩ ለባለ አንቀጽ 39ኞቹ እጅ መስጠት እኮ -ለባለጌ ማራኪ እጅ ሰጥቶ የመሞትን ያህል እኮ ነዉ።ይህን እንዴት ከመቸዉ ረሳችሁት? ለባለጌዎቹ ማራኪዎች እጁን ሰጥቶ ወደ ልምና ተሰማርቶ በገዛ ራሱ አፈር ላይ የተኛዉ ለትልቁ ሰራዊት ያልሆኑትን እነ ገብሩ አስራት ለናንተ ምን ሊበጇችሁ ነዉ? ረጋ! ረጋ! ዖረ እስኪ ረጋ በሉ! እስኪ ስለ እናንተዉ የዋህ አወዳሾች ኢትዮጵያዊያን መተቸቱ ወደ ጎን ልተዉ እና ወደ ዋናዉ አርዕስቴ ልመለስ። ገብሩ አስራት ዋሽንግተን ዉስጥ ስበሰባ ጠርቶ በነበረበት ዕለት የተደመጠዉ ጉዳይ ልንነጋገርበት ነዉ የተነሳሁት።አንድ ለመናገር ዕድል የተሰጠዉ ታዳሚ፤ (ተናጋሪዉ የትግርኛ ቋንቋ ተነጋሪ አይደለም- ያአማርኛም ተነጋሪም አይመስለኝም) አቶ ገብሩ በመምጣቱ እና በእዛ መድረክ ተገኝቶ ከህዘቡ ያለዉን ጥያቄ ተቀብሎ እንዲመልስ በመጋበዙ ለጋባዦቹ እና ለገብሩ ምሰጋናዉ አቅርቦ በገብሩ ስብሰባ ላይ አትገኙ ያሉትን ወገኖች ቅስቀሳ ደግሞ ክፉኛ አዉግዞ ቁጭ አለ። ተንጨበጨበለት። ቀጥሎ ሌሎች በየተራ ተናገሩ። አንድ ታዳሚ (የትግርኛ ቋንቃ ተናጋሪ) ተራዉ ደርሶ፤ ለትግራይ ሕዝብ ያልተባለዉን ተባለ፤ እያለ ለመለስ ዜናዊ ራዲዮ ወያነ ትግራይና መሰሎቹ የሚዲያ ጡሪዩምባኞች “ፕሮፖጋንዳ” (የ እንዲህ አሉ ወሬ) ለማቀበል ብሎም አማራዉን ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማቃቃር አስገራሚ የሆነ የነገር ማጣመም የታዘብኩት ከዚህኛዉ ሰዉ ነበር።
ሁላችሁም አንደምታስተዉሱት ጠባብ ወገንተኝነት ምን ያህል ጭፍን እና ነገሮችን ሳያጣሩ በድፍን የሚሰነዘር ሂስ ሁሉ “ሂሱ ለትግራይ ህዘብ ነዉ፤ ለትግራይ ህዝብ ነዉ” እንዲህ የምትሉት ትግራይን ለማሳጣት ነዉ ...” በማለት ልዩ ተቆርቋሪዎች ሆነዉ፤ ሌለዉ ግን ጠላት፤ ለትግራይ ሕዝብ ያለ እነሱ በቀር ሌላዉ ጎጂ አንደሆነ፤ ራሳቸዉን በጥብቅና ቆመዉለት ብዙ እሮሮ አድምጠናል(ለ17 ዓመታት ብያንስ)። ለብዙ ዓመታት በአማራዉ ላይ በህወሓት ድረጅት የተቀነባበረ ሴራ ፀረ- አማራ ቅስቀሳ እና ጎጂ እርመጃ እንደተደረገ እያወቁ፤ እነኚህ ወገኖች ሆን ብለዉ ተደርጎ እንዳልተደረገ አዉቁ እንዳለወቁ “ጀሮ ዳባ” ብለዉ የራሳቸዉን ጎሳ/ወገን በመከላከል “የነፍጠኖች” ወሬ ነዉ እየተባለ ወያኔን ለመከላከል ብዙ ዓይነት ክህደቶችና ክርክሮች ተደርገዉ አይተናል። የኮሚኒስቱ እና የአፓርታይዱ ቅይጥ ፖሊሲ የሆነዉ የወየኔዉ አንቀጽ 39 አስከ መገንጠል የተቃወመ ሁሉ እንደ ጸረ-የኢትዮጵያ ብሄረስቦችና ጸረ-ትግራይ እየተደረግን በኦነግ (ለኦሮሞ ህዝብ የመጣ መብት በማለት) እና በወያኔ ተከታዮችም (በምዕራባዊያን ተደግፎ ወያኔ ያመጣዉ ለኢትጵያ ፍቱን መድሃኒት አንቋሸሹብን በሚል) ብዙ ብዙ ተዘልፈናል። ይህ የሚቃወም ሁሉ የመጠሪያ-ስሙ’ “ነፍጠኛ- ወይም ደርግ ወይም ኢሕአፓ” አንደሆነ የምታወቁት ሀቅ ነዉ። ስለ ፓረቲዉ እና ስለ ፖሊሲዉ ግለሰዎች ሂስ ሲያቀርቡ የተባለዉን ቅሬታ በቅጡ ሳይመረምሩት፤ እራሰቸዉ ግራ አጋብተዉ የሌላዉን የዋህ ሰዉ አይዕምሮ የሚያምታቱ “ጠባቦች” መች መማር እንደሚችሉ እና ራሳቸዉን ከወገንተኝነት ነጻ ሳያደርጉ ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ይልቅ አነሱ ብቻ ለትግራይ ህዝብ ልዩ ተቆርቋነት ስሜት ኖሯቸዉ እንደቆሙ እየሆኑ ፤ሂስ በተሰነዘረ ቁጥር በቁጣ የሚነድዱ ቁጥራቸዉ እጅግ በጣም በርከት ያሉ የትግራይ ተወላጆች ዛሬም ድሮ ከነበሩበት ስሜታቸዉ መላቀቅ አቅቷቸዉ ሲያስቸግራቸዉ ይደመጣሉ። ለምሳሌ “አቶ ጌታቸዉ-..” (የአባታቸዉ ስም ማን እነደሆነ ያልተገለጸ) የተባሉት አድማጭ ስለ መገንጠል (አንቀጽ 39ኝን አስመልክቶ) እና ስለ ወያነ በወታደራዊ ተቁዋማቱ እና በመንግሥታዊ ዋና ዋና ሞተሮችና እስከ ታች ያለዉ መዋቅር ወገንተኛ ስለ መሆኑ በመዋቅሩ ላይ የሚታዩት (ገብሩ አስራት ሳይቀር ያመነበት) አድላዊ/ጎሳዊ ተግባሮችን በመዘርዘር ሲጠቁሙ፡ አቶ ጌታቸዉ( አባት ስም አልተገለጸም….?) የተናገሩት ሂስ በመጻረር/በማጣጣል ብቻ ሳይሆን በጥላቻ ነጉዶ እሳት እንደበዛበት ቡና በድንገት ገንፍሎ አንድ የትግራይ “ቁጡ ሰዉ” አቶ ጌታቸዉን ቀና አስተያየት አጣምሞ እንዴት አማራዉ እና ትግሬዉን ለማያያዝ እንደተጠቀመበት የሚከተለዉን ልጥቀስ።ልጥቀስ -ቃል በቃሉ“….. ያለዉ ነገር ሰምታችሁታል? አንድ የተናገረዉ መርዝ አለ።ምንድ ነዉ ያለዉ!? አማራዉን አስከ መቸ ጊዜ ድረስ ልንለምን ነዉ ብላችሁ ልትገነጠሉ ነዉ ወይ? አለን!.. Right at our face!!! How dare!? አንዴት?... እንደዚህ እየተናገርን ነዉ መለስን ምናወረደዉ?.......... አሜሪካ ዉስጥ ያለዉ ከ-----አስ.. ከ አፍራሽ ነዉ። ሕዝብ እና መንግሥት መለየት አልቻልንም!”
በማለት ነገሮችን አጣምሞ ከየት ወዴት አንዳምታተዉ የተከታተላችሁ ሰዎች ልብ በሉ። ሰዉየዉ ንግግሩን ጨርሶ ሲያበቃ የሁለቱንም ወገኖች ንግግር በቅጡ ሳይከታተሉ የዚህኛዉ ሰዉ ንግግር ብቻ ሚዛን የሰጡት “ዕዉራን ንቦቻቸዉ” በደማቅ ጭብጨባ ሲሸኙት/ሲደግፉት ይደመጣል.. ጨብ…ጨብ ጨብ!) የአቶ ጌታቸዉ…. መልስ ለመስጠት ዕድል ተሰጥቶት አሱን ለማብረራት፤ አንደሚከተለዉ ይደመጣል።ቃል በቀል ልጥቀስ “…ወንድሜ… Right at our face! አንዴት እንደዚህ ትለኛለህ ላለዉ፡ “ሚስ አንደርስታንድ” አድርጎኛል። እኔ ያልኩት አሁን ያለዉ የአቶ መለስ አገዛዝ “ስቲል” የመገንጠል አጀንዳ እንደያዘ ነዉ።ይሄነን የሚጠቁሙ አንዳንድ ነገሮች ያሉ ይመስለኛል…..።” ብሎ ይዘረዝሩ እና አቶ ጌታቸዉ በመቀጠልም “ …ይሄ መንግሥት አንቀጽ 39ኝን ትግራይን ለመገንጠል፤ ከመሃል አገር “ስልጣን ያጣ ከሆነ መጨረሻ መደራደርያየ ተከዜ ላይ ቆሜ ይህንን የኢትዮጵያ የዘረኞች ስርዓት አቆማለሁ፡ የሚልበት አስተያየት ይኑረዉ ይሆን ወይ? ከናንተ እየለመንን አንኖርም፡ ከአሁን በሓላ፤ የሚል ስሜት ይኖረዉ ይሆን ወይ? ነዉ እንጂ ያልኩት፤ ስለ ትግራይ ሕዝብ አይደለም ያልኩት። ያልኩት ስለ መንግሥት ጥያቄ ጉዳይ ነዉ”። በማለት “ትግሬዎች አማራዉን አስከ መቸ ልንለማመጠዉ ነዉ እያሉ ነዉ” ብለሃል በማለት “መርዝ” ብሎ የሰየመዉ “የራሱን መርዝ” ወደ አማራ እና ትግሬ እንዴት ለማያያዝ እንደሞከረ አይታቸሗል። ሰዉየዉ ስለ አንድነት ሲሰብክ ቆይቶ ወደ አማራ ሮጦ መርዙን ለመርጨት ደቂቃ አልፈጀበትም።
እኛ ሰዎች የጌታን ቃል እያምታታን፤ ሊቃዉንትና ሓዋርያት መጽሐፍ ቅዱስ ከተዉልን ትርጓሜ ዉጭ የየራሳችንነን ትርጉም እየፈለሰፍን ያለ ፈርሃት በድፈረት የጌታን ቃል ጠምዝዞ ተርጉሞ የመዳፈርን ባሕል ያደረግነዉ የዓለም ፍጡራን ሁሉ፡ ሰዎች በንግግራቸዉ ላይ ያልደመጠ፤ ያልወጣቸዉ ቃል ብለዋል፤ እያልን በሕዝብ ስም ማምታታችን እስከ መቸ እንደምንቀጥል ይገርማል።ይህ ግንፍል እንካ-ቴስታ ጠባያችን ይሁን ወይንም ከዘረኝነት ባሕሪያችን መታረም የምንችለዉ መቸ እንደሆነ ብዙ ሰዉ የገረመዉ ጉዳይ ነዉ። አሜሪካ ዉስጥ ገብሩ አስራት በበሰበሰበዉ የዓረና ድርጅት ስበሰባ ላይ የተገኙት “ነፍጠኞ-የገብሩ አስራት ወኪሎቹ ፡“የትግራ ህዘብ አማራዉን ስንት ጊዜ ልንለማመጠዉ ነዉ ያላሰብነዉን ፤ያላልነዉን (ስብሓት እንኳ ያረጋገጠልን ቢሆንም) እንገነጠላለን እያለ ነዉ… “ እያሉ የትግራይን ህዝብ እያሙትና እያስራቁት ነዉ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ሊነጥቁት እየተንደረደሩ ነዉ….. ወዘተርፈ…” በማለት ወሬ የሚቀላዉጡት “የወያኔ-ትገሬዎች” እንደሚያራቡት አትጠራጠሩ።ከዚህ ሥራ/አስተዋጽዎ ሌላ ምን ከሰማይ የሚወርድለት መና ይኖራል? ፈጣሪዉ ካልፈራ፤ አንድ ነገረ ሰሪ “የወያኔ ዕዉር ንብ” የሰዉየዉን (የእሮሮዉ አቅራቢ) ቴፕ ብቻ ቀድቶ መቀሌ ዉስጥ ላለዉ “ድምጺ ወያነ ትግራይ” ቢልከዉ፤ እዉነት መስሎት “የወይን ራዲዮ” ፤ ቱልቱላዉን እያናፋ የሚፈልገዉን የማምታቱ ስራዉ ያችን የግንፍሉን ሰዉየ ቃል “ጫፍ” ይዞ መከረኛዉ ሕዝብ አሁንም አልተኝሉህም ሊሉት ነዉ። እኛ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የተቻለንን ለብዙ ዓመታት ዉዥምብሮችን ግልጽ ለማድረግ ሞከረናል ነዉ። ቢሆንም ክቡር ፐሮፈሰር/ዶክተር ጌታቸዉ ሃይሌ በአዲሱ መጽሃፋቸዉ በ “አንዳፍታ ላዉጋችሁ” እንዳሉት “ጎጠኛ እና ጎሰኛ በወረራት ሀገር ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ስለ ሕዝቧ ዕኩልነት የሚናገር የኔ ብጤ ጠላት ማፍራቱ ሳይታለም የተፈታ ነዉ”። እንዳሉት፤ በእኔም ሆነ እኔን በመሰሉ ኢትየያዊያን ትግሬዎች የጥላቻ እና የማግለል ዘመቻ ተደርጎብናል። ሖኖም ታሪክ የሗላ ሗላ ማንን አንደሚአገልል፤ ወደፊቱ የሚታይ ይሆናል። እስከዛዉ ድረስ ግን ብዕራችን የሚዉጥ ሃይል አይኖርም። ለትግራይ ሕዝብ አሳቢዎች እና ተቆርቃሪዎች ከኛ ወድያ ላሳር የሚለዉን ወገንተኝነት፤ተምክሕት ተጠራጣሪነት እና ጎጠኝነት፤ግንፍልተኝነት ለማስቀረት እንሞክር። አማራ፤አማራ ዪሚያሰኘን ጸረ አማራነት ስካር ለማብረድ አንሞክር።
የሚቀጥለዉ ምዕራፍ ሁለት ስለ ትግራይ በልማት ተጠቅሟል ወይስ አልተጠቀመም የሚለዉን የገብሩን አቋም በተጻራሪ የቆምኩበትን ሰፊ ሀተታ ከነ ማስረጃዉ በሚቀጥለዉ አቀርባለሁ፡ ተጠባበቁ።_ ፧-፧ አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ።’-/’- http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

Thursday, October 2, 2008

ወደ ዉሸት ቀፎ የሚበሩ ዕዉራን ንቦች


ወደ ዉሸት ቀፎ የሚበሩ ዕዉራን ንቦች ጌታቸዉ ረዳ ዉሸት አገር ይፈታል ቅማል ሱሪ ያስፈታል የሚለዉ ምሳሌ ለዘመናት ሲደመጥ የኖረ ቢሆንም ለምሳሌዉ ተስማሚ ጊዜ ያገኘበት ጊዜ ቢኖር “ዉሸቱን ተቀብሎ በጭፍን የማመንን ባሕሪ፤ክህደትን፤አጭባሪነትንና፤ እየዋሹ ያለማፈርን፤በዛዉ ሐፍረተ-ቢስነት በሕሪ የመቀጠልን” አጠቃልሎ እነኚህ ነዉር የሆኑ ባህሪዎች እንደ ባሕል ተደርጎ የተወሰደ ዘመን እንደዛሬዉ ዘመን ከቶ የነበረ አይመስለኝም።
በ17 ዓመት ዉስጥ የታዘብኩት ባርኔጣቸዉን እያነሱ “ኖር” ብለዉ ቀጤማ ጎዝጉዘዉ ዉሸትን የሚቀበሉ ዜጎች ወየነ ወደ መንግሥትነት ከተለወጠ በሗላ ቁጥራቸዉ እያደገ መሄዱን ነዉ። የታሪክ ዘለፋ ብሎም ታላላቅ አዛዉንትን ሊቃዉንትን፤አርበኞችና ጀግኖችን የነገሥታትን እና የጀግኖች መታሰቢያ ሀዉልቶችን፤መቃብሮች እና በሀገር ዉስጥ የተፈጠሩ ፊደላትንና ቋንቋን የማጣጣል ባህል እና አረጋዊያንን የመዳፋር ባህሪ ባጠቃላይ-(“ዉሸት”-) የተጀመረዉ፤ በኤርትራ ነፃ አዉጪዎች ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ግምባሮች ወርዶ በወያኔ ተንከባካቢነት ነብስ ዘርቶ፤ የወጣላቸዉ የዉሸት ሰባኪያን በከፍተኛ ፍጥነት እየተራቡ/እያደጉ እንደመጡ አስተዉለናል።ዉሸት እንደ አዲስ ቅጂ/ሞዴል ሆነ እና “ስልጡን ፖለቲካ” ብለዉ ስመ-ክርስትና አወጡለት። ወያኔም፤ሻዕቢያም ሆነ በሕዝብ የጅምላ ግድያ እጁን በደም የነከረዉ እስካሁን ድረስ ከሳሽ አጥቶ የታሪክ ቀኑን እየጠበቀ ያለዉ “ኦነግ” እና የመሳሰሉት የፖለቲካ ተዉሳኮች፤ በኢትየጵያ ምድር ዉስጥ የታዩት የገዢ መደቦችን ሥልጣን ለማረጋገጥ ሲባል ወደ ሗላ ሩቅ ያለፉት ዘመናት በታዩት እርስ በረስ የተገፋፋንበትን እና የተፈጥሮ ሕግጋት ሆኖ ያገር ግንባታን/ታሪካዊ ክስተቶችን/ ለማፋጠን የተከናወኑበት ሂደቶችን በሕዝብ መሃል እንደተደረጉ ግጭቶች እያስመሰሉ በዘረኛ ስበከት ለሥልጣን ጥማቸዉ “በዉሸት” ሕዝቡን እያምታቱ ለስደት እና ለሞት ዳርገዉ በአዲሱ ትዉልድ- “በወጣቱ” ሕሊና ዉስጥም ይህንኑ ዉሸት አሰርገዉ በመመገብ ጥላቻዉ ብጥብጡ ስደቱ እና ሞቱ እንዲቀጥል ዉሸት መሳሪያቸዉ አድርገዉ ሕዘብ ከሕዝብ ሲያጋጩ ይገኛሉ።
ለምሳሌ፤- ባለፈዉ የቅንጅት መሪዎች ነን ብለዉ “እናንተን-አንድ ለማድረግ መጣን” በሚል ሽፋን/ዉሸት እኛኑን አጣልተዉ አራርቀዉ ከምንወዳቸዉ እና ከምናከብራቸዉ ወዳጆቻችን ሳይቀር በዉሸት ስበከታቸዉ አለያይተዉን በጋራ አንድ ሆነዉ መጥተዉ እነሱም ራሳቸዉ ተበጣብጠዉ ወደ መጡበት ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለሱ አንዳንድ አዉራዎቻቸዉም አሜሪካን አገር ጥገኝነት ጠይቀዉ በመቅረት ዉሸታቸዉን በረቀቀ/በአታለይ መንገድ ሳይሆን በግልጽ እየዋሹ፤ ዉሸታቸዉን እንደ ባሕል ተቀብለዉ የሚያስተናግዷቸዉ እዉቅ የዉሸት ኢነተርፕረነሮች አንደ አሸን ፈለተዋል።
ያለፈዉ ታሪካችነን ስንመለከት የአንድ ትዉልድ እልቂት ሊከናወን የቻለዉ በሁለት ዓመት ዉስጥ ነበር።የአንድ ትዉልድ እለቂት ለማከናወን ሚና የተጫወተዉ “ዉሸትና ማጭበርበርን” ተጠቅሞ ህዘቡን በማደንዘዝ የሥልጣን ጥምን” ለማርካት ነበር። ዋሾች መዋሸት ብቻ ሳይሆን መንግሥታዊ ሰገነት ከያዙ ግድያ ዉስጥም ይገባሉ።ይህም ማለት እንደሰዉ ትክክለኛዉ የፖለቲካ ጨዋታ ሊጫወቱ አይፈቅዱም።ሕጉን ተከትሎ ልጫወት የሚለዉን ከፊት ለፊት ደንቅሮ የሚቆምባቸዉን ሁሉ የወሽት ድሩ ተጠቅሞ ሌሎቹን ጥሎ ከጫዋታ ዉጭ ለማድረግ ይሞክራል።በሂደቱ ለፍትህ የሚደረጉ ትንቅንቆች ይበለሻሉ ፤ወይም ዋሾዉ ስልጣን ለይ ወጥተዉ ሌላ የመከራ ጊዜ ይቀጥላል ወይንም ህዝቡን በስቃይ እየገረፈ ያለዉን ስርዓት ዕድሜዉን እንዲረዝምለት አስተዋጽኦ ያደርጋል። በቅርብ የታዘብነዉ ትምህርት-እናንተን ለማስታረቅ እና አንድ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መጣን ያሉንን ዉሸተኞች እኛኑን ለጥገኝነት ሽፋን ተጠቅመዉ፤ አንድ ማድረግ ቀርቶ አብረዉ እንደ መጡ አብረዉ መመለስ ያቃታቸዉ ምክንያት ሲጠየቁም “እናተ ሁሉ ምንድናችሁ ማለት ነዉ? ለምን ተነጥላቸሁ ቀራችሁ ስትሉን እኮ አናነተን ራሰችሁን ሁሉ እኮ እየሰደባችሁ ነዉ?!” ብለዉ ሲመልሱ፤ እንደዚህ ዓይነት የዓለም--ምፅዓት ታይቶም ተሰምቶም አያቅም። ይህ አስገራሚ ክንዉን ሲፈጸም ቁጥሩ በጣም የማይናቅ ሕዝብ ዕቅፍ አበባ እያበረከተ ቀጤማ ይነሰንስላቸዉ ነበር። ደማቅ ዉሸት ሲዋሹም ደማቅ ጭብጨባ ይደረግላቸዉ ነበር።በዉሸት የታካኑ ቁንጮ የመድረክ ኢነተርፐሬኖሮችም አዟዟሪ/አስጎብኚ አድርገዉ ዉሸትን እንዲቀበል ህዘብን የማደንዘዙ ሥራ ተሰርቷል።አሁን ወደ ሗላ መለስ ብለችሁ ስታስተዉሉት እኮ፤ በዉነት አስገራሚ ትዕይንትና “ታላቁ ሽወዳ” የሚሰኝ መጸሃፍ የሚያስጽፍ የፖለቲካ ሸቀጥ ነበር።
ዋሾች ትልቁ እና ዋናዉ ሚናቸዉ ተከታይን ማደንዘዝ ነዉ።አድማጩን አስቀድሞ ከሰለበዉ፤ በሕሊና ስካር ዉስጥ የሚዋልል የደነዘዘ አድማጭ እዉነት ዉሸት ይደበላለቅበት እና ለዉሸትም ለእዉነትም እኩል ቦታ ይሰጣል።ሲዋሹ ያንጨበጭብላቸዋል - እወነቱን ሲናገሩም ያንጨበጭብላቸዋል።ለነሱ ሁሉም እኩል ነዉ። ሂትለር ደማቅ ዉሸቱን ሲዋሽ ደማቅ ጭብጨባና ጭሆት ሲለገስለት የነበረዉ አድማጩን አስቀድሞ በዉሸት በማደንዘዙ ነዉ። በዋሸ ቁጥር አድማጩ የዉሸት ሱሰኛ እየሆነ በመሄዱ፤ ሂትለር መድረክ በጠራ ቁጥር ድምጹን ለማዳመጥ ይቋምጡ ነበር።ጨካኙ የኛኑ ኮሎኔል በወታደራዊ ልበሱ የብዙዉ ሰዉ ዓይን ማርኳል።
እነዚህኞቹም እናንተን ለማስታረቅ ነዉ የመጣነዉ ብለዉ ሲሰብኳቸዉ፤ ተከታዮቻቸዉ የእዉነት መስሏቸዉ ጆሯቸዉ ተማርኮ የዉሸተኞቹ ስበከት ሱሰኞች በመሆን በቃላት ሊገለጥ የማይችል ካበድ የሕሊና እከክ አተርፈዉ፤ ዛሬ ዋሽዎቹ ስበሰባ ባዘጋጁ ቁጥር ሮጦ ለማዳመጥ ሲንጋጉ ይታያሉ። በስነ ሕሊና ሕግ በየዋህ አድማጭ ላይ ወንጀል ፈጸመዋል ማለት ይቻል እንደሆን አላቅም አንጂ -የሆነ ጉዳት እነዳደረሱባቸዉ አልጠራጠርም። የአገሪቱን ፖለቲካ አስተካክላለሁ ብለህ በግምበር ተሰልፌአለሁ ብለኸን እናንተን ለማስተረቅ ከ ኢትዮጵያ መጥቻለሁ(ለመምጣቴም ምክንያት የኸዉ ነዉ) ብለህ አንተ እና ጛደኛህ ለምን አዚህ ለመቅረት ወሰንክ ተብሎ ስለተጠየቀ “እናንተም ሁሉ እኮ ራሳችሁን እየሰደባችሁ ነዉ! ቀረሁ አልቀረሁ የራሴ ጉዳይ ነዉ፤ ምን ያገባችሗል?”ለምን ተጠየቅኩ ብሎ በድንፋታ ሲመልስ “ለምን በኛ ስም መጣህ? “ዋሻኸን”።ከዋሸህም፦ ከፖለቲካ መድረክ ራሰክን አስወግድ” ብሎ ከመመለስ ይልቅ ላከበረዉ ህዝብ እንደዚያ ዋሽቶ እነሱን አሳንሶ ሲያቀላቸዉ (ግርምቢጥስያ ማይ ንዓቐብ!) ደማቅ ጭብጨባ ለገሱለት። ይሄ በሽታ ነዉ። ስም ያልተሰጠዉ በሽታ።እንደዚህ ዓይነቱ ለዉሸት ራሱን የሚያስገዛ ምቹ ሕዝብ እየበረከተ ባለበት ወቅት ከቶ እንዴት ሕዘባችን ወዳጁ እና ጠላቱን ለይቶ አዉቋል እያልን እንሰብካለን? ብሎ ለሚጠይቅ መልስ የማገኝለት አይመስለኝም።
የምንቆጭለትን ከባዱን ኢትጵዊ ባሕላችን ያለ መዋሸትን ተረግጦ ዉሸትን ያክል ትልቁ አስነዋሪ ሸክም በጫንቃቸዉ ተሸክመዉ ወደ ባሕር ማዶ ሲመጡ ትከሻቸዉ በስፋት አለጥልጠዉ አመቻችተዉ የሚረከቧቸዉ የቁም ሙታን ብብዛት እንዳሉ አላጡትም ነበር’ና አገር ዉስጥ የ “የሙት -ከተማ” የትግሉን አድማ አንዳስወረዱት ሁሉ እዚህም መጥተዉ አንድነታችነን አደፈረሱት። ወያኔ ሲያቀብጠዉ በሳጥን ድምጽ ዕድሌን ልሞክር ብሎ ገብቶ አክ እንተፍ መባሉን መርዶዉን ሲሰማ፤- ርሸናዉን አጧጥፎ አሸነፍኩ በማለት “ነቨር-ኤገይን!” (አይደገምም!አይታለምም!) ያለንን የጫካዉ ሰዉ ወያኔን ማዶ ሆኖችሁ መታገል “ነዉር” ነዉ እያለ ሲየዋግዘንና “ሲያንኳስሰን” የነበረዉ “ብርሃኑ ነጋ” -ትግሉን መምራት- ከማዶ ሆኖ ነዉ ብሎ እኔ የምመራዉ ድርጅት አለ እና ይህ ቅጽ/ፎረም ሞልታችሁ እኔን ተከተሉ እያለ በየ አሜሪካን ክፍለሀገሮች ተዟዙሮ ሲቦተልክባቸዉ አሰየዉ አሉት። ስለዋሾቹ ማንሳት ቢሰለቸኝም የዕምብርቱ ችግር እነሱ ስለሆኑ ብንወድም ብንጠላም የምንመለስበት ሐዲድ ሆኖ እናገኘዋለን።
አንድነት ይፈጠር ሲባል፤ለግብር ይዉጣ ተለጣጥፋችሁ ርገጉ ማለት መሆን የለበትም። ዋሾቹ ብዙ የዉሸት አድናቂና ተካታይ መቀፍቀፋቸዉን እሰካላቆሙ ድረስ እንቅፋት ለትግሉ ደንቃሮች ናቸዉና መታቀብ ካልቻሉ /ዉሸታቸዉን አስካላቆሙ/ ድረስ የብዕር ጦርነቱ የቀጥላል። አስቀድሞ ትግሉ የሚካሄደዉ በዉሸት መሆን አለበት። ወያኔም ሆነ በተቃዋሚ ስም የተደራጁት ዋሾች ሁሉ በቅደም ተከተል በአንድ እና በሁለተኛ ደረጃ አይመደቡም። ምደባቸዉ ሁለቱም በአንደኛ ደረጃ ጠላትነት ዉስጥ ነዉ። ጠላትን ለመግደል እንዲአመች ምሽግክን ለጠላት እያጋለጠ የሚያስመታህ አስቀድሞ መግደል አሾክሿኲዉን ነዉ፡ የተባለዉም ለይስሙላ አልነበረምና በዚህ ብዥታ መኖር የለበትም።
ለምንድ ነዉ ይህ ለማለት የተገደድኩት? የኢትዮጵያ ግምባር ቀደም አረጋዊ መሪዎችን፤ ምሁራንና የፖለቲካ ታጋዮችን ክብርና ስም ሲዘልፉና ከዋሾች አንደበት የሚወጣዉ የዉሸት ሰበካ ለማድመጥ ወደ ዉሸት ቀፎ የሚበሩ ብዙ ዕዉራን ንቦች አሁንም አሉን። አንድ ቀን እግር ጥሎኝ በአንድ ሦስቱ ያከል የፓል-ቶክ መድረክ ገብቼ ያዳመጥኳቸዉ ረዢም ሰዓታት በጣም የሚያስገርም እና በስሜት የሚጋልብ ጭንቅላት መድረኩን ዉጦት የታዘብኩትን ልግለጽ። ለስሜታቸዉ ግፊት ዋነኛዉ መሳርያ የሚጠቀሙበት -እዛም- ቢሆን “ዉሸት” ነበር። አንዲት የዋህ በልቅሶ ስቅስቅ ብላ ስለ ኢትዮጵያ ችግር ስታለቅስ ሰምቻለሁ። ልጅቷ ሃገር ፍቅር ኖሯት ማልቀሷን የማከብራት ብሆንም፤ አሳዛኙ ክስተት ደግሞ የዋሾቹ ሰለባ ሆና እነሱን ስታሞግስ እና ለሚያስለቅሳት ያገሯ ተደጋጋሚ ችግር አነሱ አንደሚፈዉሱት አድርጋ ራሷን በእርግጠኝነት ስትሟገት መስማቴም አዘነኩላት።አነኚህ ንቦች ናቸዉ።ንቦቹ ንግሥቲቱ ወደ ጭስ ብትመራቸዉም አብረዉ ይቀቀላሉ።ዕዉራን ናቸዉና ወደ ዉሸት ቀፎ ይገባሉ።ለዚህም ነዉ በዉሸት ላይ መዝመት ለትግሉ ተቀዳሚ ፈዉስ ነዉ የምለዉ። ጽሁፌን በዚህ ስደመድም፡ለማስታወሻችሁ ይረዳ ዘንድ ታች የምታነቡት የዋሾቹን ማሕደር ጣል ላድርግና ልሰናበታችሁ።
ጠያቂ_ ከሌላኛዉ የቅንጅት ግሩፖች…. ጋር ያላችሁ ልዩነት የሌላኛዉ ግሩፕ የጭቃ ሹም አስተዳደር የምስለኔ እንዲሁም ደግሞ የጭቃ ሹም አስተዳደር አራማጆች ናቸዉ። እኛ ግን ዲሞክራቶች ነን የሚል ነዉ። ይሄንን፡ ከዚህ በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በንግግርዎም በቪኦኤ ምልልስም እንደዚሁም ጓደኛዎ ክቡር አቶ አንዳረጋቸዉ ጽጌ በኢንተርኔት ባሰፈሩት ይህነን ባተኮረ አስፍረዋል። የኔ ጥያቄ በሕዝብ ዉስጥ የሚነገር አንድ ንግግር አለ።ከዚህ በፊት የተከበሩ ደ/ር ብርሃኑ ነጋ የተከበረች ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳንና ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በቀስተ ዳመና ፕረዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በቀጭን ትዛዝ ለካዉንስል ምክር ቤት እንዲሁ ሳይመረጡ በእርስዎ ዉሳኔ ብቻ አሰመርጠዋቸዋል። የሚባል ነገር አለ እና ይህነን አድረገዋል ወይ? ይህስ ካደረጉ ሌሎችን ሳልነካ በእርስዎ ላትኩርና እራስዎን የዲሞክራሲ ጠበቃ አድርገዉ ለማቆም የሚየያስችል የሕሊና ንጽህና አለዎት-ወይ?
የብርሃኑ ነጋ መለስ፦ Really, በጣም ባጭሩ ነዉ የምመልሰዉ። መጀመሪያ የጠየቁት ብርቱካንና አንዳረጋቸዉን በቀጭን ትእዛዝ የካንስል አባላት አድረገሃል ነዉ። ያለኝም በጣም አጭር መልስ ነዉ። መልሱ- “ዉሸት ነዉ!” (ብርሃኑ ከካደ በሗላም- የዕዉራን ንቦች- ጭብጨባ ይደመጣል-ጨብ!!!! ጨብ!!!! ጨብ!!!!!!!!!!!) የአንዳረጋቸዉ ጽጌ መልስ ከታማኝ (ቲቪ ቃለ በጠይቅ) አድርጎ ለብረሃኑ ነጋ መለስ የሰጠዉ እዉነታዉ ቀጥሎ ያለዉን ያንብቡ።
ታማኝ- አቶ አንዳርጋቸዉ የቅንጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባል ነበሩ ወይ? “አዎ! ከዛ በፊት የማንም ድርጅቶች አባል አልነበርኩም።ልወጣ ስል ነዉ ብረሃኑ መጥቶ ይሄ ሁሉ ስራ ሰርተህ ሰዉስ ምን ይላል (አንዳረጋቸዉ ሁኔታዉ እያሳቀው መሰለኝ አግርሞት ሳቅ ሲስቅ ይደመጣል/ይታያል)…እዚች ላይ ፎርም ሙላ እና ሞልተህ ብትሄድ ይሻላሃል፤ ብሎ ብርሃኑ ነዉ የቀስተ ዳመና ፎርም አስሞልቶኝ ነበር። እና ቀስተ-ዳመና ሰዎች ወደ ላዕላይ ምክር ቤት በሚያስገባበት ሰዓት ላይ “ኦል-ሬዲ” እኔ ዉጭ ከወጣሁ በሗላ የስራ አስፈጻሚ ኮሞቴ አባል አድረገዉ አስመርጠዉኝ ነበር። እኔ በሌለሁበት ነዉ ምርጫዉ የተካሄደዉ። አቶ ዳኒኤልም ነበር። እኔ በሌለሁበት ነዉ ምርጫዉ የተካሄደዉ። አቶ ዳኒኤልም ሌሎችም በስልክ ነግረዉኛል፡ምን ዓይነት ምርጫ እንደነበረ። ይሄ በ “ኖሚነሽን” ከሌሎቹ ሰዎችም ጋር እንድወዳደር አይደለም የሆነዉ በቀጥታ በ“አክላሜሽን” ነዉ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያደረጉኝ።”
(እንግዲህ ከላይ ብርሃኑ በሕዝብ ፊት የሰጠዉ መልስ እና ሌሎችን በምሰለኔነት ሗላቀርነት ሲከስስ- አወዳድሩትና ገምግሙት-)።
ብርሃኑ ነጋ፦ “ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካ ትግል ዉስጥ ከገባሁ አንድ 6 ወር 7 ወር ቢሆን ነዉ።ከዚያ በፊት ያሉት ነገሮች ብትጠይቁኝ “አላቅላችሁም!” ነዉ የምላቸወሁ። “ሶ” ኮንተይን/ (ኮንስንት..?) የምናደርገዉ በነዚህ ጊዜዎች ነዉ።”
ብረሃኑ ነጋ፦”ኢሰንሺያሊ-ሞር ዛን ኤኒቲንግ ኤልስ/ ወደ ትግሉ ልገባ የፈለግኩት በኢኮኖሚዉ ምክንያት ነዉ”:
{አንባቢ-ልብ በሉ።ሰዉየዉ የገባዉ ቅደሚያ ኮኖሚዉ አሳስቦት እንጂ ፖለቲካዉ አልነበረም። ኢኮኖሚዉ አድጎ በልጽጎ ቢሆን ወያኔ ያፈለገዉ “ግራዚያኒም ሆነ ፈራንኮ፤ሂተልርም ይሁን ፖልፔት” ፖለቲካ ዉስጥ ባልገባ ነበር ነበር ማለት ነዉ። ዓይኑ ትኩረቱ -ሞር ዛን ኤኒቲንግ ኤልስ- “ኢኮኖሚዉ” ላይ ነብርና ወደ ትግሉ ከ6 ወር በፊት ወደ ፖለቲካዉ ሊገባ የቻለዉና በዋናነትያሳሰበዉ)። ግምገማዉ ለናንተዉ ልተዉ።
ብረሃኑ ነጋ። ጦርነት ላይ አንገባም ስትሉ ኢሕአዴግ ጋር ተስማምታችሗል ወይ? የሚል ጥያቄ አለ። … የተስማማንበት ነገር የለም፡፤ አሱ ማለት ከሆነ። እኛ ከዚህ ፖለቲካ ዉስጥ የገባነዉ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ነዉ።ጦርነት ለማካሄድ የሚፈልግ ይችላል። ዕድሉ መሞከር ይችላል።ጦርነት የሚፈልግ ጦርነት ካለበት ቦታ ሄዶ ይዋጋ።እኔ አንድ አድቫይስ የማደርገዉ፤ ጦርነት ሚፈለግ ሰዉ አንተንም ልጆችህንም አሱም ለጆቹንም ጨምሮ የሚታገል መሆን አለበት ነዉ የምለዉ። ሌላ የድሃ ገበሬ ልጅ የሚያታገልበትና ከዉጭ ሆኖ አመራር የሚሰጥበት ዓይነት ጦርነት ካሁን በሗላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያቆመ መሰለኝ።
(እንግዲህ ዶክተሩ የራሱን ድርጅት መስርቶ በ አመራር ደረጃ ተቀምጦ እዉራን ንቦቹን እያደናበረ ዉጭ አገር ነዉ የለዉና- የሚቀጥለዉ ተዕይንት አበረን ለማየት ያብቃን።) ዉሸቱ የመጽሃፍ ክምር ሊሆንብን ነዉና በዚህ ላብቃ።አምላክ ኢትየጵያን ይጠብቅ//-// www.ethiopiansemay.blogspot.com